መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

አሞጽ 6

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በጽዮን በምቾት፥በሰማሪያ ተራሮች ላይ ያለ ስጋት ለሚኖሩ፥የእስራኤል ቤት ለርዳታ ወደ እነርሱ ለሚመጡባችው፥ ለታላላቅ የሕዝብ አለቆች ወዮላቸው!
2መሪዎቻችሁ እንዲህ ይላሉ፦«ወደ ካልኔ ሂዱና ተመልከቱ፥ከዚያም ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ሐማት እለፉ፥ ከዚያም ወደ ፍልስጤም ጌት ውረዱ። እነርሱ ከእናንተ ሁለት መንግሥታት የተሻሉ ናቸውን? የእነርሱ ድንበር ከእናንተ ድንበር ይሰፋልን?»
3የጥፋትን ቀን ለምታርቁ፥የግፍንም መንበር ለምታቀርቡ ወዮላችሁ!
4ከዝሆን ጥርስ በተሠሩ አልጋዎች ላይ ይተኛሉ፥በመከዳዎቻቸውም ላይ ይዝናናሉ። ከበጎች መንጋ ጠቦትን፥ከበረትም ጥጃን ይበላሉ።
5በበገና ድምጽ ጣዕም የሌለው ዜማ ያዜማሉ፥ እንደ ዳዊት በተገኘው የሙዚቃ መሣሪያ መጫወት ይሻሉ።
6በዋንጫ የወይን ጠጅ ይጠጣሉ፥ ከሁሉ በተመረጠ ዘይት ይቀባሉ፥ ነገር ግን በዮሴፍ መጥፋት አያዝኑም።
7ስለዚህ ከመጀመሪያዎቹ ምርኮኞች ጋር ወደ ምርኮ ይሄዳሉ፥ የሚዝናኑቱ ድግሶችና ፈንጠዚያዎች ያከትማሉ።
8እኔ ጌታ እግዚአብሔር በራሴ ምያለሁ፥ ይህ የሠራዊት አምላክ የጌታ እግዚአብሔር አዋጅ ነው፦«የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፥ ምሽጎቹንም ጠልቼአለሁ። ስለዚህ ከተ ማይቱን በውስጧ ካሉት ሁሉ ጋር አሳላፌ አሰጣለሁ።»
9እንዲህም ይሆናል፤ በአንድ ቤት አሥር ሰዎች ቢቀሩ ሁሉም ይሞታሉ።
10የሰው ዘመድ አስከሬኖቹን ለመውሰድ በመጣ ጊዜ፤ አስከሬኖቹን ከቤት አውጥቶ የሚያቃጥላቸው ሰው፥ በቤት ውስጥ ያለውን ሰው፦«ከአንተ ጋር ሌላ ሰው አለን?» ሲለው፤ ሰውዬውም፦ «ማንም የለም» ብሎ በመለሰለት ጊዜ፥ እርሱም፦«ዝም በል፥ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት አይገባንምና» ይለዋል።
11ተመልከቱ፥ እግዚአብሔር ትዕዛዝ ይሰጣል፤ ትልቁም ቤት ይሰባበራል፥ ትንሹም ቤት ይደቅቃል።
12ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን? ሰውስ በዚያ ላይ በበሬዎች ያርሳልን? እናንተ ግን ፍትሕን ወደ መርዝነት፥ የጽድቅንም ፍሬ ወደ መራርነት ለውጣችኋል።
13እናንተ ሎዶባርን በማሸነፋችሁ ደስ ያላችሁ፥ «ቃርናይምን በራሳችን ብርታት አልወሰድንምን?» የምትሉ፤
14«ነገር ግን፥ የእስራኤል ቤት ሆይ አነሆ ሕዝብን አስነሣባችኋለሁ»፥ ይህ የሠራዊት አምላክ የጌታ እግዚአብሔር አዋጅ ነው። «ከሐማት መግቢያ አንስቶ እስከ ዓረባ ወንዝ ድረስ ያስጨንቋችኋል።»
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።