መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

2ኛ ተሰሎንቄ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከጳውሎስ፣ ስልዋኖስና ጢሞቴዎስ በእግዚአብሔር በአባታችን በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ላሉ ለተሰሎንቄ ሰዎች ቤተክርስቲያን።
2ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
3ወንድሞች ሆይ፣ ስለ እናንተ ሁልጊዜ ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ አለብን፣ ይህ ተገቢ ነውና፣ ምክንያቱም እምነታችሁ እጅግ እያደገ ነውና፣ የእያንዳንዳችሁ ፍቅርም ለሌሎች የሚተርፍ ሆኗል።
4በመሆኑም በስደቶቻችሁና በመከራዎቻችሁ ሁሉ ስለ መጽናታችሁ ስለ ትዕግስታችሁና እምነታችሁ እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር አብያተክርስቲያናት መካከል በልበ ሙሉነት እንመሰክራለን።
5እናንተ ደግሞ መከራን ለምትቀበሉለት ለእግዚአብሔር መንግሥት ብቁ ሆናችሁ ትቆጠሩ ዘንድ ይህ የእግዚአብሔር ፍርድ ጻድቅ የመሆኑ ግልጽ ምልክት ነው።
6መከራን ለሚያመጡባችሁ መከራን ይመልስላቸው ዘንድ ይህ በእግዚብሔር ፊት ቅን ፍርድ ነው፣
7ጌታችን ኢየሱስ ከኀይሉ መላዕክት ጋር ከሰማይ በሚገለጥበት ጊዜ ከእኛ ጋር መከራን ለተቀበላችሁት ደግሞ እረፍትን ይሰጣችኋል።
8እግዚአብሔርን የማያውቁትንና ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ግን በሚነድ እሳት ይበቀላቸዋል።
9ከጌታ ሀልዎትና ከኀይሉ ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት እየተቀጡ ይሰቃያሉ፣
10እርሱ በቅዱሳኑ ሊከበር በሚመጣበት በዚያን ቀን፣ ምስክርነታችንን አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ይገረምባቸዋል።
11በዚህ ምክንያት እኛ ደግሞ አምላካችን ለጥሪአችሁ የተገባችሁ አድርጎ ይቆጥራችሁና መልካሙን ምኞታችሁንና ማናቸውንም የእምነት ሥራ በኀይል ይፈጽምላችሁ ዘንድ ባለማቋረጥ እንጸልይላችኋለን።
12ይህም በአምላካችንና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ምክንያት የጌታችን የኢየሱስ ስም በእናንተ እንዲከበርና እናንተም በእርሱ ትከብሩ ዘንድ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።