1የባቢሎን ንጉሥ ቤልሻዘር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ዳንኤል በአልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ ሕልም አለመ፤ ራእይም አየ፤ የሕልሙንም ዋና ሃሳብ ጻፈው።
2ዳንኤል እንዲህ አለ፤ “ኣቱ የሰማይ ነፋሳት ታላቁን ባሕር ሲያናውጡት ሌሊት በራእይ አየሁ፤
3እርስ በርሳቸው የማይመሳሰሉ አራት ታላላቅ አራዊት ከባሕሩ ወጡ።
4የመጀመሪያው አንበሳ ይመስል ነበር፤ የንስርም ክንፎች ነበሩት፤ ክንፎቹ እስኪነቃቀሉ ድረስ ትመለከትሁ፤ እንደ ሰው በሁለት እግር እንዲቆም ከመድር ከፍ ከፍ ተደረገ፤ ሰብዓዊ አእምሮ ተሰጠው።
5እነሆም ሁለተኛው አውሬ ድብ ይመስል ነበር፤ በአንድ ጎኑ ከፍ ብሎአል፤ በአፉ ውስጥ በጥርሶቹ መካከል ሦስት የጎድን አጥንቶች ነበርት። እርሱም፤ “ተነሥ እስክትጠግብ ድረስ ሥጋ ብላ” ተባለ።
6ከዚህ በኋላ ተመለክትሁ፤ በፊቱ በኩል ነብር የሚመስል ሌላ አውሬ ነበር፤ በጀርባውም በኩል የወፍ ክንፍ የሚመስሉ አራት ክንፎች ነበርት፤ ይህ አውሬ አራት ራስ ነበረው፤ ለመግዛትም ሥልጣን ተሰጠው።
7ከዚህ በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ በፊቴም የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ በጣም ኃይለኛ የሆነ አራተኛ አውሬ ነበር፤ ትልቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት፤ ያደቅና ይበላ፣ የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ ይረጋግጥ ነበር። ከእርሱ በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየ ሲሆን፤ አሥር ቀንዶች ነበሩት።
8ስለ ቀንዶቹ ሳስብ ሳለሁ፣ ከመካከላቸው አንድ ሌላ ትንሽ ዘንድ ብቅ ሲል አየሁ፤ ከመጀመሪያዎቹ ቀንዶች ሦስቱ ከፊቱ ተነቃቀሉ፤ ይህም ቀንድ የሰው ዐይኖችን የሚመስሉ ዐይኖች፣ በትዕቢትም የሚናገር አፍ ነበረው።
9እኔም ስመለከት፣ ዙፋኖች ተዘረጉ፣ ጥንታዌ ጥንቱም ተቀመጠ፣ ልብሱ እንደ በረዶ ነጭ ነበረ፣ የሩስም ጠጉር እንደ ጥጥ ነጭ ነበረ፣ ዙፋኑ የእሳት ነበልባል፣ መንኩራኩሮቹም ሁሉ እንደሚነድ እሳት ነበር፥
10የእሳት ወንዝ ከፊት ለፊት ፈልቆ ይፈስ ነበር ሺህ ጊዜ ሺዎች ያገለግሉት ነበር፤ እልፍ ጊዜ እልፍ በፊቱ ቆመዋል፤ የፍርድ ጉባዔ ተሰየመ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ።
11ቀንዱም ከሚናገረው የትዕቢት ቃል የተነሣ፣ መመልከቴን ቀጠልሁ፣ አውሬው እስኪታረድና እካሉድቆ ወደሚንበለበለው እሳት እስኪጣል ድረስ ማየቴን አላቋርጥሁም።
12ሌሎቹም አራዊት ሥልጣናቸው ተገፎ ነበር፤ ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜና ወቅት በሕይወት እንዲኖሩ ተፈቀደላቸው።
13ሌሊት ባየሁት ራእይ የሰውን ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመና ጋር ሲመጣ አየሁ፤ ወደ ጥንታዌ ጥንቱ መጣ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት።
