1ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፤ የበጋ ፍሬ ቅርጫት ተመለከትሁ!
2እርሱም፥ «አሞጽ፥ ምን ታያለህ?» አለኝ። እኔም፥ «የበጋ ፍሬ ቅርጫት» አልሁት። ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ «በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፍጻሜ መጥቶአል፤ ከእንግዲህ ወዲያ አልምራቸውም።
3የቤተ መቅደሱ ዝማሬ ዋይታ ይሆናል። የጌታ እግዚአብሔር አዋጅ ይህ ነው፥ በዚያን ቀን፥ «አስከሬኑ ብዙ ይሆናል፤ በሁሉ ሥፍራ በዝምታ ይጥሏቸዋል።»
4እናንተ ችግረⶉችን የምትረግጡና የምድሪቱን ድኾች የምታጠፉ ስሙ።
5እንዲህ ይላሉ፦«እህል እንሸጥ ዘንድ የወር መባቻው መቼ ያልፋል? በሐሰተኛ ሚዛን እያታለልን፥ መስፈሪያውን እያሳነስን፥ ዋጋውን ከፍ እያደረግን፥ ስንዴ ለገበያ እናቀርብ ዘንድ፥
6የስንዴውን ግርድ እንሸጥና ደኻውን በብር፥ ችግረኛውንም በጥንድ ጫማ እንገዛ ዘንድ ሰንብት መቼ ያልፋል?»
7እግዚአብሔር በያዕቆብ ክብር እንዲህ ሲል ምሎአል፦ «በእርግጥ የትኛውንም ሥራቸውን ፈጽሞ አልረሳም።»
8በዚህ ነገር፥ ምድር አትናወጥምን፥ በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ አያለቅሱምን? ሁለመናዋ እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፥ እንደ ግብጽ ወንዝም ወደ ላይ ይወረወራል፥ተመልሶም ይወርዳል።
9«በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል» ፥የእግዚአብሔር አዋጅ እንዲህ ይላል፥ «ፀሐይ በቀን እንድትጠልቅ አደርጋለሁ፥ በቀንም ብርሃን እያለ ምድርን አጨልማታለሁ»።
10ዓመት በዓላችሁን ወደ ልቅሶ፥ መዝሙራችሁንም ሁሉ ወደ ዋይታ እለውጣለሁ። ሁላችሁም ማቅ እንድትለብሱ፥ ጸጉራችሁንም እንድትላጩ አደርጋለሁ። ለአንድያ ልጅ እንደሚለቀስ፥ እንደ መራራም ቀን አደርገዋለሁ።
11ተመልከቱ፥ቀኖቹ እየቀረቡ ናቸው» ፥የእግዚአብሔር አዋጅ እንዲህ ይላል፥ «ረሓብን በምድር ላይ እሰድዳለሁ፥ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል የመስማት ረሓብ እንጂ እንጀራን የመራብ ወይም ውኃን የመጠማት አይደለም።
12የእግዚአብሔርን ቃል ፍለጋ ከባሕር ወደ ባሕር ይንከ ራተታሉ፥ ከሰሜን ወደ ምሥራቅ ይሮጣሉ፤ ነገር ግን አያገኙትም።
13በዚያን ቀን ያማሩ ደናግላንና ወጣቶች ከውኃ ጥም የተነሳ ይዝላሉ።
14'ዳን ሆይ ሕያው አምላክህን' ድግሞም 'ሕያው የቤርሳቤህ አምላክ' እያሉ በሰማርያ ኃጢአት የሚምሉ ፤ይወድቃሉ፥ዳግመኛም አይነሱም።»