መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

2ኛ ተሰሎንቄ 2

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ወንድሞች ሆይ፣ አሁን የምንለምናችሁ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና ወደ እርሱ ስለመሰብሰባችን ነው፣
2ከእኛ የሆነ በሚመስል በመንፈስ፣ በቃል ወይም በደብዳቤ እነሆ የጌታ ቀን ሆኗል ብላችሁ በማመን በቀላሉ በአዕምሮአችሁ እንዳትናወጡ ወይም እንዳትደነግጡ እንለምናችኋለን።
3በየትኛውም መንገድ ማንም አያስታችሁ። የመጨረሻው ክህደት ሳይመጣና የአመጽ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ ያ ቀን አይመጣምና።
4የሚቃወመውና አምላክ ከተባለው ወይም ከሚመለከው ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ የሚያደርገው እርሱ ነው፣ በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እስኪቀመጥም ድረስ ራሱን እንደ አምላክ ያስተዋውቃል።
5ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ስለእነዚህ ነገሮች እንደነገርኳችሁ ትዝ አይላችሁምን?
6በትክክለኛው ጊዜ ብቻ ይገለጥ ዘንድ አሁን የሚከለክለው ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ።
7የአመጽ ምስጢር በሥራ ላይ ነው፣ ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ አሁን የሚከለክለው አንድ ብቻ አለ።
8ከዚያም ጌታ ኢየሱስ በአፉ እስትንፋስ የሚገድለውና በመምጣቱ መገለጥ የሚያጠፋው የአመጽ ሰው ይገለጣል።
9የአመጽ ሰው አመጣጥ እንደ ሰይጣን አሰራር በኀይል ሁሉ፣ በምልክቶችና በሐሰተኛ ድንቆች፣
10ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉት በአመጽ ማታለል ሁሉ ነው።
11በዚህ ምክንያት ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል፣
12ይኸውም እነዚያ እውነትን ያላመኑ ነገር ግን በአመጻ የተደሰቱ ሁሉ ይፈረድባቸው ዘንድ ነው።
13ነገር ግን ስለ እናንተ በጌታ ስለተወደዳችሁት ወንድሞች ለእግዚአብሔር ሁልጊዜ ምስጋና ልናቀርብ ይገባናል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ መቀደስና እውነትን በማመን ለድነት እንደ በኩራት መርጧችኋልና፣
14የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር እንድትካፈሉ በወንጌላችን ጠራችሁ።
15እንግዲያውስ ወንድሞች ሆይ፣ ጸንታችሁ ቁሙ፣ በቃልም ሆነ ወይም በደብዳቤአችን የተማራችኋቸውን ልማዶች አጥብቃችሁ ያዙ።
16አሁን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱና የወደደን፣ የዘላለምን መጽናናትና በጸጋው ተስፋ የምናደርግበትን መልካሙን መታመን የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን፣
17በቃልና በመልካም ሥራ ሁሉ ልባችሁን ያጽናኑት፣ ያበርቷችሁም።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።