መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘዳግም 20

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ጠላቶቻችሁን ለመውጋት ወደ ጦርነት ስትሄዱ ሠርገሎችንና ፈረሶችን ከእናንተ የሚበልጥ ሰራዊትንም በምታዩበት ጊዜ፥ አትፍሩአቸው፥ ከግብፅ ያወጣችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከእናንተ ጋር ነውና።
2ወደ ውጊያው ቦታ ስትቃረቡ፥
3ካህኑ ወደ ፊት ወጣ ብሎ ለሠራዊቱ ይናገር፥ እንዲህም ይበል እስራኤል ሆይ ስማ በዛሬው ቀን ጠላቶቻችሁን ለመግጠም ወደ ጦርነት ልትገቡ ነው። ልባችሁ አይባባ፤ አትፍሩ፤ አትደግጡ፤ በጠላቶቻችሁ ፊት አትሸበሩ።
4ድልን ያቀዳጃችሁ ዘንድ ስለ እናንተ ጠላቶቻችሁን ሊወጋ አብሮአችሁ የሚወጣው አምላካችሁ እግዚአብሔር ነውና።
5አለቆቹም ለሠራዊት እንዲህ ይበሉ፥ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ አለን? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ፥ ያለበለዚያ በጦርነቱ ላይ ሲሞት፥ ቤቱን የሚያስመርቀው ሌላ ሰው ይሆናል።
6ወይን ተክሎ ገና ያልበላለት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፣ ያለበለዚያ በጦርነቱ ሲሞት፥ ሌላ ሰው ይበለዋል።
7ሚስት አጭቶ ያላገባት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፥ ያለበለዚይ በጦርነቱ ሲሞት ሌላ ሰው ያገባታል።
8በዚያም አለቆቹ፦ የሚፈራ ወይም ልቡ የሚባባ ሰው አለን? የወንድሞችም ልብ እንዳይባባ፥ ወደ ቤቱ ይመለስ፤ በማለት ጨምረው ይናገሩ።
9አለቆቹ ለሰራዊቱ ተናግረው ሲያበቁ አዛዦችን በሰራዊቱ ላይ ይሹሙ።
10አንድን ከተማ ለመውጋት በምትዘምቱበት ጊዜ አስቀድማችሁ ለሕዝቧ የሰላም ጥሪ አስተላልፉ፥
11ከተቀበሉአችሁና ደጃቸውን ከከፊቱላችሁ በከተማዋ ውስጥ ሕዝብ ሁሉ የጉልበት ሥራ ይሥሩ፥ ያገልግላችሁም።
12ዕርቀ ሰላምን ባለመቀበል ውጊያ ከመረጡ፥ ከተማዪቱን ክበቡአት።
13እግዚአብሔር አምላካችሁ አሳልፎ በእጃችሁ በሰጣችሁ ጊዜ በውስጧ ያሉትን ወዶች በሙሉ በሰይፍ ግደሉአቸው።
14ነገር ግን ሴቶቹን ሕፃናትን እንስሳትንና በከተምዩቱ ውስጥ የሚገኘውን ማናቸውንም ነገር በምርኮ ለራሳችሁ አድርጉ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከጠላቶቻችሁ የሚሰጣችሁን ምርኮ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።
15እንግዲህ የአካባቢያችሁ አሕዛብ ከተሞች ባልሆኑትና ከእናንተ እጅግ ርቀው በሚገኙት ከተሞች ሁሉ ላይ የምታደርጉት ይኸው ነው።
16እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ በአሕዛብ ከተሞች ውስጥ እስትንፋስ ያለውን ነገር አታስተርፉ።
17በዚህ ፈንታ፥ ኬጢያዊውን፥ አሞራዊውን፥ ከነዓናዊውን፥ ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውን፥ ኢያቡሳዊውን እግዚአብሔር አምላካችሁ ባዘዛችሁ መሠረት ፈጽማችሁ ደምስሱአቸው።
18አለበለዚያ አማልክታቸውን በሚያመልኩበት ጊዜ የሚፈጽሟቸውን አስጻያፊ ተግባራት ሁሉ ታደርግ ዘንድ ያስተምሩአችኋል፤ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ላይ ኃጢአት ትሠራላችሁ።
19አንድን ከተማ ተዋገታችሁ ለመያዝ የረጅም ጊዜ ከበባ በምታድርጉበት ጊዜ፥ ዛፎቹን በመጥረቢያ ጨፍጭፋችሁ ማጥፋት የለባችሁም። የዛፎችን ፍሬ መብላት ስለምትችሉ አትቁረጡአቸው። ከባችሁ የምታጠፉአችሁ የሜዳ ዛፎች ሰዎች ናቸውን?
20የሚበላ ፍሬ እንደማያፈራ የምታውቁትን ዛፍ ግን ልትቆርጡና ጦርነት የምታካሄዱባትን ከተማ በድል እስክትቆጣጠሩአት ድረስ ለከበባው ምሽግ መሥሪያ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።