መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

የሐዋርያት ሥራ 5

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሐናንያ የሚባል አንድ ሰውም ከሚስቱ ከሰጲራ ጋራ መሬት ሸጠ፤
2የሽያጩን ገንዘብ ከፊል መጠን አስቀረው (ሚስቱም ታውቅ ነበር)፤ ሌላውን የገንዘብ መጠን ግን አምጥቶ በሐዋርያት እግር አጠገብ አስቀመጠው።
3ጴጥሮስ ግን ሐናንያን እንዲህ አለው፤ “ሐናንያ ሆይ፣ ለመንፈስ ቅዱስ እንድትዋሽና የመሬቱን ዋጋ ከፊል መጠን እንድታስቀር ሰይጣን ልብህን ለምን ሞላው?
4መሬቱ ሳይሸጥ የአንተ እንደ ሆነ አይዘልቅም ነበርን? ከተሸጠ በኋላስ በአንተ ቊጥጥር ሥር አልነበረምን? በልብህ ይህን ነገር እንዴት ዐሰብህ? የዋሸኸው ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰዎች አይደለም።
5እነዚህን ቃሎች ሰምቶ፣ ሐናንያ ወደቀ፤ ሞተም። በሰሙት ሁሉ ላይም ታላቅ ፍርሀት መጣ።
6ጐበዛዝቱ ወደ ፊት መጡና ከፈኑት፤ ወደ ውጭ አውጥተውም ቀበሩት።
7ከሦስት ሰዓት ያህል በኋላ፣ ሚስቱ ምን እንደ ሆነ ሳታውቅ ወደ ውስጥ ገባች።
8ጴጥሮስ፣ “መሬቱን ይህን ለሚያህል ዋጋ ሸጣችሁት ከሆነ ንገሪኝ” አላት። እርሷም፣ "አዎ፣ ይህን ለሚያህል ነው” አለችው።
9ከዚያም ጴጥሮስ፣ “የጌታን መንፈስ ለመፈታተን እንዴት ተስማማችሁ? ተመልከቺ፣ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በር ላይ ነው፤ አንቺንም ወደ ውጭ ያወጡሻል።”
10እርሷም ወዲያው በጴጥሮስ እግር ሥር ወደቀች፤ ሞተችም፤ ጐበዛዝቱም ወደ ውስጥ ሲገቡ ሞታ አገኟት፤ ወደ ውጭ አወጧትና በባሏ አጠገብ ቀበሯት።
11በቤተ ክርስቲያን ሁሉና እነዚህን ነገሮች በሰሙት ላይ ታላቅ ፍርሀት መጣ።
12በሕዝቡ መካከል ብዙ ምልክቶችና ድንቆች በሐዋርያት እጅ ይደረጉ ነበር። ሁሉም በሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በአንድነት ነበሩ።
13ነገር ግን አንድም ሌላ ሰው እንኳ ከእነርሱ ጋር ለመተባበር ድፍረት አልነበረውም፤ ሆኖም ከሕዝቡ ከፍተኛ አክብሮት ነበራቸው።
14አሁንም የበለጡ አማኞች፣ እጅግ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ለጌታ ይጨመሩ ነበር፤
15በሽተኞችንም እንኳ ተሸክመው ወደ መንገድ እያመጡ በዐልጋና በቃሬዛ ላይ ያስቀምጧቸው ነበር፤ ይኸውም ጴጥሮስ ሲያልፍ በተወሰኑት ላይ ጥላው እንዲያርፍባቸውነው።
16በሽተኞችንና በርኩሳን መናፍስት የሚሠቃዩትን በማምጣት በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካሉ ከተሞች አያሌ ሰዎችም በአንድነት ተሰበሰቡ፤ በሽተኞችም ሁሉ ተፈወሱ።
17ነገር ግን ሊቀ ካህናቱና ዐብረውት የነበሩትም ሁሉ ተነሡ (የሰዱቃውያን ወገን የሆነው ማለት ነው)፤ እነርሱም በቅናት ተሞልተው ነበር፤
18እጃቸውንም በሐዋርያት ላይ ጫኑ፤ በሕዝብ ወኅኒ ውስጥም አስገብተው አሰሯቸው።
19ይሁን እንጂ፣ የጌታ መልአክ በሌሊት የወኅኒውን በሮች ከፈተ፤ ወደ ውጭ አውጥቶአቸውም እንዲህ አላቸው፤
20“ሂዱ፤ በቤተ መቅደስ ውስጥ ቁሙና የዚህን ሕይወት ቃሎች ሁሉ ለአሕዝቡ ተናገሩ።”
21ይህን ሲሰሙም፣ ንጋት ላይ ወደ ቤተ መቅደስ ገቡና አስተማሩ። ነገር ግን ሊቀ ካህናቱና ከእርሱ ጋር የነበሩት መጡ፤ ሸንጎውንም በአንድነት፣ የእስራኤል ሕዝብ ሽማግሌዎችንም ጠሩ፤ ሐዋርያቱን እንዲያመጧቸውም ወደ ወኅኒው ላኩ።
