መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዳንኤል 9

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የሜዶናዊው የአርጤክስስ ልጅ ዳርዮስ በባቢሎን በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት
2በዘመነ መንግሥቱ በመጀመሪያው ዓመት፣ እኔ ዳንኤል ለነቢዩ ኤርምያስ በተሰጠው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት፣ የኢየሩሳሌም መፈራረስ ሰባ ዓመት እንደሚቆይ ከቅዱሳት መጻሕፍት አስተዋልሁ።
3ስለዚህ ማቅ ለብሼ በራሴም ላይ ዐመድ ነስንሼ በጾምና በጸሎት፣ በምልጃም ፊቴን ውደ ጌታ አምላክ አቀናሁ።
4ወደ እምላኬ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፣ ተናዘዝሁም፤ “ከሚወዱህና ትእዛዝህን ከሚፈጽሙ ሁሉ ጋር የፍቅር ቃል ኪዳንህን የምትጠብቅ፣ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ጌታ ሆይ፤
5እኛ ኃጢአት ሠርተናል፣ በድለናልም፣ ክፋትን አድርገናል፣ ዐምፀናልም፣ ከትእዛዝህና ከሕግህ ዘወር ብለናል።
6ለንጉሦቻችን፣ ለልዑሎቻችንና ለአባቶቻችን እንዲሁም ለምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ በአንተ ስም የተናገሩትን አገልጋዮችህን ነቢያትን አልሰማንም።
7“ጌታ ሆይ፤ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን በአንተ ላይ ስለ ሠራነው ታላቅ ክፋት እኛን በበተንህባቸው አገሮች ሁሉ የምንገኝ የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምና የመላው እስራኤል ሕዝብ፣ በሩቅም ሆነ በቅርብ ያለን በዚህ ቀን ኀፍረት ተከናንበናል።
8እግዚአብሔር ሆይ፤ እኛና ንጉሦቻችን፣ ልዑሎቻችንና አባቶቻችን በአንተ ላይ ኃጢአት ስለ ሠራን ኀፍረት ተከናንበናል።
9ምንም እንኳ በእርሱ ላይ ያመፅን ብንሆን፣ ጌታ አምላካችን ይቅር ባይና መሐሪ ነው።
10እግዚአብሔር አምላካችንን አልታዘዝነውም፤ ደግሞም በአገልጋይቹ በነቢያት በኩል የሰጠንን ሕግ አልጠበቅንም፤
11መላው እስራኤል አንተን ባለመታዘዝ ሕግህን ተላልፎአል፤ ዘወርም ብሎአል።በአንተ ላይ ላይ ኃጢአትን ስለ ሠራን፣ በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴ ሕግ የተጸው መሐላና ርግማን ፈሰሰብን።
12ታላቅ ጥፋት በእኛ ላይ በማምጣት፣ የተነገረውን ቃል ፈጸምህብን፤ በኢየሩሳሌም ላይ የተደረገውን የሚያህል ከሰማይ በታች ከቶ የለም።
13በሙሴም ሕግ እንደ ተጻፈው፤ ይህ ሁሉ ጥፋት በእኛ ላይ ደረሰ፤ ሆኖም ከኃጢአታችን በመመለስና እውነትህን በመከተል ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ምሕረትን አልፈለግንም።
14አምላካችን እግዚአብሔር በሚያደርገው ሁሉ ጻድቅ ነውና፣ በእኛ ላይ እግዚአብሔር ጥፋት ከማምጣት አልተመለሰም፣ እኛም አልታዘዝነውም።
