1የእስራኤል ቤት ሆይ፥ይህን ቃል ይኽውም በእናንተ ላይ የማሰማውን የሐዘን እንጉርጉሮ ስሙ።
2ድንግሊቱ እስራኤል ወደቀች፤ ከእንግህም ወዲያ አትነሳም፥ በራሷ ምድር ላይ ተተወች፤ የሚያነሳትም ማንም የለም።
3ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ለእስራኤል ቤት ሺህ ታወጣ የነበረች ከተማ መቶ ይቀርላታል፥ መቶም ታወጣ የነበረች ከተማ አሥር ይቀርላታል።»
4ከዚህ የተነሳ እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላል፦ «እኔን ፈልጉ፥በሕይወትም ኑሩ!
5ጌልጌላ በእርግጥ ትማረካለችና፥ በቴልም ታዝናለችና፤ ቤቴልን አትፈልጉ፥ወደ ጌልጌላ አትግቡ፥ ወደ ቤርሳቤህም አትሂዱ።
6እግዚአብሔርን ፈልጉ፥በሕይወትም ኑሩ፤ይህ ካልሆነ በዮሴፍ ቤት ላይ እንደ እሳት ይነሳል። ይበላል፥ በቤቴልም የሚያጠፋው ማንም የለም።
7እነዚያ ሰዎች ፍትህን ወደ መራራ ነገር ለውጠዋልና፥ ጽድቅንም ወደ ምድር ጥለዋልና።
8ሰባቱን ከዋክብትና ኦርዮንን የፈጠረ አምላክ፥ ጨለማን ወደ ንጋት ይለውጣል፥ ቀኑን በሌሊት ያጨልማል፥ የባሕርንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት ላይ ያፈሳቸዋል። ስሙ እግዚአብሔር ነው!
9ምሽጉ እንዲፈርስ ድንገትኛ ጥፋትን ያመጣል።
10በከተማይቱ በር ላይ የሚያርማቸውን ማንንም ጠሉ፥ እውነትን የሚናገረውን ማንንም ተጸየፉ።
11ድኻውን ረግጣችኋልና፥ የስንዴውን ም ድርሻ ከእርሱ ወስዳችኋልና፤ ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ብትሠሩም አትኖሩባቸውም። ያማሩ የወይን ተክል ቦታዎች አሉአችሁ፥ የወይን ጠጃቸውን ግን አትጠጡም።
12እናንተ ጻድቁን የምታጥቁ፥ ጉቦ የምትቀበሉ፥ በከተማይቱም በር ችግረኛውን የምትገለብጡ፤ በደላችሁ እንዴት ብዙ እንደሆን፥ ኃጢአታችሁም እንዴት ታላቅ እንደሆን እኔ አውቃለሁ።
13ጊዜው ክፉ ነውና፥ አስተዋይ የሆነ ማንም በእንደዚህ ዓይነቱ ጊዜ ዝም ይላል።
14በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን ፈልጉ፥ ክፉውንም አይደለም። እርሱም እንደተናገራችሁት ነውና፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር በእርግጥ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
15ክፉውን ጥሉ፥ መልካሙንም ውደዱ፥ በከተማይቱም በር ፍትሕን አጽኑ፤ ምናልባት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ለዮሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆናል።
16ሰለዚህ ጌታ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «በአደባባዮቹ ሁሉ ዋይታ ይሆናል፥ በየመንገዶቹ ወዮ! ወዮ! ይላሉ። ገበሬዎችን ለለቅሶ፥ አልቃሾችንም ለዋይታ ይጠራሉ።
17እኔ በመካከልህ አልፋለሁና፥ በወይን ተክል ቦታዎች ሁሉ ዋይታ ይሆናል» ይላል እግዚአብሔር።
18የእግዚአብሔርን ቀን ለምትፈልጉ ወዮላችሁ! የእግዚአብሔርን ቀን ለምን ትፈልጋላችሁ? ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም።
19አንድ ሰው ከአንበሳ ሲሸሽ ድብ እንደሚያጋጥመው፥ ወደ ቤት ገብቶ እጁን ግድግዳ ላይ ሲያስደግፍ እባብ እንደሚነድፈው ነው።
20የእግዚአብሔር ቀን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ አይደለምን? ብሩህ ሳይሆን ደብዛዛ አይደለምን?
21ዓመት በዓላችሁን ጠልቼዋለሁ፥ ተጸይፌዋለሁም፤በጉባዔዎቻችሁ ደስ አይለኝም።
22የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁንና የእህል ቁርባናችሁን ብታቀርቡልኝ እንኳን አልቀበላቸውም፤ ወይም ወደ ሰቡ እንስሶቻችሁ የኅብረት መሥዋዕት አልመለከትም።
23የመዝሙሮችህን ጩኽት ከእኔ አርቅ፤ የበገናህንም ድምጽ አልሰማም።
24በዚያ ፈንታ ፍትሕ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም ሳያቋርጥ እንደሚመነጭ ምንጭ ይፍሰስ።
25የእስራኤል ቤት ሆይ በምድረ በዳው ለአርባ ዓመታት መሥዋዕትንና ቁርባንን አቅርባችሁልኝ ነበርን?
26ለራሳችሁ የሠራችኋቸውን ጣዖታት፥ ሞሎክን እንደ ንጉሣችሁ፥ሬፋን እንደ ኮከብ አምላካችሁ አንሥታችሁ ትሸከማችሁ።
27ስለዚህ ከደማስቆ ማዶ እስማርካችኋለሁ» ይላል፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ የሆነው እግዚአብሔር።