1እናንተ የባሳን ላሞች፥በሰማሪያ ተራራ የምትኖሩ፥ድኾችን የምትጨቁኑ፥ችግረኞችን የምታደቅቁ፥ ባሎቻችሁንም «መጠጥ አምጡልን» የምትሉ ይህን ቃል ስሙ።
2ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ብሎ ምሎአል፦ «ተመልከቱ፥ እናንተን በመንጠቆ፥ የቀሩትንም በዓሳ መንጠቆ የ ሚወስዱበት ቀናት ይመጣል።
3በከተማው ቅጥር ፍራሽ በኩል ትወጣላችሁ፥እያንዳንዳችሁ በእርሱ በኩል ወደ ፊት ቀጥ ብላችሁ ትሄዳላችሁ፥ወደ ሬማንም ትጣላላችሁ--ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
4ወደ ቤቴል ሂዱና ኃጢአት ሥሩ፥ወደ ጌልጌላ ሂዱና ኃጢአት አብዙ። መሥዋዕታችሁን በየማለዳው፥ አሥራታችሁንም በየሦሥተኛው ቀን አቅርቡ።
5እርሾ ያለበትን የምስጋና መሥዋዕት ሠው፤ እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፥ ይህ ደስ ያሰኛችኋልና በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትን አው ጁ፥ ስለ እነርሱም አውሩ --- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
6የጥርስ ንፃትን በከተማዎቻችሁ ሁሉ፥ እንጀራንም ማጣትን በስፍራዎቻችሁ ሁሉ እሰጣችኋለሁ። እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም ---- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
7ለመከር ሦሥት ወር ሲቀረው ዝናብ ከለከልኋችሁ። በአንዱ ከተማ ላይ እንዲዘንብ፥ በሌላውም ከተማ ላይ እንዳይዘንብ አደረግሁ። በአንዱ ቁራጭ መሬት ላይ ዘነበበት፥ ያልዘነበበት ቁራጭ መሬት ግን ደረቀ።
8ሁለት ወይም ሦሥት ከተሞች ውኃ ለመጠጣት ወደ ሌላ ከተማ እየተንገዳገዱ ሄዱ፤ ነገር ግን አልረኩም። ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም --- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
9በዋግና በአረማሞ መታኋችሁ። የአትክልቶቻችሁን ብዛት፥ ወይኖቻችሁን፥ የበለስና የወይራ ዛፎቻችሁን ሁሉ አንበጦች በሉት። እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም --- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
10«በግብጽ ላይ እንዳደረግሁባቸው መቅሰፍት ላክሁባችሁ። ወጣቶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፥ ፈረሶቻችሁንም አስማረክሁ፥ የሠፈራች ሁንም ግማት ወደ አፍንጫችሁ እንዲደርስ አደረግሁ። እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም --- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
11እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን እንደገለበጣቸው፥ በመካከላችሁ ከተሞችን ገለበጥሁ።እናንተም ከእሳት እንደተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፥ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
12«ስለዚህ እስራኤል ሆይ አስደንጋጭ ነገር አደርግብሃለሁ፥ አስደንጋጭንም ነገር ስለማደርግብህ እስራኤል ሆይ አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ!
13እነሆ፥ ተራሮችን የሠራ፥ነፋስንም የፈጠረ፥ አሳቡንም ለሰው የሚገልጥ፥ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፥የምድርንም ከፍታዎች የሚረግጥ» ስሙ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።