መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ቆላስይስ 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ጌቶች ሆይ፥ እናንተም በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ዐውቃችሁ ለአገልጋዮቻችሁ በትክክልና የሚገባቸውን ስጡአቸው።
2በንቃት እግዚአብሔርን እያመሰገናችሁ ሳታቋርጡ ጸልዩ።
3የክርስቶስ ምሥጢር የሆነውን የቃሉን እውነት መናገር እንድንችል እግዚአብሔር በር እንዲከፍትልን ለእኛም ደግሞ በአንድ ልብ ጸልዩልን፤ ምክንያቱም እስር የሆንኩት ስለእርሱ ነውና።
4እኔም እንደሚገባ ቃሉን መግለጥና መናገር እንድችል ጸልዩልኝ።
5በውጪ ካሉት ጋር በጥበብ ተመላለሱ፤ ዘመኑንም ዋጁ።
6ለእያንዳንዱ ሰው እንዴት መመለስ እንዳለባችሁ እንድታውቁ ንግግራችሁ ሁልጊዜ በጨው እንደ ተቀመመ በጸጋ ይሁን።
7ቲኪቆስ መጥቶ እኔ ስላለሁበት ሁኔታ ሁሉንም ነገር ይነግራችኋል። እርሱም ተወዳጅ ወንድም፤ ታማኝ አገልጋይና በጌታ ሥራም የአገልግሎት ባልደረባዬ ነው።
8እርሱንም ወደ እናንተ የላክሁበት ምክንያት ስለ እኛ ሁኔታ ትክክል የሆነውን እንዲነግራችሁና ልባችሁንም እንዲያጽናና ነው።
9ከእርሱም ጋር የእናንተ ወገን የሆነውን የታመነውንና የተወደደውን ወንድም አናሲሞስን ወደ እናንተ ልኬዋለሁ። እነርሱ በዚህ ስፍራ የተደረገውን ነገር ሁሉ ይነግሩአችኋል።
10ከእኔም ጋር የታሰረው አርስጥሮኮስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ አንድ ጊዜ፥ «ወደ እናንተ በሚመጣበት ጊዜ ተቀበሉት» ብዬ አሳስቤአችሁ የነበረው የበርናባስ የአጎት ልጅ ማርቆስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል።
11ኢዮስጦስ ተብሎ የሚጠራው ኢያሱም ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ከተገረዙ ወገኖች መካከል ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩት ሰዎች እነዚህ ብቻ ናቸው፤ ለእኔም መጽናናት ሆነውኛል።
12የእናንተ ወገን የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ኤጳፍራም ሰላምታ ያቀርብላችኋል። እርሱም ፍጹም ጠንክራችሁና ሙሉ በሙሉ ተማምናችሁ በእግዚአብሔር ፈቃድ በሁሉ ጸንታችሁ እንድትቆሙ ዘወትር ስለ እናንተ በጸሎት እየተጋ ነው።
13ስለ እናንተ በሎዶቅያና በሂራፖሊስ ስላሉትም ሰዎች ተግቶ እንደሚሠራ እኔ ራሴ እመሰክርለታለሁ።
14የተወደደው ሐኪም ሉቃስና ዴማስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
15በሎዶቅያ ላሉት ወንድሞች ለንምፉና በቤትዋም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ ።
16ይህን መልእክት እናንተ ካነበባችሁ በኋላ በሎዶቅያ ሰዎች ዘንድ ባለችው ቤተ ክርስቲያን እንዲነበብ አድርጉ፤እናንተም ከሎዶቅያ የሚላክላችሁን መልእክት አንብቡ።
17ለአርኪጳስም፥ «በጌታ አገልግሎት የተሰጠህን ሥራ በጥንቃቄ ፈጽም» ብላችሁ ንገሩልኝ።
18ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍኩት እኔ ጳውሎስ ነኝ፤ በሰንሰለት ታስሬ እንዳለሁ አስታውሱና ጸልዩልኝ። የእግዚአብሔር ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።