1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «አመድ እስኪሆን ድረስ የኤዶምን ንጉሥ አጥንት አቋጥሏልና፤ ስለ ሞዓብን ሦሥት ኃጢአቶች፥ይልቁንም ስለ አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም።
2በሞዓብ ላይ እሳት እልካለሁ፥ የቂርዮትንም ምሽጎች ይበላል። ሞዓብ በጩኽትና በመለከትድምጽ፥ በሁካታ ውስጥ ይሞታል።
3በውስጧ የሚገኝውን ፈራጁን አጠፋለሁ፥ መሳፍንቱን ሁሉ ከእርሱ ጋር እገድላለሁ» ይላል እግዚአብሔር።
4እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፥ ትእዛዙንም አለጠበቁምና ስለ ሦሥት የይሁዳ ኃጢአቶች፥ይልቁንም ስል አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም። ሐሰታቸው አስቷቸዋልና፥በዚሁ መንገድ አባቶቻቸውም ሄዱ።
5እሳት በይሁዳ ላይ እልካለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም ምሽጎች ይበላል።
6እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ንጹሑን ስለ ብር፥ ችግረኛውንም ስለ ጥንድ ጫማ ሽጠዋልና ፤ስለ እስራኤል ሦሥት ኃጥአቶች፥ ይልቁንም ስለ አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም።
7ሰዎች በምድር ላይ ትቢያን እንደሚረግጡ፥ የድኾችን ራስ ይረግጣሉ፤ የተጨቆኑትን ይገፋሉ። አባትና ልጅ ከአንዲት ሴት ጋር ይተኛሉ፥ ቅዱስ ስሜንም ያረክሳሉ።
8በየመሠዊያው አጠገብ በመያዣነት በተወሰደ ልብስ ላይ ይተኛሉ፥በአምላካቸውም ቤት በመቀጫነት የተወሰደውን ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።
9ነገር ግን ቁመታቸው እንደ ዝግባ፥ጥንካሬያቸው እንደ ባሉጥ ዛፍ የነበረውን አሞራዊያንን ከፊታችው አጠፋሁ። ከላይ ፍሬውን፥ ከታችም ሥሩን አጠፋሁ።
10የአሞራውያንን ምድር እንድትወርሱ እናንተን ከግብፅ አወጣሁ፤ በምድረ በዳ አርባ ዓመት መራሁዋችሁ።
11ነቢያትን ከወንዶች ልጆቻችሁ፥ናዝራዊያንንም ከጎልማሶቻችሁ መካከል አስነሳሁ። የእስራኤል ህዝብ ሆይ፥ይህ እንደዚህ አይደለም ን? ይላል እግዚአብሔር።
12«እናንተ ግን ናዝራዊያንን የወይን ጠጅ ይጠጡ ዘንድ አሳባቸውን አስለወጣችሁ፥ነቢያቱንም እንዳይተነብዩ አዘዛችኋቸው።
13እነሆ፥በእህል የተሞላ ሰረገላ ሰውን እንደሚያደቅቅ እንዲሁ አደቅቃችኋለሁ።
14ፈጣኑ ሰው አያመልጥም፥ብርቱው ለራሱ ብርታትን አይጨምርም፥ኃያልም ራሱን አያድንም።
15ቀስተኛው አይቆምም፥ፈጣኑ ሯጭ አያመልጥም፥ፈረሰኛውም ራሱን አያድንም።
16ጅግኖቹ ተዋጊዎች እንኳን በቀን ዕርቃናቸውን ይሸሻሉ፤ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»