መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

2 ጢሞቴዎስ 2

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እንግዲህ ልጄ ሆይ በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጽጋ በርታ፡፡
2ከብዙ ምስክሮች ጋር ከእኔ የሰማኸውን፣ ሌሎችን ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ፡፡
3እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ወታደር ሆነህ አብረኸኝ መከራ ተቀበል፡፡
4አለቃውን ማስደሰት የሚፈልግ ወታደር በምድራዊው ነገር ራሱን አያጠላልፍም፡፡
5ማንም በስፖርታዊ ውድድር የሚሳተፍ፣ በደንቡ መሠረት ካልተወዳደረ የድሉን አክሊል ሊያገኝ አይችልም፡፡
6በርትቶ የሚሠራው ገበሬ ምርቱን ከሚበሉት የመጀመሪያው ሊሆን ይገባል፡፡
7የምለወን ተመልከት ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ፡፡
8በወንጌል መልእክቴ የገለጽኩትን፣ ከሙታን የተነሣውንና ከዳዊት ዘር የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፡፡
9በዚህም ምክንያት እንደ ወንጀለኛ በመታሰር መከራ እቀበላለሁ፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል አይታሰርም፡፡
10ስለዚህ ስለተመረጡት ስል በሁሉ እጸናለሁ፣ እነርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነውን መዳን ከዘላለማዊ ክብር ጋር ያገኙ ዘንድ፡፡
11እንዲህ የሚለው ቃል የታመነ ነው ‹‹ከእርሱ ጋር ከሞትን፣ ከእርሱ ጋር እንኖራለን፡፡
12ብንጸና ከእርሱ ጋር እንነግሣለን፡፡ ብንከዳው እርሱ ደግሞ ይክደናል፡፡
13ባናምነው እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፣ ራሱን ሊክድ አይችልምና፡፡
14እነዚህን ነገሮች አስታውሳቸው፡፡ በቃል እንዳይጣሉ በእግዚአብሔርም ዘንድ አስጠንቅቃቸው፣ይህ ምንም ጥቅም የሌለው የሚሰሙትንም የሚጎዳ ነው፡፡
15የእውነትን ቃል በትክክል የሚይዝ፣ የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነሀ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ትጋ፡፡
16እግዚአብሔርን ከመምሰል የሚያርቅህን አለማዊ ተረቶቸን አስወግድ፡፡
17ቃላቸው እንደ ቆላ ቁስል ነው፣ ከእነርሱም ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ ይገኙባቸዋል፣
18እነዚህም ሰዎች ከእውነት ርቀው ትንሣኤ ሙታነ ካሁን ቀደም ሆናል ይላሉ፣ በዚህም የአንዳንዶችን እምነት ይገለብጣሉ፡፡
19ሆኖም፣ ‹‹ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል›› ደግሞም ‹‹የጌታን ስም የሚጠራ ከዓመፃ ይራቅ›› የሚለው ማኅተም ያለበት የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል፡፡
20በሀብታም ቤት ውስጥ የሚገኙት የወርቅ እና የብር ዕቃዎች ብቻ አይደሉም ነገር ግን የእንጨት እና የሸክላ ዕቃዎችም ይገኛሉ፣ አንዳንዶቹ ለክብር ሌሎቹም ክብር ለማይሰጣቸው ሥራዎች ይውላሉ፡፡
21ማንም ከማያስከብር ሥራ ራሱን ቢያነጻ፣ የተከበረ ዕቃ፣ የተቀደሰ፣ ለጌታውም የሚጠቅም፣ ለማንኛውም መልካም ሥራ የተዘጋጀ ይሆናል፡፡
22ከወጣትነት ምኞት ራቅ፣ በንጹህ ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ሰላምን ተከታተል፡፡
23ነገር ግን ጠብን እንደሚያመጣ አውቀህ ከሰነፎችና ካልተማሩ ምርመራ ራቅ፡፡
24የጌታ አገልጋይ ሊጣላ አይገባውም፣ ከዚሀ ይልቅ ለሁሉ የሚጠነቀቅ፣ ለማስተማርም የሚበቃ በትእግስትም የሚጸና፣
25በትህትናም ለሚቃወሙት ትምህርት የሚሰጥ ሊሆን ይገባዋል፡፡ እውነትን በማወቃቸው እግዚአብሔር ምናልባት ንስሐን ይሰጣቸው ይሆናልና፣
26እንዲሁም ለዲያብሎስ እና ለፈቃዱ ከተያዙበት ወጥመድ ተላቀው ወደ ኅሊናቸው ሊመለሱ ይችሉ ይሆናል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።