መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘዳግም 14

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እናንተ የእግዚአብሔር የአምላካችሁ ሕዝብ ናችሁ። ስለ ሞተው ሰው አካላችሁን አታቆስሉ፥ የትኛውንም የፊታችሁን ክፍል አትላጩ።
2ምክንያቱም እናንተ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ፤ በምድርም ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለራሱ ሕዝብ ትሆኑ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር እናንተን መርጦአልና።
3ርኩስን ነገር ሁሉ አትብሉ።
4የምትበሉአቸው እንስሶች እነዚህ ናቸው፦ በሬ፥ በግ፥ ፍየል፥
5ዋላ፥ ሚዳቋ፥ የበረሃ አጋዘን፥ አጭ፥ በራይሌ፥ የተራራ በግ (ድኩላ)።
6ከእንስሶች ሰኮናው የተሰነጠቀውን ጥፍሩም ከሁለት የተከፈለውን የሚያመነዥከውንም እንስሳ ሁሉ ትበላላችሁ።
7ነገር ግን ከማያመሰኩ ወይም ሰኮናቸው ካልተሰነጠቀ፥ እነዚህን አትበሉም፤ ግመል፥ ጥንቸል፥ ሽኮኮን፥ አትበሉም። የሚያመነዥኩና ነገር ግን ሰኮናቸው ያልተሰነጠቀም እነዚህ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው።
8እርያም ሰኮናው ስለ ተሰነጠቀ ነገር ግን ስለማያመነዥክ፥ እርሱ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ ሥጋውን አትብሉ በድኑንም አትንኩ።
9በውኃ ውስጥ ከሚኖሩት ሁሉ የምትበሉአቸው እነዚህ ናቸው፤ ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ትበላላችሁ።
10ነገር ግን ክንፍና ቅርፊትም የሌላቸውን አትበሉም፥ ለእናንተ ርኩስ ናቸው።
11ንጹሕ የሆኑትን ወፎችን ሁሉ ትበላላችሁ።
12ነገር ግን ከወፎች ሊበሉ የማይገባቸው እነዚህ ናቸው። ንስር፥ ገዴ፥ ዓሣ አውጭ፥
13ጭልፊት፥ ጭላት፥ በየወገኑ፥
14ቁራም ሁሉ በየወገኑ፥
15ሰጎን፥ ጠላቋ፥ ዝዪ፥ በቃል፥ በየወገኑ፥
16ጉጉት፥ ጋጋኖ፥
17የውኃ ዶሮ ይብራ፥
18ጥምብ አንሣ፥ አሞራ፥ እርኩም ሽመላ ሳቢሳ፥ በየወገኑ፥ ጅንጅላቴ ወፍ፥ የሌሊት ወፍ፥።
19የሚበርርም ተንቀሳቃሽ ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ አይበሉም።
20ንጹሕ የሆኑትን ወፎች ሁሉ ብሉ።
21የበከተውን ሁሉ አትብሉ፥ ይበላው ዘንድ በአገራችሁ ደጅ ለተቀመጠ፥ መጻተኛ ትሰጠዋላችሁ፥ ወይም ለእንግዳ ትሸጣላችሁ። ምክንያቱም እናንተ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የተቀደሰ ሕዝብ ናችሁ። የፍየሉን፥ ጠቦት፥ በእናቱ ወተት አትቀቅሉ።
22ከእርሻችሁ በየዓመቱ ከምታገኙት ከዘራችሁ ፍሬ ሁሉ አሥራት ታወጣላችሁ።
23ሁልጊዜ እግዚአብሔር አምላካችሁን መፍራት ትማሩ ዘንድ ስሙ፤ እንዲጠራበት በመረጠው ስፍራ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት የእህላችሁን የወይን ጠጃችሁንም የዘይታችሁንም አሥራት የላማችሁንና የበጋችሁንም በኩራት ብሉ።
24እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ ጊዜ መንገዱ ሩቅ ቢሆን፥ እግዚአብሔር አምላካችሁም ስሙን ያኖርበት ዘንድ የመረጠው ስፍራ ቢርቅባችሁ ግን ወደዚያ ለመሸከም ባትችሉ ትሸጣላችሁ፥
25የዋጋውንም ገንዘቡ በእጃችሁ ይዛችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደ መረጠው ስፍራ ትሄዳላችሁ።
26በዚያም በገንዘቡ የፈለጋችሁትን በሬ ወይም፥ በግ ወይም፥ የወይን ጠጅ፥ ወይም ብርቱ መጠጥ፥ ወይም የፈለጋችሁትን ሁሉ ትገዛላችሁ፤ በዚያም በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ትበላላችሁ፥ እናንተና ቤተ ሰባችሁም ደስ ይላችኋል።
27ድርሻና ርስት ከእናንተ ጋር ስለሌለው በአገራችሁ ደጅ ውስጥ ያለውን ሌዋዊውን ቸል አትበሉ።
28በየሦስተኛው ዓመት መጨረሻ በዚያ ዓመት ሌዋዊው ከእናንተ ጋር ክፍልና ርስት ስለሌለ የፍሬአችሁን አሥራት ሁሉ አምጥታችሁ በአገራችሁ ደጅ ታኖራላችሁ፤
29በአገራችሁም ደጅ ያለ መጻተኛ፥ ድሀ አደግ፥ ባል የሞተባት መጥተው ይበላሉ፤ ይጠግባሉም። ይኸውም እግዚአብሔር አምላካችሁ በምታደርጉት በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ይባርካችሁ ዘንድ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።