መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘዳግም 22

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእስራኤላዊ ወንድማችሁ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ብታዩ ወደ እርሱ መልሳችሁ አምጡለት እንጂ ዝም ብላችሁ አትለፉት፥
2ወንድማችሁ በአቅራቢያ ባይኖር፥ ወይም የማን መሆኑን የማታውቁ ከሆነ ባለቤቱ ፈልጎ እስኪ መጣ ድረስ ወደ ቤታችሁና ወስዳችሁ ከእናንተ ዘንድ አቆዩት፤ ከዚያም መልሳችሁ ስጡት።
3የእስራኤላዊ ወንድማችሁን አህያ ወይም ልብስ ወይም የጠፋበትን ማናቸውንም ነገር ስታገኙ እንደዚህ አድርጉ፥ በቸልታ አትለፉት።
4የወንድማሁ አህያ ወይም በሬ መንገድ ላይ ወድቆ ብታዩት በእግሩ እንዲቆም ርዳው እንጂ አልፋችሁ አትሂዱ።
5ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፤ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ፤ እንዲህ የሚያደርገውን ሁሉ እግዚአብሔር አምላካችሁ ይጸየፈዋልና።
6በመንገድ ስታልፉ አንዲት ወፍ ጫጩቶቿን ወይም ዕንቁላሎቿን የታቀፈችበትን ጎጆ በዛፍ ወይም በመሬት ላይ ብታገኙም እናቲቱን ከነጫጩቶቿ አትውሰፉ፤
7ጫጩቶቿን መውሰድ ትችላላችሁ እናቲቱን ግን መልካም እንዲህንላችሁና ዕድሜአችሁም እንዲርዝም ልቀቁት፤
8አዲስ ቤት በምትሠሩበት ጊዜ፥ ከጣራው ላይ ሰው ወድቆ ቤታችሁ ላይ የደም በደል እንዳታመጡ፥ በጣራው ዙሪያ መከታ አብጁለት።
9በወይን ተክል ቦታችሁ ውስጥ ሁለት ዓይነት ዘር አትዝሩ ይህን ካደረጋችሁም የዘራችሁት ሰብል ብቻ ሳይሆን የወይን ፍሬአችሁ ይጠፋል።
10በሬና አህያ በአንድ ላይ ጠምዳችሁ አትረሱ።
11ሱፍና ሐር አንድ ላይ ተፈትሎ የተሠራ ልብስ አትልበሱ።
12በምትለብሱት ልብስ ላይ በአራቱ ማእዘኖች ዘርፍ አድርጉ።
13አንድ ወንድ ሚስት አግብቶ አብሮአት ከተኛ በኋላ ቢጠላት፥
14ስሟንም በማጥፋት፥ ይህችን ሴት አገባኋት፥ዳሩ ግን በደረስሁባት ጊዜ ድንግልናዋን አላገኘሁም ቢል፥
15የልጂቱ አባትና እናት ድንግልናዋን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘው በከተማዪቱ በር ወዳሉት አለቆች ይምጡ።
16የልጂቱም አባት ለአለቆቹ እንዲህ ይበል፥ ልጄን ለዚህ ሰው ዳርሁለት፥ እርሱ ግን ጠላት፤
17ስሟንም በማጥፋት ልጅህን ከነድንግልናዋ አላገኘኋትም ብሎኛል፤ ነገር ግን የልጄ ድንግልና ማረጋገጫ ይኸውላችሁ። ከዚያም ወላጆቿ የደሙን ሸማ በከተማዪቱ አለቆች ፊት ይዘርጉት።
18ከዚያም በኋላ አለቆቹ ሰውየውን ይዘው ይቅጡት፥
19ይህ ሰው የአንዲት እስራኤላዊት ድንግል ስም አጥፍቶአልና አንድ መቶ ሰቅል ብር ያስከፍሉት፥ ገንዘቡንም ለልጂቱ አባት ይስጡት፥ ሴቲቱም ሚስቱ ሆና ትኖራለች፤ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም።
20ሆኖም ክሱ እውነት ሆኖ ሴቲቱ ድንግል ለመሆኗ ምንም ማረጋገጫ ማቅረብ ካልተቻለ፥
21በአባቷ ቤት ሳለች በማመንዘር በእስራኤል ውስጥ አሳፋሪ ተግባር ፈጽማለችና ወደ አባቷ ቤት ደጃፍ ያምጣት፥ እዚያም የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሯት።
22አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ፥ አብሮአት የተኛው ሰውና ሴቲቱ ሁለቱም ይገደሉ። ክፉውን ከእስራኤል ማስወገድ አለባችሁ።
23አንድ ሰው የታጨች ድንግል በከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእርሷ ጋር ቢተኛ፥ ልጃገረዲቱ በከተማ ውስጥ እያለች አስጥሉኝ ብላ ስላልጮኸች፥ ሰውየውም የሌላን ሰው ሚስት አስግድዶ ስለ ደፈረ፥
24ሁለቱንም ወደ ከተማ ደጃፍ ወስዳችሁ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሯቸው። ክፉውን ከመካከላችሁ ማስወገድ አለባችሁ።
25ነገር ግን አንድ ሰው የታጨችውን ልጃገረድ ከከተማ ውጭ አግኝቶ በማስገደድ ቢደፍራት፥ ይህን ድርጊት የፈጸመው ሰው ብቻ ይገደል።
26በልጃገረዲቱ ላይ ግን ምንም አታድርጉባት፥ ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት ምንም አልሠራችም፥ ይህ ዓይነቱ ጉዳይ አደጋ ጥሎ ባልንጀራውን ከሚገድል ሰው አድራጎት ጋር የሚመሳሰል ነው።
27ምክንያቱም ሰውየው የታጨችውን ልጃገረድ ከተማ ውጭ ስላገኛትና ብትጮኽም እንኳ ለርዳታ የደረሰላት ምንም ሰው ስላልነበር ነው።
28አንድ ሰው ያልታጨች ልጃገረድ አግኝቶ በማስገደድ ቢደርስባትና ቢጋለጡ
29ሰውየው ለልጅቷ አባት አምሳ ስቅል ብር ይክፈል፥ ልጃገረዲቱን አስገድዶ ደፍሮአታልና እርሷን ማግባት አለበት፥ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም።
30አንድ ሰው አባቱን ሚስት ማግባት የለበትም፥ የአባቱንም መኝታ አያርክስ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።