መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘዳግም 25

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በሰዎች መካከል ጠብ ቢነሣ ወደ ፍርድ አደባባይ ቢሄዱ፥ ዳኞች ተበዳይን ነጻ፥ በዳይን ግን ጥፋተኛ፥ በማድረግ የፍርድ ውሳኔ ይስጡ።
2በደለኛው ሰው መገረፍ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ፥ ዳኛው መሬት ላይ ያጋድመው፥ ለጥፋቱ ተመጣጣኝ የሆነ ግርፋት እርሱ ባለበት ይገረፍ።
3ሆኖም ግርፋቱ ከአርባ የሚበልጥ አይሁን፥ ከዚህ ካለፈ ግን እስራኤላዊ ወንድማችሁ በፊታችሁ የተዋረደ ይሆናል።
4እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰሩ።
5ወንድማማቾች በአንድነት ቢኖሩና፥ ከእነርሱ አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፥የሟቹ ሚስት ከቤተ ሰቡ ውጭ ባል ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ይውሰዳትና ያግባት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት።
6በመጀመሪያ የምትወልደውም ልጅ ስሙ ከእስራኤል ፈጽሞ እንዳይጠፋ በሟች ወንድሙ ስም ይጠራ።
7ሆኖም ግን አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት ለማግባት ባይፈልግ ሴትዮዋ በከተማዋ በር ወዳሉት ሽማግሌዎች ሄዳ የባለቤቴ ወንድም የወንድሙን ስም በእስራኤል ለማስጠራት አልፈለገም፥ የዋርሳነት ግዴታውንም አልፈጸመልኝም ትበላቸው።
8ከዚያም የከተማው ሽማግሌዎች ያን ሰው ጠርተው ያነጋግሩት እርሱም እርሷን ላገባት አልፈልግም ብሎ በሐሳቡ ቢጸና፥
9የወንድሙንም ሚስት በሽማግሌዎች ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፥ የአንድ እግሩን ጫማ በማውለቅ በፊቱ ላይ ትትፋበትና የወንድሙን ቤት ማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ያለው ድርጊት ይፈጸምበታል ትበል።
10የዚያም ሰው የዘር ሐረግ በእስራኤል ዘንድ ጫማው የወለቀበት ቤት ተብሎ ይታወቃል።
11ሁለት ሰዎች ቢደባደቡ፥ የአንደኛው ሚስት ባሏን ከደብዳቢው እጅ ለማስጣል መጥታ እጇን ዘርግታ ብልቱን ብትይዘው
12፥እጇን ቁረጡ አትራሩላት።
13በከረጢታችሁ ውስጥ ከባድና ቀላል የሆኑ ሁለት የተለያዩ ሚዛኖች አይኑሩአችሁ።
14በቤታችሁም ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት የተለያዩ መስፈሪያዎች አይኑሩአችሁ።
15እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም ትክክለኛና የታመነ ሚዛንና መስፈሪያ ይኑራችሁ።
16እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲህ ያሉትን ጽድቅ ያልሆን ነገሮች የሚፈጽመውንና የሚያምታታውን ሁሉ ይጸየፈዋልና።
17ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ አማሌቅ በመንገድ በእናንተ ላይ ያደረጉባችሁን አስታውሱ፤
18ደክማችሁና ዝላችሁ በነበራችሁበት ጊዜ በጉዞ ላይ አግኝቶአሁ ከኋላ ያዘግሙ የነበሩትን ሁሉ ገደሉ፤ እግዚአቤርንም አልፈሩም።
19እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ዙሪያ ካሉት ጠላቶቻችሁ ሁሉ ባሳረፋችሁ ጊዜ ከሰማይ በታች ያለውን የአማሌቅን መታሰቢያ ደምስሱ፤ ከቶ እንዳትረሱ!
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።