1እኔም፣ ሜዶናዊ ዳርዮስ በነገሠ በመጀመሪው ዓመት እርሱን ለማገዝና ለማበርታት በአጠገቡ ቆሜ ነበር፡፡
2አሁንም እውነቱን እነግርሃለሁ፤ እነሆ ሦስት ሌሎች ነገስታት በፋርስ ይነሳሉ፤ አልተኛውም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ እጅግ ባለጠጋ ይሆናል፡፡ በባለጠግነቱም እጅግ በበረታ ጊዜ ሌላውን ሁሉ አሳድሞ በግሪክ መንግስት ላይ ያስነሣል፡፡
3ከዚያም በታላቅ ኃይል የሚገዛና የወደደውንም ሁሉ የሚያደርግ ሃይል ንጉስ ይነሣል፡፡
4በኃይሉ እየገነነ ሳለም፣ መንግስቱ ይፈርሳል፤ ወደ አራቱ የሰማይ ነፍሳትም ይከፋፈላል፡፡ መንግስቱ ተወስዶ ለሌሎች ስለሚሰጥ ለዘሩ አይተላለፉም፤ ኃይሉም እንደ መጀመሪያው አይሆንም
5የደቡብ ንጉስ ይበረታል፤ ነገር ግን ከጦር አዛዦቹ አንዱ ከእርሱ የበለጠ የበረታ ይሆናል፣ ግዛቱም ታላቅ ይሆናል፡፡
6ከጥቂት ዓመታት በኋላም አመቺ ጊዜ ሲያገኙ አንድነት ይፈጥራሉ፡፡ የደቡብ ንጉስ ሴት ልጅ ስምምነት ለማድረግ ወደ ሰሜኑ ንጉስ ትሄዳለች፤ ነገር ግን ኃይሏን ይዞ መቆየት አትችልም፤ በእነዚያ ቀናት እርሷ ከቤተ መንግስት አጃቢቿ፣ ከአባቷና ከደጋፊዎቿ ጋር አልፋ ትሰጣለች፡፡
7ከዘመዶቿ አንዱ ስፍራዋን ሊይዝ ይነሳል፤ የሰሜኑን ንጉስ ሰራዊት ይወጋል፤ ምሽጎቹንም ጥሶ ይገባል፤ ከእነርሱም ጋር ተዋግቶ ድል ያደርጋል፡፡
8አማልክታቸውን፤ የብረት ምስሎቻቸውን፣ ከክብርና ከወርቅ የተሰሩ የክብሩ ዕቃዎቻቸውን ይማርካሉ፤ ወደ ግብፅም ይወስዳል፡፡ ለጥቂት ዓመታም ከሰሜኑ ንጉስ ጋር ከመዋጋት ይቆጠባል፡፡
9የሰሜኑም ንጉስ፣ የደቡቡን ንጉስ ግዛት ይወራል፤ ነገር ግን አፈግፍጎ ወደ ገዛ አገሩ ይመለሳል፡፡
10ወንዶች ልጆቹም ለጦርነት ይዘጋጃሉ፤ እስከ ጠላት ምሽግ ደርሶ የሚዋጋና ሊቋቋሙት እንደማይቻል ጎርፍ የሚጠራርግ ታላቅ ሰራዊት ይሰበስባሉ፡፡
11ከዚያም የደቡቡ ንጉስ በቁጣ ወጥቶ የሰሜኑን ንጉስ ይወጋል፡፡ የሰሜኑ ንጉስ ታላቅ ሰራዊት ቢያሰባስብም ሰራዊቱ ለደቡብ ንጉስ አልፎ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
12ሰራዊቱ በሚማረክበት ጊዜ ልቡ በትዕቢት ይሞላል፤ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችንም ይገድላል፤ ነገር ግን በድል አድራጊነቱ አይጸናም፡፡
13የሰሜን ንጉስ ከመጀመሪው የሚበልጥ ታላቅ ሰራዊት ያሰባስባል፤ ከብዙ አመታ በኋላ በትጥቅ እጅግ ከተደራጀ ታላቅ ሰራዊት ጋር ተመልሶ ይመጣል፡፡
14በዚያም ዘመን ብዙዎች በደቡብ ንጉስ ላይ ይነሣሉ፡፡ ራዕዩ ይፈጸም ዘንድ ከህዝብህ መካከል ዐመፀኛ የሆኑ ሰዎች ይከሣሉ፤ ነገር ግን ተሰነካክለው ይወድቃሉ፡፡
15የሰሜኑም ንጉስ መጥቶ የዐፈር ድልድል ይክባል፤ የተመሸገእውንም ከተማ ይይዛል፡፡ የደቡቡ ሰራዊትም ለመቋቋም ኋይል ያጣል፤ የተመረጡት ተዋጊዎቻቸው እንኳ ፀንተው መዋጋት አይችሉም፡፡
