1በቴቁሔ ከነበሩት እረኞች መካከል አንዱ የሆነው አሞጽ፥ ስለ እስራኤል በራዕይ የተቀበላቸው ነገሮች አነዚህ ናቸው። እነዚህንም ነገሮች በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመነ መንግሥት፥በእስራኤል ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት፥የምድርም መናወጥ ከመሆኑ ከሁለት ዓ መት አስቀድሞ ተቀበለ።
2እንዲህም አለ፥«እግዚአብሔር ከጽዮን ይጮኻል፥ ከኢየሩሳሌምም ድምጹን ከፍ አድርጎ ያሰማል። የእረኞች ማሰማሪያ ዎች ያለቅሳሉ፥የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።»
3እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ገልዓድን በብረት መሣሪያ አድቅቋልና፤ ስለ ደማስቆ ሦሥት ኃጢአቶች፥ይልቁንም ስለ አራቱ ፥ ቅጣቴን አልመልስም።
4በአዛሄል ቤት ላይ እሳት እልካለሁ፥ የወልደ አዴርንም ምሽጎች ትበላለች።
5የደማስቆን በር መቀርቀሪያዎች እሰብራኣለሁ፥በአዌን ሸለቆ የሚኖረውን ሰውና በቤተ ኤደንም በትረ መንግሥት የያዘውን ሰው ድል ነሳለሁ፤ የሶርያም ሕዝብ ተማርኮ ወደ ቂር ይሄዳል» ይላል እግዚአብሔር።
6እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ለዔዶም አሳልፈው ሊሰጧቸው ሕዝቡን ሁሉ ማርከው ወስደዋልና፤ ስለ ጋዛ ሦሥት ኃጢአቶች፥ ይልቁን ም ስለ አራቱ ፥ ቅጣቴን አልመልስም።
7በጋዛ ቅጥሮች ላይ እሳት እልካልሁ፥ምሽጎቹዋንም ይበላል።
8በአሽዶድ የሚኖረውንና በአስቀሎና በትረ መንግሥት የያዘውን ሰው አጠፋለሁ። እጄን በአቃሮን ላይ እመልሳለሁ፥ የቀሩት ፍልስጤማውያንም ይጠፋሉ»ይላል እግዚአብሔር።
9እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«የሕዝብን ወገኖች ሁሉ ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋልና የወንድማማችነትንም ኪዳን አፍርሰዋልና፥ ስለ ጢሮስ ሦሥት ኃጢአቶች፥ ይልቁንም ስለ አራቱ፥ ቅጣቴን አለመልስም።
10በጢሮስ ቅጥሮች ላይ እሳት እልካለሁ፥ምሽጎችዋንም ሁሉ ይበላል።»
11እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፥ ርኅራኄንም ሁሉ ጥሎአልና፥ ቁጣው ሳያቋርጥ ነዶአልና፥ ቁጣው ለዘላለም ነውና፤
12በቴማን ላይ እሳት እልካለሁ፥ የባሶራንም አብያተ መንግሥት አጠፋለሁ።»
13እግዚእብሔር እንዲህ ይላል፦«ድንበሩን ለማስፋት የገለዓድን እርጉዝ ሴቶች ቀድዶአልና፤ ስለ አሞን ሕዝብ ሦሥት ኃጢአቶች፥ ይልቁንም ስለ አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም።
14በረባት ቅጥሮች ላይ እሳት አነድዳለሁ፥ በጦርነት ቀን ከጩኽት ጋር፥ በአውሎ ነፋስም ቀን ከማዕበል ጋር፤ አብያተ መንግሥትን ይበላል።
15ንጉሣቸው ከአለቆቻቸው ጋር ወደ ምርኮ ይሄዳል» ይላል እግዚአብሔር።