መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘዳግም 27

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሙሴና የእስራኤል አለቆች ሕዝቡን እንዲህ ብለው አዘዙ፦ ዛሬ የማዛችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ።
2አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ ጥቂት ትልልቅ ድንጋዮችን አቁሙና በኖራ ለስኑአቸው።
3የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ማርና ወተት ወደምታፈሰው፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን ስትሻገሩ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ጻፉባቸው።
4ዮርዳኖስን እንደ ተሻገራችሁም ዛሬ ባዘዙአችሁ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ ላይ ትከሉአቸው በኖራም ለስኑአቸው።
5እዚያም ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የድንጋይ መሠዊያ ሥራ፥ በድንጋዮቹም ላይ ማናቸውንም የብረት መሣሪያ አታሳርፉባቸው።
6የእግዚአብሔር የአምላካችሁን መሠዊያ ካልተጠረበ ድንጋይ ሥሩ፥ በላዩም ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡበት።
7በላዩም የኅብረት መሥዋዕት ሠዉ፤ ብሉም፤ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ደስ ይበላችሁ።
8በድንጋዮቹም ላይ የዚህ ሕግ ቃላት ሁሉ ግልጽ አድርጋችሁ ጻፉባቸው።
9ሙሴና ሌዋውያን ካህናትም፥ ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ተናገሩ፦ እስራኤል ሆይ፥ ጸጥ ብላችሁ አድምጡ! እናንተ ዛሬ የእግዚአብሔር የአላካችሁ ሕዝብ ሆናችኋል።
10ስለዚይም እግዚአብሔር አምላካችሁን ታዘዙ፥ ዛሬ የሚሰጣችሁን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ጠብቁ።
11ሙሴ በዚያኑ ዕለት ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዘ፦
12ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ ስምዖን ፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዮሴፍና ብንያም ወገኖች ሕዝቡን ለመባረክ በገሪዛን ተራራ ላይ ይቁሙ።
13ሮቤል፥ ጋድ፥ አሴር፥ ዛብሎን፥ ዳንና ንፍታሌምወገኖች በጌባል ተራራ ላይ ለመርገም ይቁሙ።
14ሌዋውያን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብለው ይናገሩ፦
15ጥበበኛ የሠራውን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ የሆነውን ምስል የሚቀርጽ ወይም ጣዖትን የሚያበጅ በስውርም የሚያቆም ሰው የተረገመ ይሁን። ሕዝብም ሁሉ፥ አሜን ይበል።
16አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገም ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል።
17የባልንጀራውን የድንበር ድንጋይ ከቦታው የሚያንቀሳቅስ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል።
18ዐይነ ስዉርን በተሳሳተ መንገድ የሚመራ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል።
19በመጻተኛው፥ አባት በሌለውና ባል በሞተባት ላይ ፍትሕ የሚያዛባ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል።
20ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን፤ የአባቱን መኝታ ያረክሳልና። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል።
21ከማናቸውም እንስሳ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚያደርግ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል።
22የአባቱ ወይም የእናቱ ልጅ ከሆነችው ከእኅቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን።
23ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል። ከሚስቱ እናት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል።
24በድብቅ ባልንጀራውን የሚገድል የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል።
25ንጹሕውን ሰው ለመግደል ጉቦ የሚቀበል የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል።
26የዚህን ሕግ ቃሎች በመፈጸም የማይጸና የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።