መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

2ኛ ሳሙኤል 21

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በዳዊት ዘመን ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ራብ ሆነ፣ ዳዊትም የእግዚአብሔርን ፊት ፈለገ፡፡ስለዚህ እግዚአብሔር፣ “ሳዖልና ገዳይ ቤተሰቡ ገባዖናውያንን እንዲሞቱ ስላደረገ ይህ ረሃብ በአንተ ላይ ነው” አለ፡፡
2እንግዲህ ገባዖናውያን ከአሞራውያን የተረፉ እንጂ የእስራኤል ሕዝብ ወገን አልነበሩም፡፡ የእስራኤል ሕዝብ እንደማይገድሏቸው ምለውላቸው ነበር፣ ሳዖል ግን ለእስራኤልና ለይሁዳ ሕዝብ ከነበረው ቅናት የተነሣ እንዲሁ ሁሉንም የመግደል ሙከራ አድርጎ ነበር፡፡
3ስለዚህ ዳዊት ገባዖናውያንን በአንድነት ጠራቸውና፣ “ምን ላደርግላችሁ? የእርሱን በጎነትና ተስፋ ቃሉን የሚወርሱትን የእግዚአብሔርን ሕዝብ ትባርኩ ዘንድ ስርየትን እንዴት ማድረግ እችላለሁ?” አላቸው፡፡
4ገባዖናውያንም፣ “በእኛና በሳዖል ወይም በቤተሰቡ መካከል ያለው የብርና የወርቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ በእስራኤልም ውስጥ ማንም ሰው እንየዲገደል የምናደርግ እኛ አይደለንም፡፡” ብለው መለሱለት፡፡ ዳዊትም፣ “የምትጠይቁትን ማንኛውንም ነገር ቢሆን እኔ ያንን አደርግላችኋለሁ” አላቸው፡፡
5እነርሱም ለንጉሡ፣ “እንድንጠፋና በእስራኤል ክልል ውስጥ ምንም ስፍራ እንዳይኖረን ሁላችንንም ለመግደል ሙከራ ካደረገውና በእኛ ላይ ሤራ ካውጠነጠነው
6ከእርሱ ዝርያዎች ሰባት ሰዎች ለእኛ ተላልፈው ይሰጡን እኛም በእግዚአብሔር በተመረጠው በሳዖል አገር በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንሰቅላቸዋለን” አሉት፡፡ ስለዚህ ንጉሡ፣ “እነርሱን እሰጣችኋለሁ” አላቸው፡፡
7ንጉሡ ግን በእርሱና በሳዖል ልጅ በዮናታን ስለነበረው የእግዚአብሔር መሐላ የሳዖልን ልጅ የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን አዳነው፡፡
8ነገር ግን ንጉሡ የኢዩሄል ልጅ ሪጽፋ ለሳዖል የወለደቻቸውን ሁለቱን ወንዶች ልጆች ሄርሞንንና ሜምፊቦስቴን ወሰዳቸው፣ በተጨማሪም ዳዊት የሳዖል ልጅ ሜልኮል ለመሓላታዊው ለቤርዜሊ ልጅ ለኤስድሪኤል የወለደቻቸውን አምስት ወንዶች ልጆች ወሰዳቸው፣
9በገባዖናውያንም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም በተራራው ላይ በእግዚአብሔር ፊት ሰቀሏቸው፣ ሰባቱም አንድ ላይ ሞቱ፡፡ የተገደሉት በመከራ ወቅት፣ የገብስ መከር በሚሰበሰብባቸው የመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናት ነበረ፡፡
10ከዚያ በኋላ የኢዩሄል ልጅ ሪጽፋ ከመከር መሰብሰብ ጊዜ ጀምሮ ዝናብ በእነርሱ ላይ እስኪወርድባቸው ድረስ በአስከሬኖቹ አጠገብ ባለው ተራራ ለራሷ ማቅ ወስዳ ዘረጋች፡፡ የሰማይ ወፎች በቀን፣ የዱር አራዊት በማታ እንዲነኳቸው አልፈቀደችም፡፡
11የሳዖል ቁባት የኢዩሄል ልጅ ሪጽፋ ያደረገችው ለዳዊት ተነገረው፡፡
12ስለዚህ የሳዖልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት ሳዖልን በጊልቦዓ ከገደሉት በኋላ ሰቅለውት ከነበረበት ከቤትሻን አደባባይ ከሰረቁት ከኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ዘንድ ዳዊት ሄዶ አመጣ፡፡
13ዳዊት ከዚያ ስፍራ የሳዖልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት እንዲሁም በዚያ የተሰቀሉትን የሰባት ሰዎች አጥንትም ሰብስቦ ወሰደ፡፡
14የሳዖልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት በብንያም አገር በጼላ በአባቱ በቂስ መቃብር ቀበሩአቸው፡፡ ንጉሡም ያዘዘውን ነገር ሁሉ አከናወኑ፡፡ ከዚያ በኋላ ለምድሪቱ የተደረገውን ጸሎት እግዚአብሔር መለሰ፡፡
15ከዚያ በኋላ ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር እንደገና ውጊያ ገጠሙ፡፡ ስለዚህ ዳዊት ከሠራዊቱ ጋር ወርዶ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፡፡ ዳዊት በጦርነቱ የሰውነት መዛል አጋጠመው፡፡
16የኃላኑ ዝርያ የነበረውና የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝነው እንዲሁም አዲስ ሰይፍ የታጠቀው ይሽቢብኖብ ዳዊትን ለመግደል አቀደ፡፡
17ነገር ግን የጽሩይ ልጅ አቢሳ ፍልስጥኤማዊውን ወግቶ በመግደል ዳዊትንም ታደገው፡፡ ከዚያ በኋላም የዳዊት ሰዎች፣ “የእስራኤል መብራት እንዳታጠፋ ከእንግዲህ አንተ ከእኛ ጋር መውጣት የለብህም” ብለው ማሉለት፡፡
18ከዚህ በኋላ ጎብ በተባለ ስፍራ የራፋይም ዝርያ የነበረው ኩስታዊው ሴቦካይ ሳፋንን የገደለበት ጦርነት ከፍልስጥኤማውያን ጋር እንደገና ተደረገ፡፡
19ጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በተደረገ ጦርነት የቤተልሔሙ የየዓሬዓርጊም ልጅ ኤልያናን የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን የጌት ሰው ጎልያድን ገደለ፡፡
20ጋዛ ላይ በተደረገ ሌላ ጦርነት በእጆቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች በእግሮቹም ላይ ስድስት ጣቶች ባጠቃላይ ሃያ አራት ጣቶች የነበሩት ታላቅ ቁመት የነበረው ሰው ነበር፡፡ እርሱም የራፋይም ዝርያ ነበር፡፡
21እርሱም በእስራኤል ላይ ባፌዘ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሣማ ልጅ ዮናታን ገደለው፡፡
22እነዚህ የጋዛዋ ራፋይም ዝርያዎች ነበሩ፣ እነርሱም በዳዊት እጅና በወታደሮቹ እጅ ተገደሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።