14ሥልጣን፣ ክብርና ታላቅ ኃይል ተሰጠው፤ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች፤ መንግሥታትና ሕዝቦች ሰገዱለት፤ ግዛቱም ለዘላለም የማያልፍ ነው፤ መንግሥቱም ፈጽሞ የማይጠፋ ነው።
15እኔ ዳንኤል በመንፈሴ ታወክሁ፤ ያየሁትንም ራእይ እጅግ አስጨነቀኝ።
16በዚያ ከቆሙት ወደ አንዱ ቀርቤ የዚህ ሁሉ ትርጕም ምን እንደ ሆነ ጠየቅሁት።
17“አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ መንግሥታት ናቸው፤
18ነገር ግን የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ፣ ለዘላለምም ይይዙታል።
19ከዚያም የሚያደቅቀውንና የሚበላውን የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ የሚረጋግጠውን የብረት ጥርሶችና የናስ ጥፍሮች የነበሩትን ከሌሎች የተለየና እጅግ አስፈሪ የሆነውን የአራተኛውን አውሬ ምንነት የበለጠ ማወቅ ፈለግሁ።
20ደግሞም በራሱ ላይ ስላሉት አሥር ቀንዶች፣ ከመካከላቸው ብቅ ስላለው ቀንድና ከዚሁ ቀንድ ፊት ስለተነቃቀሉት ሦስት ቀንዶች፣ እንደዚሁም ከሌሎች ስለበለጠው የሰው ዓይኖች የሚመስሉ ዓይኖች በትዕቢትም የሚናገር አፍ ስለነበሩት ስለዚሁ ቀንድ ማወቅ ፈለግሁ።
21እየተመለክትኩም ሳለሁ ይህ ቀንድ በቅዱሳን ላይ ጦርነት ዐውጆ አሸነፋቸው።
22ይህም የሆነው ጥንታዌ ጥንቱ እስኪመጣና ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪፈርድላቸው ድረስ ነበር፤ ኪዝያም የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን የሚወርሱበት ዘመን መጣ።
23እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “አራተኛው አውሬ በምድር ላይ የሚነሣ አራተኛው መንግት ነው። ከሌሎች መንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፤ መላውንም ምድር እየረገጠና እያደቀቀ ይበላል።
24ዐሥሩ ቀንዶች ከዚህ መንግሥት የሚወጡ ዐሥር ነገሥታት ናቸው፤ ከዚያም በኋላ ከእነርሱ የተለየ ሌላ ንጉሥ ይነሣል፤ ሦስቱንም ነገሥታት ያንበረክካል።
25በልዑል ላይ የዓመፅ ቃል ይናገራል፤ የልዑልንም ቅዱሳን ያስጨንቃል፤ ለበዓላት የተመደበውን ጊዜና ሕግን ለመለወጥ ይሞክራል፤ እነዚህም ነገሮች ለዘመን፣ ለዘመናት፣ ለዘመን እኩሌታም ለእርሱ ዐልፈው ይሰጣሉ።
26ነገር ግን የፍርድ ዙፋን ይዘረጋል፤ ሥልጣኑም ይወሰድበታል፤ ፈጽሞ ለዘላለም ይደመሰሳል።
27ከዚያም ከሰማይ በታች ያሉ መንግሥታት ልዕልና፣ ሥልጣንና ታላቅነት ለልዑሉ ሕዝብ ለቅዱሳን ይሰጣል። መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ይሆናል፤ ገዦች ሁሉ ያመልኩታል ይታዘዙታልም።
28የነገሩ ፍጻሜ ይህ ነው፤ እኔም ዳንኤል በሃሳቤ እጅግ ተጨነቅሁ፤ መልኬም ተለወጠ፤ ይሁን እንጂ ነገሩን በልቤ ጠበቅሁት።