መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ቆላስይስ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ከሞት ካስነሣችሁ፤ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያሉትን ነገሮች እሹ።
2በላይ ስላሉት ነገሮች እንጂ በምድር ስላሉት ነገሮች አታስቡ።
3ምክንያቱም ሞታችኋል፤ ሕይወታችሁንም እግዚአብሔር በክርስቶስ ውስጥ ሰውሮታልና።
4ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እናንተም ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።
5ስለዚህ ምድራዊ ምኞቶቻችሁን ግደሉ፦ እነርሱም፦ ዝሙት፣ ርኩሰት፣ ፍትወት፣ ክፉ ምኞት፣ ስግብግብነትና ጣዖትን ማምለክ ናቸው።
6በእነዚህም ነገሮች ምክንያት በማይታዘዙ ልጆች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣባቸዋል።
7እናንተም ራሳችሁ ከዚህ በፊት በማይታዘዙ ሰዎች መካከል ሳላችሁ እነዚህን ነገሮች እያደረጋችሁ ትመላለሱ ነበር።
8አሁን ግን ቁጣን፤ ንዴትን፤ ተንኮልን፤ ስም ማጥፋትን ከእናንተ አስወግዱ፤ የሚያሳፍር ንግግርም ከአፋችሁ አይውጣ።
9አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር አውልቃችሁ ስለ ጣላችሁ፣ አንዳችሁ በሌላው ላይ አትዋሹ።
10የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል ዕውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል።
11በዚህ ዕውቀት በግሪካዊና በአይሁዳዊ፣ በተገረዘና ባልተገረዘ፣ በሠለጠነና ባልሠለጠነ፣ በባሪያና በነጻ ሰው መካከል ልዩነት የለም፤ ክርስቶስ ግን ሁሉ ነው፤ በሁሉም ነው።
12ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳንና የተወደዳችሁ ሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ገርነትን፣ ትዕግሥትን ልበሱ።
13እርስ በርሳችሁ ታገሱ፤ እርስ በርሳችሁም ቸሮች ሆኑ። ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅርታ ቢኖረው፣ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።
14በዚህ ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነው ፍቅር ይኑራችሁ።
15የአንድ አካል ክፍሎች ሆናችሁ የተጠራችሁት ለዚህ ሰላም ስለ ሆነ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይንገሥ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ።
16የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ። በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤በመዝሙርና በውዳሴ፤ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።
17በእርሱ እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ በቃልም ሆነ በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።
18ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደሚገባ ለባሎቻችሁ ታዘዙ።
19ባሎች ሆይ፥ ሚስቶቻችሁን ውደዱ መራራም አትሁኑባቸው።
20ልጆች ሆይ፥ ይህ ጌታን ደስ የሚያሰኝ በመሆኑ ለወላጆቻችሁ በሁሉ ነገር ታዘዙ።
21አባቶች ሆይ፥ልጆቻችሁ ተስፋ እንዳይቆርጡ አታስመርሩአቸው።
22አገልጋዮች ሆይ፥ ሰውን ለማስደሰትና ለታይታ ሳይሆን በቅን ልብ ጌታን በመፍራት ለምድራዊ ጌቶቻችሁ በሁሉ ነገር ታዘዙ።
23የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው እንደምታደርጉ ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት።
24ከጌታ ዘንድ እንደ ዋጋ የምትቀበሉት ርስት እንዳለ ታውቃላችሁና።
25በዚህም የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስን ነው። በእግዚአብሔር ዘንድ አድልዎ ስለሌለ ክፉ የሚሠራ ማንም ስለ ክፉ ሥራው ቅጣቱን ይቀበላል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።