መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

አሞጽ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእስራኤል ሕዝብ፥ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ ወገኖች ሁሉ፥እግዚአብሔር በእናንተ ላይ የሚናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤
2ከምድር ወገኖች ሁሉ እናንተን ብቻ መረጥሁ። ስለዚህ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ እቀጣችኋለሁ።
3ሁለቱ ካልተስማሙ በስተቀር አብረው ይሄዳሉን?
4አንበሳ የሚሰብረውን ሳያገኝ በጫካ ውስጥ ያገሳልን? የአንበሳ ደቦል ምንም ሳይዝ በዋ ሻው ውስጥ ያጉተመትማልን?
5ማታለያ ምግብ ካልተዘጋጀለት በስተቀር ወፍ በምድር ወጥመድ ዉስጥ ይገባልን? አንዳች ሳይዝ ወጥመድ ከምድር ይፈናጠራልን?
6በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? በከተማ ላይ ጥፋት ከመጣ የላከው እግዚአብሔር አይደለምን?
7በእርግጥ ጌታ እግዚአብሔር ሊያደርግ ያለውን ለአልጋዮቹ ለነቢያት ካልገለጠ በስተቀር ምንም አያደርግም።
8አንበሳው አገሳ፥የማይፈራ ማነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፥ትንቢት የማይናገር ማነው?
9ይህንን በአዛጦንና በግብጽ ምሽጎች አውጁ፥ እንዲህም በሉ፦«በሰማሪያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፥ በውስጧ ምን ዓይነት ታላቅ ግራ መጋባትና ጭቆና እንዳለ ተመልከቱ።
10ቅን ነገርን እንዴት እንደሚያደርጉ አያውቁምና፥ዝርፊያንና ጥፋትን በምሽጎቻቸው አከማችተዋል።» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።
11ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ጠላት ምድሪቱን ይከብባል፤ምሽጎቻችሁን ያፈርሳል ይበዘብዛልም።
12እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት እግር ብቻ፥ወይንም የጆሮ ቁራጭ እንደሚያድን፥ በመከዳ ጠርዝ ብቻ ወይም በትንሽ የአልጋ ልብስ በሰማሪያ የሚኖሩ የእስራኤል ሰዎች ብቻ ይድናሉ»
13ስሙ፥በያዕቆብም ቤት ላይ መስክሩ፥ ይላል የሠራዊት አምላክ ጌታ እግዚአብሔር።
14የእስራኤልን ኃጢአት በምቀጣበት ቀን የቤቴልን ም መሠዊያዎች እቀጣለሁ። የመሠዊያው ቀንዶች ይቆረጣሉ፥ወደ ምድርም ይወድቃሉ።
15የክረምቱን ቤት ከበጋው ቤት ጋር አጠፋለሁ። በዝሆን ጥርስ የተዋቡ ቤቶች ይጠፋሉ፥ታላላቅ ቤቶችም ይደመሰሳሉ፥» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።