22ነገር ግን የተላኩት መኰንኖች በወኅኒው ውስጥ አላገኟቸውም፤ ተመልሰው በመሄድም እንዲህ ብለው ተናገሩ፣
23“ወኅኒው በደኅና እንደ ተቈለፈና ጠባቂዎችም በር ላይ እንደ ቆሙ አግኝተናል፤ በከፈትነው ጊዜ ግን በውስጡ ማንንም አላገኘንም።”
24የመቅደሱ ጥበቃ ሹምና ሊቃነ ካህናቱ እነዚህን ቃላት ሲሰሙ፣ እስረኞችን በሚመለከት ምን እንደሚሆን እጅግ ግራ ተጋቡ።
25ከዚያም አንድ ሰው መጣና፣ “ወኅኒ ውስጥ ያስገባችኋቸው ሰዎች ቤተ መቅደስ ውስጥ ቆመው ሕዝቡን እያስተማሩ ናቸው” ብሎ ነገራቸው።
26ስለዚህ ሹሙ ከመኰንኖች ጋር ሄደ፤ መልሶም አመጣቸው፤ ያመጧቸው ግን በኀይል አልነበረም፤ ሕዝቡ በድንጋይ ይወግሯቸዋል ብለው ፈርተው ነበርና።
27አምጥተዋቸው በነበረ ጊዜ፣ በሸንጎው ፊት አቆሟቸው። ሊቀ ካህናቱም ጠየቃቸው፤
28እንዲህም አላቸው፤ “በዚህ ስም እንዳታስተምሩ በጥብቅ አስጠንቅቀናችሁ ነበር፤ እናንተ ግን ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋታል፤ የዚህን ሰው ደም በእኛ ላይ ለማምጣትም ትፈልጋላችሁ።”
29ጴጥሮስና ሐዋርያቱ ግን መልሰው፣ “ለሰው ከመታዘዝ ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።
30የአባቶቻችን አምላክ በዕንጨት ላይ በመስቀል የገደላችሁትን፣ ኢየሱስን አስነሣው።
31አዳኝና የሁሉ የበላይ እንዲሆን፣ ለእስራኤል ንስሓንና የኀጢአት ይቅርታን ለመስጠት እግዚአብሔር በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።
32እኛና እግዚአብሔር ለሚታዘዙት የሰጠው መንፈስ ቅዱስ የእነዚህ ነገሮች ምስክሮች ነን።”
33የሸንጎው አባሎች ይህን ሲሰሙ፣ በጣም ተናደዱ፤ ሐዋርያቱንም ለመግደል ፈለጉ።
34ነገር ግን የሕግ መምህር የነበረና ሕዝቡም ሁሉ የሚያከብረው ገማልያል የሚባል አንድ ፈሪሳዊ ተነሥቶ፣ ሐዋርያት ለተወሰነ ጊዜ ውጭ እንዲቈዩ አዘዘ።
35ከዚያም እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ በእነዚህ ሰዎች ልታደርጉ ያሰባችሁትን በጥንቃቄ ተመልከቱት።
36ከጥቂት ጊዜ በፊት ቴዎዳስ ትልቅ ሰው ነኝ በማለት ተነሥቶ ነበርና፤ አራት መቶ ያህል ወንዶችም ተከተሉት። እርሱ ተገደለ፤ ይታዘዙለት የነበሩትም ሁሉ ተበታትነው እንዳልነበሩ ሆኑ።
37ከዚህም ሰው በኋላ፣ የገሊላው ይሁዳ በቈጠራው ቀናት ዐምፆ የተወሰኑ ሰዎችን አስከትሎ ሄደ። እርሱም ሞተ፤ እርሱን ይታዘዙት የነበሩትም ተበታተኑ።
38አሁንም እነግራችኋለሁ፤ ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ፤ እነርሱንም ተዉአቸው፤ ይህ ዐሳብ ወይም ሥራ የሰዎች ከሆነ፣ ይጠፋል።
39የእግዚአብሔር ከሆነ ግን፣ ልታጠፏቸው አትችሉም፤ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጋጩም እንኳ እንዳትገኙ።” እነርሱም በዐሳቡ ተስማሙ።
40ከዚያም በኋላ፣ ሐዋርያቱን ወደ ውስጥ ጠርተው ገረፏቸው፤ በኢየሱስ ስም እንዳይናገሩም አዘዟቸውና ለቀቋቸው።
41እነርሱም ስለ ስሙ ይዋረዱ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ፣ ደስ እያላቸው ከሸንጎው ወጡ።
42ከዚያ በኋላ በየቀኑ፣ በቤተ መቅደስና ከቤት ወደ ቤት፣ በተከታታይ ኢየሱስ፣ ክርስቶስ እንደ ሆነ ያስተምሩና ይሰብኩ ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።