1በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሆነው የሕይወት ተስፋ፣ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ የሆነው፣ጳውሎስ
2ለተወደደው ልጄ፣ ለጢሞቴዎስ፣ ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእግዚአብሔር አባታችን፣ ቤታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ለአንተ ይሁን፡፡
3ሌትና ቀን በጸሎቴ ስለማስብህ፣ እንደ አባቶቼ አድርጌ በንጹህ ኅሊና የማገለግለወን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፣
4እምባህን እያሰብኩ በደስታ እሞላ ዘንድ ላይህ እናፍቃለሁ፤
5ያለህንም እውነተኛ እምነት አስባለሁ፣ ይህም እምነት አስቀድሞ በአያትህ በሎይድ በእናትህም በኤውንቄ ነበረባቸው፣ በአንተም እንዳለ ተረድቼአለሁ፡፡
6እግዚአብሔር የሰጠህን በአንተ ያለውን ስጦታ እንድታነሣሣ ስእጆቼን በመጫኔ አሳስብሃለሁ፡፡
7እግዚአብሔር የኃይል እና የፍቅር ራስንም የመግዛት እንጂ፣ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም፡፡
8በጌታ እና የእርሱ እስረኛ በሆንኩት በእኔም ምሥክርነት አትፈር፣ እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል መከራን ተቀበል፡፡
9ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ያዳነን፣ በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነው፤ ይህም የሆነው በራሱ እቅድና በጸጋወ ነው እጂ በእኛ ሥራ አይደለም፡፡
10አሁን ግን የእግዚአብሔር ማዳን፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ እና፣ ሞትን በማጥፋቱ እና የዘላለምን ሕይወት ወደ ብርሃን በማውጣቱ በወንጌሉ ተገልጦአል፣
11ይህንንም ወንጌል ለማብሰር እኔ ሐዋርያ እና አስተማሪ ሆኜ ተሹሜአለሁ፡፡
12ስለዚህ ምክንያት እኔ መከራ እቀበላለሁ፣ ነገር ግን አላፍርበትም፣ ያመንኩትን አውቃለሁና፤ የሰጠሁትን አደራ እስከዚያች ቀን ድረስ እንደሚጠብቅ ተረድቼአለሁ፡፡
13ከእኔ የሰማኸውን ጤናማ ቃል፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር በምሳሌነት ጠብቅ፡፡
14በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አድርገህ በእግዚአበሔር የተሰጠህንም አደራ ጠብቅ፡፡
15በእስያ ያሉት ሁሉ ከእኔ ፈቀቅ እንዳሉ ታውቃለህ፣ ከእነዚህም ጊሊጎስ እና ሄርዋጌኔስ ይገኙባቸዋል፡፡
16ጌታ ለሄኔሲፎሩ ቤተ ሰብ ምሕረትን ይስጣቸው፣ ብዙ ጊዜ አሳርፎኛልና፣ በሰንሰለቴም አላፈረበትም፡፡
17ነገር ግን በሮም በነበረ ጊዜ፣ በብርቱ ፈልጎ አገኘኝ፣
18ጌታ በዚያች ቀን ምሕረትን እንዲያገኝ ይስጠው፣ በኤፌሶን ምንያህል እንደረዳኝ አንተ በደኅና ታውቃለህ፡፡