መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘዳግም 23

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ብልቱ የተቀጠቀጠ ወይም የተቆረጠ ማናቸውም ሰው ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።
2ዲቃላም ይሁን፥ የዲቃላው ዘር የሆነ ሁሉ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ እንኳን ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።
3አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማናቸውም የእርሱ ዘር፥ እስከ አሥር ትውልድ እንኳ ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።
4ምክንያቱም ከግብፅ ከወጣችሁ በኋላ በጉዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህልና ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም። በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር ይኖር የነበረውን የቢዖርን ልጅ በለዓምም እናንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዙት።
5ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ በብዓምን አልሰማውም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ስለሚወዳችሁ ርግማኑን ወደ በረከት አደረገላችሁ።
6በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ ሰላምን ለእነርሱ አትመኙ።
7ወንድማችሁ ስለ ሆነ ኤዶማዊውን አትጸየፈው፤ መጻተኛ ሆናችሁ በአገሩ ኖራችኋልና ግብፃዊውን አትጥሉት።
8ለእነርሱ የተወለዳቸው የሦስተኛው ትውልድ ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ መግባት ይችላሉ።
9ጠላታችሁን ለመውጋት ወጥታችሁ በሰፈራችሁ ጊዜ ከማናቸውም ርኩሰት ራሳችሁን ጠብቁ።
10ከመካከላችሁ ሌሊት ዘር በማፍሰስ የረከስሰው ቢኖር፥ ከሰፈር ወጥቶ እዚያው ይቆይ።
11እየመሸ ሲመጣ ግን ገላውን ይታጠብ ፀሐይ ስትጠልቅም ወደ ሰፈሩ ይመለስ።
12ለመጸዳጃ የሚሆንህን ቦታ ከሰፈር ውጭ አዘጋጅ። ከትጥቅህም ጋር መቆፍሪያ ያዝ፥
13በምትጸዳዳበት ጊዜ አፈር ቆፍረህ በዐይነ ምድርህ ላይ መልስበት።
14እግዚአብሔር አምላክህ ሊጠብቅህ ጠላቶህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥህ በሰፈር ውስጥ ስለሚዘዋወር በመካከልህ አንዳች ነውር አይቶ ከአንተ እንዳይመለስ፥ ሰፈርህ የተቀደሰ ይሁን።
15አንድ ባሪያ ከአሳዳሪው ኮብልሎ ወደ እናንተ ቢመጣ፥
16ለአሳዳሪው አሳልፋችሁ አትስጡት፥ ደስ በሚያሰኘው ቦታን ራሱ በመረጠው ከተማ በመካከላችሁ ይኑር፤ እናንተም አታስጨንቁት።
17ወንድ ወይም ሴት እስራኤላዊ የቤተ ጣዖት አመንዝራ አይኑራችሁ።
18ለዝሙት አዳሪ ሴት ወይም ለወንድ ዝሙተኛ የተከፈለውን ዋጋ ለማናቸውም ስእለት አድርጋችሁ ለመስጠት ወደ እግዚአብሔር ወደ አምላካችሁ ቤት አታምጡ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ ሁለቱንም ይጸየፋቸዋልና።
19የገንዘብ፥ የእህል ወይም የማንኛውንም ነገር ወለድ ለማግኘት ለወንድማችሁ በወለድ አታበድሩ። ባዕድ ለሆነ ሰው በወለድ ማበደር ትችላላችሁ።
20ነገር ግን ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር እጃችሁ በሚነካው በማናቸውም ነገር እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲባርካችሁ ለእስራኤልዊ ወንድማችሁ በወለድ አታበድሩት።
21ለእግዚአብሔር ለአምልካችሁ ስእለት ከተሳላችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ አጥብቆ ከእናንተ ይሻዋልና፤ ኃጢአት እንዳይሆንባችሁ ለመክፈል አትዘግዩ።
22ሳትሳሉ ብትቀሩ ግን በደለኛ አትሆኑም። በአንደበታችሁ የተናገራችሁትን ሁሉ ለመፈጸም ጠንቃቃ ሁኑ፥
23ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር በገዛ አንደበታችሁ ፈቅዳችሁ ስእለት ተስላችኋልና።
24ወደ ባልንጀራችሁ የወይን ተክል ቦታ በምትገቡበት ጊዜ ያሰኛችሁን ያህል መብላት ትችላላችሁ፤ ነገር ግን አንዳችም በዕቃችሁ አትያዙ።
25ወደ ባልንጀራችሁ እርሻ በምትገቡበት ጊዜ እሸት መቅጠፍ ትችላላችሁ፤ በሰብሉ ላይ ግን ማጭድ አታሳርፉበት።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።