15አሁንም ሕዝብህን ከግብፅ ምድር በብርቱ እጅ ያወጣህ፣ እስከዚህም ቀን ድረስ ስምህ እንዲታወቅ ያደረግህ፤ ጌታ አምላካችን ሆይ፤ ኃጢአት ሠርተና፣ አንተንም በድለናል።
16ጌታ ሆይ እንዳደረግኸው የጽድቅ ሥራህ ሁሉ፣ ከከተማህ ከኢየሩሳሌም፣ ከቅዱሱም ተራራህ ቁጣህን መልስ፣ በእኛ ኃጢአትና በአባቶቻችን በደል ምክንያት ኢየሩሳሌምና ህዝብህ በዙሪያችን ባሉት ዘንድ መሣለቂያ ሆነዋል።
17አሁንም አምላካችን ሆይ፣ የአገልጋይህን ጸሎትና ልመና ስማ። ጌታ ሆይ፤ ስለ ስምህ ስትል ፊትህን ወደፈረሰው መቅደስ መልስ።
18አምላክ ሆይ፤ ጆሮህን አዘንብለህ ስማ፣ ዐይንህን ገልጠህ መጥፋታችንንና ስምህ የተጠራበትን ከተማ ተመልከት። ልመናችንን የምናቀርበው ስለ ጽድቃችን ሳይሆን፣ ስለ ታላቅ ምሕረትህ ነው።
19ጌታ ሆይ፣ አድምጥ! ጌታ ሆይ፤ ይቅር በል! ጌታ ሆይ፤ ስማ! አድርግም፤ ስምህ በከተማንህና በሕዝብህ ላይ ተጠርቶአልና አምላኬ ሆይ፣ ስለ ስምህ ስትል አትዘግይ።”
20እኔም እየተናገርሁና እየጸለይሁ፣ የራሴንና የሕዝቤን የእስራኤልን ኃጢአት እየተናዘዝሁ፣ ስለ ቅዱስ ተራራውም እግዚአብሔር አምላኬን እየለመንህ
21እየጸለይሁም ሳለሁ፣ በመጀመሪያው ራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል፣ በሠርክ መሥዋዕት ጊዜ በፍጥነት እየበረረ ወደ እኔ መጣ።
22እርሱም እንዲህ ብሎ አስረዳኝ፤ “ዳንኤል ሆይ፣ አሁን ጥበብንና ማስተዋልን ልሰጥህ መጥቻለሁ
23አንተ እጅግ የተወደድህ ስለሆንህ፣ ገና መጸለይ ስትጀምር መልስ ተሰጥቶአል፣ አኔም ይህን ልነግርህ መጣሁ። ስለዚህ መልእክቱን ልብ በል፤ ራእዩንም አስተውል።
24ዐመፃን ለማስቆም፣ ኃጢአትን ለማስወገድ፣ በደልን ለማስተሰረይ፣ ዘላለማዊ ጽድቅን ለማምጣት፣ ራእይንና ትንቢትን ለማተምና እጅግ ቅዱስ የሆነውን ለመቀባት ስለ ሕዝብህና ስለ ተቀደሰችው ከተማህ ሰባ ሱባዔ ታውጇል።
25ይህንን ዕወቅ አስተውለውም፤ ኢየሩሳሌምን ለማደስና ለመጠገን ዐዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ገዢው መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስልሳ ሁለት ሱባዔ ይህናል። ኢየሩሳሌም ከጎዳናዎቿና ከቅጥሮቿ ጋር ትታደሳለች፤ ይህ የሚሆነው ግን በመከራ ጊዜ ነው።
26ከሥልሳ ሁለት ሱባዔ በኋላ መሲሑ ይገደላል፤ ምንም አይቀረውም። የሚመጣው አለቃ ሰዎችም ኢየሩሳሌምንና ቤተ መቅደሱን ይመደስሳል። ፍጻሜውም እንደ ጎርፍ ይመጣል፤ ጦርነት እስከ መጨረሻው ይቀጥላል፤ ጥፋትም ታውጇል።
27አለቃው ከብዙዎች ጋር ለአንድ ሱባዔ ቃል ኪዳኑን ያጸናል፤ በሱባዔውም እኩሌታ መሥዋዕትና ቁርባን ማቅረብን ያስቀራል። በርኵሰቱ ጫፍ ላይ ጥፋቱን የሚፈጽመው ይገለጣል። የታወጀው ፍርድ ጥፋትን በሚያመጣው ላይ የሚፈስ ይሆናል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።