16ነገር ግን የሰሜኑ ንጉስ በደቡቡ ንጉስ ላይ ደስ ያሰኘውን ያደርጋል፤ ማንም ሊቋቋመው አይችልም፡፡ በመልካሚቱ ምድር ላይ ይገዛል እርሷን ለማይፋትም ኋይል ይኖረዋል፡፡
17የሰሜኑ መንግስት ያለውን ሠራዊት ሁሉ ይዞ ለመምጣት ይወስናል፤ ከደቡቡም ንጉስ ጋር ይስማል፣ የደቡቡንም መንግስት ለመጣል ሴት ልጁን ይድርለታል፤ ይሁን እንጂ ዕቅዱ አይሳካለትም፤ ያሰበውም ነገር አይጠቅመውም፡፡
18ከዚህም በኋላ በባሕር ጠረፍ ወዳሉት አገሮች ፊቱን በመመለስ ብዙዎቹን ይይዛል፤ ነገር ግን አንድ አዛዥ ትዕቢቱን ያከሸፍበታል፤ በራሱም ላይ ይመልስበታል፡፡
19በገዛ አገሩ ወዳሉት ምሽጎችም ፊቱን ይመልሳል፤ ነገር ግን ተሰናክሎ ይወድቃል፤ ደግሞም አይታይም፡፡
20በእርሱ ቦታ የሚተካውም የመንግስቱን ክብር ለማስጠበቅ የሚውል ግብር እንዲከፍል የሚያስገድድ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ በቁጣ ወይም በጦርነት ሳይሆን በጥቂት ዓመታ ውስጥ ይደመሰሳል፡፡
21በእርሱም ፋንታ የተናቀ ሰው የነግሣል፤ ለእርሱም ሕዝቡ ንጉሳዊ ክር አይሰጡትም፣ በቀስታ ይገባና በተንኮል መንግስቱን ይዛል፡፡
22ከፊቱ የሚቆመው ሰራዊት እንደ ጎርፍ ተጠራርጎ ይወሰዳል፡፡ ሰራዊቱና የቃል ኪዳኑም አለቃ ሳይቀር ይደመሰሳሉ፡፡
23ከእርሱ ጋር ስምምነት ከተደረገ በኋላ የማታለል ስራውን ይሰራል፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር በብርታት እየጨመረ ይሄዳል
24የበለጸጉትን ክፍለ አገሮች በሰላ ሳሉ በድንገት ይወሯቸዋል፤ አባቶቹም ሆኑ አያቶቹ ያላደረጉትን ነገር ያደርጋሉ፤ ብዝበዛውን ምርኮውንና የተገኘውን ሀብት ሁሉ ለተከታዮቹ ያካሏቸዋል፤ ምሽጎችን ለመጣል ያሤራል፤ ይህን የሚያደርገውም ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፡፡
25“ታላቅ ሠራዊት አደራጅቶ ኀይሉንና ብርታቱን በደቡብ ንጉስ ላይ ይነሳሳል፤ የደቡብ ንጉሱም ብርቱ የሆነ ኃይል ሰራዊት ይዞ ጦርነትን ያውጃል፤ ከር ግን ከተዶለተበት ሴራ የተነሳ መቋቋም አይእል፣፡፡
26ከንጉስ ማዕድ አብረውት ሲበሉ የነበሩት፤ ብዙዎቹም በጦርነት ይገደላሉ፡፡
27አንዳቸው በሌላኛው ላይ ልባቸው ወደ ክፋት ያዘነበለው ሁለት ነገስታት፣ በአንድ ገበታ አብረው ይቀመጣሌ፤ እርስ በእርሳቸውም በከንቱ ውሸት ይነጋገራሉ፤ ምክንያቱም ፍፃሜ የሚሆነው በተወሰነው ጊዜ ነው
28የሰሜን ንጉስ ብዙ ሃብት ይዞ ወደ ሀዛ አገሩ ይመለሳ፤ ነገር ግ ልቡ በተቀደሰው ኪዳን ላይ ይነሣሣል፤ የወደደውን ያደርጋል፣ ከዚያም ወደ ገዛ አገሩ ይመለሳል፡፡
29በተወሰነው ጊዜ ይመለስና ደቡቡን እንደ ገና ይወርራል፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ውጤቱ ከበፊቱ የተለየ ይሆናል፡፡
