1ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁን ውዳዱት፥ ሁልጊዜም መመሪያዎቹን፥ ሥርዓቶቹን፥ ድንጋጌዎችንና ትእዛዛትን ጠብቁ።
2የእግዚአብሔርን የአምላካችሁን ቅጣት፥ታላቅነቱን፥ ኃያልነቱን፥ የተዘረጋውንም ክንዱን፥ ላላወቁት ወይም ላላዩት ልጆቻችሁ እየተናገርሁ እንዳልሆነ አስታውሉ፤
3በግብፅም መካከል በንጉሡ በፈርዖንና በአገሩ ሁሉ ላይ ያደረጋውን ተአምራቱንና ሥራውን፥
4በተከተሉአችሁም ጊዜ በግብፅ ጭፍራ፥ በፈረሶቻቸውና በሰረገሎቻቸው ያደረገውን፥በኤርትራ ባሕር ውኃ እንዳሰጠማቸው፥ እግዚአብሔርም እስከ ዛሬ ድረስ እንዳጠፋቸው፥
5ወደዚህ ስፍራ እስከትመጡ ድረስ በምድረ በዳ ያደረገላችሁን፥አይተዋል።
6በእስራኤልም ሁሉ መካከል ምድር አፍዋን ከፍታ እነርሱንና ቤተ ሰቦቻቸውን ድንኳኖቻቸውንም ለእነርሱም የነበራቸውን ሁሉ በዋጠቻቸው በሮቤል ልጅ፥ በኤልያብ ልጆች፥ በዳታንና በአቤሮን እግዚአብሔር ያደረገውን አላዩም።
7ነገር ግን እግዚአብሔር ያደረገውን ታላቁ ሥራ ሁሉ ዓይኖቻቸው አይተዋል።
8እንግዲህ እንድትጠነክሩ ትወርሱአትም ዘንድ ወደምትሄዱባት ምድር እንድትሄዱ ዛሬ ለእናንተ የማዘዘውን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤
9እግዚአብሔርም ለአባቶቻችሁና ለዘራቸው ይሰጣቸው ዘንድ በማለላቸው ወተትና ማርም በምታፈስሰው ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዘም ትእዛዘትን ጠብቁ።
10ትወሱአት ዘንድ የምትሄዱባት ምድር በመጣችሁበት በግብፅ አገር ዘር እንደዘራችሁና ውኃ በእግራችሁ ታጠጡ እንደነበረ፥ እንደ አትክልት ቦታ አይደለችም፤
11ነገር ግን ትወርሱአት ዘንድ ተሻግራችሁ የምትገቡባት ምድር ኮረብታና ሸለቆ ያለባት በሰማይ ዝናብ ውኃ የምትጠጣ አገር ናት፤
12አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚንከባከባት፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ የእግዚአብሔር የአምላካችሁ ዓይን ሁልጊዜ በእርስዋ ላይ የሆነ አገር ናት።
13እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ እግዚአብሔር አምላካችሁን ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁ፥ ትወድዱና ታገለግሉት ዘንድ ዛሬ የማዝዛችሁን ትእዛዘትን ፈጽማችሁ ብትሰሙ፥
14እህላችሁን፥ ወይናችሁን፥ ዘይታችሁን ትሰበስቡ ዘንድ በየዚዜው ለምድራችሁ የመጀመሪያውንና የኋለኛውን የወቅቱን ዝናብ ይሰጣችኋል።
15በሜዳ ለእንስሶቻችሁም ሣርን እሰጣለሁ፤ትበላላችሁ፣ ትጠግባላችሁም።
16ልባችሁ እንዳይስት ፈቀቅ እንዳትሉ ሌሎችንም አማልክት እንዳታመልኩ፥ እንዳትሰግዱላቸውም፥
17የእግዚአብሔርም ቁጣ እንዳይነድድባችሁ ዝናብ እንዳይዘንብ ምድሪቱም ፍሬዋን እንዳትሰጥ ሰማይን እንዳይዘጋባችሁ፤ እግዚአብሔርም ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችሁ እንዳትጠፉ ተጠንቀቁ።
18ስለዚህ እነዚህን ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ፤እነርሱንም ለምልክት በእጃችሁ ላይ እሰሩአቸው፥ በዓይኖቻችሁም መካከል እንደ ክታብ ይሁኑላችሁ። ፥
19በቤታችሁም ስትቀመጡ፥ በመንገድ ላይም ስትሄዱ፥ ስትተኙ፥ ስትነሡም ልጆቻችሁንም አስተምሩአቸው።
20በቤታችሁ መቃኖችና በከተሞቻችሁ በሮች ላይ ጻፈው፥
21እግዚአብሔርም እንዲሰጣቸው ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር፥ እንደ ሰማይ ቀኖች በላይ በምድር ከፍ ያሉና የልጆቻችሁም ዘመን የረዘመ ይሁን ።
22እግዚአብሔር አምላካችሁን ትወድዱ ዘንድ በመንገዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ትጣበቁ ዘንድ፥ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዘት ሁሉ ብትጠብቁ፥ ብታደርጉአቸውም፥
23እግዚአብሔር እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያወጣል፤ ከእናንተም የሚበልጡትን፥ የሚበረቱትንም አሕዛብ ትወርሳላችሁ።
24የእግራችሁ ጫማ የሚረግጥበት ስፍራ ሁሉ ለእናንተ ትሆናለች፤ ከምድረ በዳም ከሊባኖስ ወንዝ፥ ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል።
25በእናንተም ፊት ማንም መቆም አይችልም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር እርሱ እንደ ተናገራችሁ ማስፈራታችሁና ማስደንገጣችሁ በምትረግጡበት ምድር ሁሉ ላይ ያኖራል።
26እነሆ፥ ዛሬ በፊታችሁ በረከትንና መርገምን አኖራለሁ፤
27በረከትም የሚሆነው፥ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ትእዛዝ ብትሰሙ
28እንዲሁም መርገም የሚሆነው የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ትአዛዝ ባትሰሙ፥ ዛሬም ካዘዝኋችሁ መንገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎችንም የማታውቋቸውን አምልክት ብትከተሉ ነው።
29እግዚአብሔር አምላካችሁ ትወሱአት ዘንድ እናንተም ወደምትሄዱባት ምድር ባገባሃችሁ ጊዜ፥ በረከቱን በገሪዛን ተራራ፥ መርገሙንም በጌባል ተራራ ይሆናል።
30እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ከምዕራብ ካለው መንገድ በኋላ በዓረባ በሚኖሩት በከነዓናውያን ምድር በጌልገላ ፊት ለፊት በሞሬ የአድባር ዛፍ አጠገብ አይደለምን?
31እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ፥ ትወርሱአታላችሁ፥ ትቀመጡባታላችሁም።
32እኔም ዛሬ በፊታችሁ የማኖራውን ሥርዓትና ድንጋጌዎች ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ።