መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘዳግም 12

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር እንድትወርሱ በሚሰጣችሁ ምድር፥ ሁልጊዜ በምድር እያላችሁ የምትጠብቁአችሁ ሥርዓትና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው።
2እናንተ የምትወርሱአቸው አሕዛብ አማልክታቸውን ያመለኩባቸውን በረጅም ተራሮች በኮረብቶችም ከለምለምም ዛፍ በታች ያለውን ስፍራ ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉአቸው።
3መሠዊያቸውንም አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥የማልመኪያ ዐፀዶቻችቸውንም በእሳት አቃጥሉ፥የአማልክታቸውንም የተቀረጹ ምስሎች ቆራርጡአቸው፥ ከዚያም ስፍራ ስማቸውን አጥፉ።
4እግዚአብሔር አምላካችሁን እንዲህ ባለ ሁኔታ አታምልኩ።
5ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ከነገዶቻችሁ ሁሉ ስሙን በዚያ ያኖር ዘንድ ወደዚያ ወደ መረጠው ስፍራ ትመጣላችሁ፥ ማደሪያውንም ትሻላችሁ።
6ወደዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ሌላም መሥዋዕታችሁንም፥ አሥራታችሁንም፥ በእጃችሁም ያነሣችሁትን ቁርባን፥ ስእለታችሁንም በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትን፥ የላማችሁንና የበጋችሁንም በኩራት ውሰዱ።
7በዚያም በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ብሉ፥ እጃችሁንም በምትዘረጉበት እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ ነገር ሁሉ እናንተና ቤተ ሰባችሁ ደስ ይበላችሁ።
8ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን፥ እኛ በዚህ ዛሬ የምናደርገውን ሁሉ አታደርጉም፥
9እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚሰጣችሁ ዕረፍትና ርስት እስከ ዛሬ ድረስ አልገባችሁምና።
10ነገር ግን ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችሁም በሚያወርሳችሁ ምድር በተቀመጣችሁ ጊዜ ያለ ፍርሃትም እንድትኖሩ፥ ከከበቡአችሁ ጠላቶች ሁሉ ዕረፍት በሰጣችሁ ጊዜ በዚያ ጊዜ
11እግዚአብሔር አምላካችሁ ፥ ስሙ ይጠራበት ዘንድ ወደዚያ ወደ መረጠው ስፍራ እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ሌላም መሥዋዕታችሁን አሥራታችሁንም፥ በእጃችሁ ያነሣችሁትንም ቁርባን፥ ለእግዚአብሔርም ተስላችሁ የመረጣችሁትን ስእልታችሁን ሁሉ ውሰዱ።
12እናንተም፥ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁ፥ አገልጋዮቻችሁና የቤት አገልጋዮቻችሁ፥ ከእናንተ ጋር ክፍልና ርስት ስለሌለው በደጆቻችሁ የተቀመጠው ሌዋዊም፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።
13የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን በሚታያችሁ ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርቡ ተጠንቀቁ።
14ነገር ግን እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ከአንዱ ዘንድ በመረጠው ስፍራ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አቅርቡ፥ በዚያም የማዝዛችሁን ሁሉ አድርጉ።
15ይሁን እንጂ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሰጣችሁ በረከት ሰውነታችሁ እንደ ፈቀደ በደጆቻችሁ ሁሉ ውስጥ አርዳችሁ ብሉ፤ንጹሕም ያልሆነ ሰው እንደ ሚቋና እንደ ዋላ ያለውን ይብላው።
16ደሙን ግን እንደ ውኃ በምድር ላይ ያፍስሰው፤ ደሙን አትብሉ።
17የእህላችሁን፥ የወይናችሁን፥ የጠጃችሁን የዘይታችሁንም፥ አሥራት፥ የላማችሁንና የበጋችሁንም በኩራት የተሳላችሁትንም ስእለት ሁሉ በፈቃዳችሁም ያቀረባችሁትን፥ በእጃችሁም ያነሣችሁትን ቁርባን በደጆቻችሁ መብላት አትችሉም።
18በዚህ ፈንታ እናንተ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም አገልጋዮቻችሁና የቤት አገልጋዮቻችሁ፥በአገራችሁ ደጅ ያለው ሌዋዊ እግዚአብሔር አምላካችሁ በመረጠው ስፍራ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ብሉት፥ እጃችሁንም በምትዘረጉባችሁ ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ደስ ይበላችሁ።
19በምድራችሁ ላይ በምትኖሩባት ዘመን ሁሉ ሌዋዊውን ቸል እንዳትሉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
20እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ነገራችሁ አገራችሁን ባሰፋ ጊዜ፥ ሰውነታችሁም ሥጋ መብላት ስለ ወደደ፦ ሥጋ እንብላ፥ ስትሉ እንደ ሰውነታችሁ ፈቃድ ሥጋን ብሉ።
21እግዚአብሔር አምላካችሁ በዚያ ስሙን ያኖር ዘንድ የመረጠው ስፍራ ከእናንተ ሩቅ ቢሆንም እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከላምና ከበግ መንጋችሁ እንዳዛዝኋችሁ እረዱ፥ እንደ ሰውነታችሁም ፈቃድ ሁሉ በአገራችሁ ደጅ ብሉ።
22ሚዳቋና ዋላ እንደሚበሉ እንዲሁ ብሉ፥ ንጹሕ ሰው ንጹሕ ያልሆነም ይብለው።
23ደሙ ሕይወት ነውና፥ ነፍሱንም ከሥጋው ጋር መብላት አይገባችሁምና፥ ደሙን እንዳትበሉ ተጠንቀቁ።
24በምድር ላይ እንደ ውኃ አፍስሱት እንጂ አትብሉ።
25በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር ስታደርጉ ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም እንዲሆንላችሁ አትብሉ።
26ነገር ግን የተቀደሰውን ነገራችሁን ስእለታችሁንም ይዛችሁ እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ሂዱ።
27የሚቃጠለውንም መሥዋዕታችሁን ሥጋውንና ደሙን በአምላካችሁ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርቡ፤ የመሥዋዕታችሁም ደም በእግዚአብሔር በአምላካችሁ መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፥ ሥጋውንም ብሉ።
28በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት መልካምና ቅን የሆነውን ነገር ስታደርጉ ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ ለዘላለም መልካም ይሆንላችሁ ዘንድ እኔ የማዝዛችሁን እነዚህን ቃሎች ሁሉ ሰምታችሁ ጠብቁ።
29እግዚአብሔር አምላካችሁ ትወርሱአቸው ዘንድ የምትሄዱባቸውን አሕዛብን ፊታችሁ ባጠፋ ጊዜ፥ እናንተም በወረሳችሁ ጊዜ፥ በምድራቸውም በተቀመጣችሁ ጊዜ፥
30ከፊታችሁ ከጠፉ በኋላ እነርሱን ለመከተል እንዳትጠመዱ፦ እነዚህ አሕዛብ አማልክታቸውን የሚያመልኩት እንዴት ነው? እንዲሁ ደግሞ እኔም አደርጋለሁ ብላችሁ ስለ አማልክታቸው እንዳትጠይቁ ተጠንቀቁ።
31እግዚአብሔር የሚጠላውን ርኩሰት ሁሉ እነዚህን ለአማልክታቸው አድርገዋል፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ለአማልክታቸው በእሳት አቃጥሎአቸዋል፥ እናንተም ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ እንዲሁ አታድርጉ።
32እኔ የማዝዛችሁን ነገር ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ፤ ምንም በእርሱ ላይ አትጨምሩ ከእርሱም ምንም አታጉድሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።