30የኪቲም መርከቦች ይቃወሙታል፤ ልቡም ይሸበራል፡፡ ወደ ኋላም ይመለሳል፤ ቁጣውን በተቀደሰው ኪዳን ላይ ይወርዳል፤ ተመልሶም የተቀደሰውን ኪዳ የተዉትን ይንከባከባል፡፡
31የጦ ሠራዊቶቹም ቤተ መቅደሱንና ቅጥሩን ያረክሳሉ፤ የዘውትሩንም መስዋዕት ያስቀራሉ፤ በዚያም ፍፁም ጥፋትን የሚያመጣውን የጥፋት ርኩሰት ይተክላሉ፤
32ኪዳኑን የሚተላለፉትን በማታለል ይስታል ይረክስባቸዋልም፤ አምላካቸውን የሚያውቁ ሕዝብ ግን ደንተው ይቃወሙታል፤ ርምጃም ይወስዳሉ፡፡
33“ለጊዜው በሰይፍ ቢወድቁም፣ ቢቃጠሉም፣ ቢማረኩና ቢዘረፉም፣ ጥበበኛ የሆኑ ሰዎች ብዙዎችን ያስተምራሉ፡፡
34በሚወድቁበት ጊዜ መጠነኛ ርዳታ ይገኛሉ፤ እውነተኛ ያልሆኑ ብዙ ሰዎችም ይተባበሯቸዋል፡፡
35ጥበበኛ ከሆኑ ሰዎች አንዳንዶቹ ይሰናከላሉ፣ ይህም እስከ ፍፃሜ ዘመን ድረስ የጠሩ፣ የነጠሩና እንከን የሌለባቸው ይሆን ዘንድ ነው፤ የተወሰነው ጊዜ ገና አልደረሰምና፡፡
36ንጉሱ እንዳለው ያደርጋል፤ ከአማልክት ሁሉ በላይ ራሱን እጅግ ከፍ በማድረግ በአማልክት አማላክ ላይ አስገራሚ ነገሮችን ይናገራል፤ የቁጣውም ዘመን እስኪፈጸም ይሳካለታል፤ የተወሰነ ነገር ሁሉ መሆን አለበትና።
37ሴቶች ለሚወዱትም ሆነ ለአባቶቹ አምላክ ትክብርን አይሰጥም፤ ማንኛውንም አምላክ አያከብርም፤ ነገር ግን ራሱን ከእነዚህ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል።
38በእነርሱም ምትክ የምሽጎችን አምላክ ያደብራል፤ አባቶቹ የማያውቁትን አምላክ በወርቅ፣ በብር፣ በከበሩ ድንጋዮችና በውድ ስጦታዎች ያከብራል።
39በባዕድ አምላክ ርዳታ ጽኑ ምሽቶችን ይወጋል፤ ለእርሱ የሚገዙትን በእጅጉ ያከበራቸዋል፤ በብዙ ሕዝብ ልያ ገዦች ያደርጋቸዋል፤ ምድሩንም በዋጋ ያከፋፍላቸዋል።
40“በመጨረሻው ዘመን የደቡብ ንጉሥም ጦርነት ያውጅበታል፤ የሰሜን ንጉሥም በፈረሰኞችና በሰርጎች በብዙ መርከቦችም እንደ ማዕበል ይመጣበታል፤ ብዙ አገሮችን ይወራል፤ እንደ ጎርም እየጠራረገ በመካከላቸው ያልፋል።
41የከበረችውንም ምድር ይወራል፤ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩእስራኤላውያንም ተሰነካክለው ይወድቃሉ፣ ነገር ግን ከኤዶም፣ ከሞዓብ ብዙ ሰዎች እንዲሁም ከአሞን የቀሩት ሕዝብ ከእጁ ያመልጣሉ።
42ሥልጣኑን በብዙ አገሮች ላይ ያንሰራፋል ግብፅም አታመልጥ።
43የወርቅና የብር ክምችትን፣ እንዲሁም የግብፅን ሀብት ሁሉ በቁጥጥሩ ሥር ያደርጋል፤ የሊቢያና የኢትዮጵያ ሰዎችም ይገዙታል።
44ነገር ግን ከምሥራቅና ከሰሜን የሚመጣ ወሬ ያስደነግጠዋል፤ ብዙዎችንም ለማጥፋትና ለመደምሰስ በታላቅ ቁጣ ይወጣል።
45ንጉሣው ድንኳኖቹን በባሕሮች መካከል ውብ በሆነው ቅዱስ ተራራ ላይ ይተክላል፤ ይሁን እንጂ ወደ ፍጻሜው ይመጣል፤ ማንም አይረዳውም።