1በዚያን ዘመን ስለ ሕዝብህ የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል። መንግሥታት ከተመሠረቱበት ጊዜ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ የመከራ ጊዜ ይሆናል። ነገር ግን በዚያን ጊዜ ስማቸው በመጽሐፉ ተጾጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ ይድናሉ።
2በምድር አፈር ውስጥ ካንቀላፉት ብዙዎች ይነቃሉ፤ አንዳንዶቹ ለዘላለም ሕይወት፣ ሌሎቹም ለውርደትና ለዘላለም ጉስቁልና ይነሣሉ።
3ጥበበኞች እንደ ሰማይ ጸዳል፣ ብዙዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ክዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ።
4ዳንኤል ሆይ፣ አንተ ግን፣ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የመጽሐፉን ቃል ዝጋ አትመውም። ብዙዎች ወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ ዕውቀትም ይበዛል።
5እኔም ዳንኤል ተመለከትሁ፤ እነሆ ከፊት ለፊቴ ሌሎች ሁለት ቆመው ነበር፤ አንዱ ከወንዙ በዚህኛው ዳር፣ ሌላው ደግሞ ከወንዙ በዚያኛው ዳር።
6ከእነርሱም አንዱ፣ ከወንዙ በላይ የነበረውንና በፍታ የለበሰውን ሰው፣ እነዚህ አስደናቂ ነገሮች ሊፈጽሙ ምን ያህል ጊዜ ይቀራል?” አለው።
7ከወንዙ ውሃ በላይ የነበረው በፍታ የለበሰው ሰው፣ ቀኝ እጁንና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አንሥቶ፣ “ለዘመን፣ ለዘመናት፣ ለዘምንም እኩሌታ ማለትም ለሦስት ዓመት ተኩል ይሆናል፤ የተቀደሰው ሕዝብ ኃይል መስበር ሲያከትም፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ይፈጸማሉ” ብሎ ለዘላልም በሚኖረው በእርሱ ሲምል ሰማሁ።
8እኔም ሰማሁ፤ ነገር ግን አላስተዋልሁትም፤ ስለዚህ፣ ጌታዬ፣ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ ምንድን ነው?” ብዬ ጠየቅሁ።
9እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ቃሉ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ስለሆነ ሂድ፤
10ብዙዎቹ ይነጻሉ፤ ይጠራሉ እንከን አልባምይሆናሉ፤ ክፉዎች ግን በክፋታቸው ይድናሉ፤ ከክፉዎች አንዳቸውም አያስተውሉም፣ ጠቢባን ግን ያስተውላሉ።
11“የዘወትሩ መሥዋዕት ከተቋረጠበትና ፍጹም ጥፋት የሚያመጣው አስጸያፊ ርኵሰት ከተተከለበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል።
12የሚታገሥና እስከ አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሰለሳ አምስት ቀን ፍጻሜ የሚደርስ የተባረከ ነው።
13“አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ድረስ ሂድ፣ ታርፋለህ፤ በቀኖች መጨረሻም ተንሥተህ የተመደበልህን ርስት ትቀበላለህ።”