1በየሰባት ዓመት የዕዳ ምሕረት ታደጋላችሁ።
2ይህ ዕዳ ምሕረት አፈጻጸም እንከሚከተለው ነው፤ አበዳሪ ሁሉ ለባልንጀራው ላበደረው እንዲተውዋውና ከባልጀራው ወይም ወንድሙ መልሶ እንዳይጠይቅ እግዚአብሔር ያወጀው ይህ ነው።
3ለእንግዳ ያበደራችሁትን መጠየቅ የምትችሉ ሲሆን፥ ለእስራኤላዊ ወንድማችሁ ያበደራችሁትን ግን ምሕረት አድርጉለት።
4ይሁን እንጂ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ትወርሱአት ዘንድ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ውስጥ አብዝቶ ስለሚባርካችሁ በመካከላችሁድኻ አይኖርም።
5ይህ የሚሆነው የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ድምፅ ፈጽማችሁ ስትሰሙና ዛሬ የማዛችሁን ትእዛዘትን ሁሉ ስትታዘዙ ብቻ ነው።
6እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ተሰፋ መሠረት ስለሚባርካችሁ እናንተ ለብዙ አሕዛብ ታበድራላችሁ እንጂ እናንተ አትበደሩም፤ብዙ አሕዛብን ትገዛላችሁ እንጂ ማንም እናንተን አይገዛችሁም።
7እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ምድር ላይ ደኻ ቢኖር፥ በደኻ ወንድማችሁ ላይ ልባችሁ አይጨክን፥ለደኻ ወንድማችሁ ላይም እጃችሁን ከመዘርጋት አትቆጥቡ፤
8ነገር ግን እጃችሁን በትክክል ፍቱለት ለማያስፈልገውም ቅር ሳትሉ አበድሩት።
9ዕዳ የሚሠርዝበት ሰባተኛ ዓመት ቀርቦአል፥ በማለት ክፉ አሳብ አድሮባችሁ በችግረኛ ወንድማችሁ ላይ እንዳትጨክኑና ምንም ሳትሰጡት እንዳይቀር እርሱ በእናንተ ላይ ወደ እግዚአብሔር ጮኾ በደለኞች እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ።
10በቅን ልቦና ስጡት፥ ስትሰጡትም ልባችሁ አይጸጸት፥ከዚያም የተነሣ ግዚአብሔር አምላካችሁ ሥራችሁንና እጃችሁን ያረፈበትን ሁሉ ይባርክላችኋል።
11በምድሪቱ ላይ ሁልጊዜ ድኾች አይጠፉም፥ስለዚህ በዚያ ለሚኖሩ ወንድሞቻችሁ ለድኾችና ለችግራኞች እጃችሁን እንድትዘረጉ አዛችኋለሁ።
12እናንተም ወንድማችሁን ዕብራዊውን ወይም ዕብራዊቱን ብትገዙ ስድስት ዓመት ያገልግላችሁ በሰባተኛውም ዓመት ከእናንተ ዘንድ አርነት አውጡት።
13ከእናንተም ዘንድ አርነት በሚታወጣበት ጊዜ ባዶውን አትስደዱት።
14ነገር ግን ከመንጋህ፥ ከአውድማችሁም፥ ከወይራችሁም መጥመቂያም ትለግሱታላችሁ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ መጠን ትሰጡት ዘንድ ይገባል።
15እናንተም በግብፅ አገር ባሮች እንደ ነበራችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁም እንደ ነበራችሁ አስቡ፤ስለዚህ እኔ ዛሬ ይህን እንድታደርጉ አዛችሁኋለሁ።
16ነገር ግን አገልጋያችሁ እናንተንና ቤተ ሰቦቻችሁን በመውደዱና ከእናንተ ጋር ደስተኛ ሆኖ ከመኖሩ የተነሣ፦ ከእናንተ መለየት አልፈልግም ቢላችሁ፦
17ጆሮውን ከቤታችሁ መዝጊያ ላይ በማስደግፍ በወስፌ ትበሳላችሁ፤ከዚያም ዕድሜ ልኩን አገልጋያችሁ ይሆናል። በቤት አገልጋዮችሁም ላይ እንዲሁ አድርግ።
18አገልጋያችሁን አርነት ማውጣት ከባድ መስሎ አይታያችሁ፤ ምክንያቱም የስድስት ዓመት አገልግሎቱ አንድ የቅጥር ሠራተኛ ከሚሰጠው አገልግሎት እጥፍ ነውና። እግዚአብሔር አምላካችሁ በምታደጉት ነገር ሁሉ ይባርካችኋልና።
19የቀንድ ከብት፥ የበግና የፍየል መንጋዎቻችሁን ተባዕት በኩር ሁሉ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ቀድሱ። የበሬአችሁን በኩር አትሥሩባቸው፥ የበጋችሁንም በኩር አትሸልቱ፥
20እርሱ በሚመርጠው ስፍራ እናንተና ቤተ ሰባችሁ በየዓመቱ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ትበሉታላችሁ።
21አንድ እንስሳ እንከን ካለበት፤ አንካሳ ወይም ዕውር ወይም ደግሞ ማናቸውም ዓይነት ከባድ ጉድለት ያለበት ከሆነ፤ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር አትሠዉ።
22የከተሞቻችሁ ትበላላችሁ፤ በሥርዓቱ መሠረት ንጹሕ የሆነውም ሆነ ያልሆነው ሰው፥ እንደ ድኩላ እንደ ዋላ ያሉትን ይበላዋል።
23ደሙን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሱት እንጂ አትብሉት።