መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘዳግም 26

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ ወደ ሚሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፥ ስትወርሱአትና ስትኖሩባት፤
2እግዚአብሔር አምላካችሁ ከሚሰጣችሁ ምድር ከሁሉም የመጀመሪያ ፍሬ ውሰዱት። ከዚያም በቅርጫት ውስጥ አድርጉትና እግዚአብሔር አምላካችሁ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ሂዱ።
3በዚያን ወቅት ወደ ሚያገለግለው ካህን ሄዳችሁ ፦ እግዚአብሔር ለእኛ ሊሰጠን ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር እንደ ገባሁ ዛሬ እግዚአብሔር አምላካችሁን ለማምስገን እቀባለለሁ በለው።
4ካህኑም ቅርጫቱን ከእጃችሁ ተቀብሎ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ መሠዊያ ፊት ለፊት ያኖረዋል።
5እናንተም በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት እንዲህ ብላችሁ ትናገራላችሁ፦ አባቴ ዘላን ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚያም ተቀመጠ፤ ታላቅ፥ ኃያልና ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ።
6ግብፃውያንም በመጥፎ ሁኔታ እንገላቱን፥ አሠቃዩንም። እንደ ባሪያ ከባድ ሥራ እንድንሠራ አደረጉን።
7ከዚያ በኋላ ወደ አባቶቻችን አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጮኸን፥ እርሱም ጩኸታችንን ሰማ፤ መከራችንን፣ ድካማችንንና የተፈጸመብንን ግፍ ተመለከተ።
8ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔር በብርቱ እጅና በተዘረጋው ክንዱ፥ በታላቅ ድንጋጤና ታምራት በምልክትና በድንቅ ከግብፅ አወጣን፤
9ወደዚህም ስፍራ አመጣን፥ ማርና ወተት የምታፈሰውን ይህችን ምድር ሰጠን።
10እግዚአብሔር ሆይ እነሆ፥ አንተ ከሰጠኸኝ ከምድሪቱ የመጀመሪያ ፍሬ አምጥቻለሁ፤ ቅርጫቱንም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አኑራሃው አምልከው፤
11ለአንተና ለቤትህ ባደረገው መልካም ነገር አንተ፥ ሌዋውያንና መጻተኞች በእግአብሔር በአምላክህ ፊት ደስ ይበላችሁ።
12የአሥራት ዓመት የሆነውን የሦስተኛውን ዓመት ፍሬ አንድ አሥረኛ ለይታችሁ ካወጣችሁ በኃላ በየከተሞቻችሁ ውስጥ በልተው እንዲጠግቡ፥ ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛው፥አባት ለሌለውና ባል ለሞተባቸው ስጡአቸው።
13ከዚያ በኋላ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር እንዲህ በል፦ በሰጠኸኝ ትእዛዝ መሠረት ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን ከቤቴ አምጥቼ ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ባል ለሞተባት ሰጥቻለሁ። ከትእዛዝህ አልወጣሁም፤ አንዱንም አልረሳሁም።
14በሐዘን ላይ ሳለሁ፥ ከተቀደሰው ክፍል ላይ ምንም አልበላሁም ባልነጻሁበትም ጊዜ ከዚህ ላይ ያነሣሁትምና ለሙታን ያቀረብሁት ምንም ነገር የለም። አምላኬን እግዚአብሔርን ታዝዣለሁ፥ ያዘዝኸኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ።
15ከቅዱስ ማደሪያ ሆነህ ከሰማይ ተመልከት፥ ሕዝብህን እስራኤልንና ለአባቶቻችን በማለህላቸው መሠረት፥ ለእኛ የሰጠኸንን ይህችን ማርና ወተት የምታፈሰውን ምድር ባርክ።
16እግዚአብሔር አምላካችሁ ይህን ሥርዓትንና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ዛሬ ያዝዛችኋል፤ እናንተም በፍጹም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትፈጽሙት ዘንድ ተጠንቀቁ።
17እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆነ በመንገዱም እንደምትሄዱ፥ ሥርዓቱን፥ ትእዛዙንና ሕጉን እንደምትጠብቁ እንደምትታዘዙለት በዛሬው ዕለት ተናግራችኋል።
18እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት እንንተ ሕዝቡና ርስቱ መሆናችሁን ትእዛዙንም ሁሉ እንደምትጠብቁ በዛሬው ዕለት ተናግሮአል፤
19ከፈጠራቸው ሕዝቦች ሁሉ በላይ ለማመስገን፥ ለማክበረና ከፍ ለማድረግና በሰጠውም ተስፋ መሠረት ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ቅዱስ ሕዝብ እንደምትሆኑ ማረጋገጫ ሰጥቶአል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።