1በዚህ ጊዜ በዚሁ ስፍራ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሳቤዔ የተባለ አንድ ችግር ፈጣሪ ብንያማዊ ነበር፡፡ እርሱም መለከት ነፍቶ፣ “እኛ ከዳዊት ጋር ድርሻ የለንም፣ ከእሴይ ልጅም ጋር ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፣ እያንዳንዱ ሰው ወደ ቤቱ ይመለስ” አለ፡፡
2ስለዚህ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ዳዊትን ከድተው የቢክሪን ልጅ ሳቤዔን ተከተሉ፡፡ የይሁዳ ሰዎች ግን ከዮርዳኖስ አንስተው እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ንጉሣቸውን አጥብቀው ተከተሉ፡፡
3ዳዊት በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መንግሥቱ በመጣ ጊዜ ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁ ትቶአቸው የነበሩትን ዐሥሩን ቁባቶች በአንድ ቤት ውስጥ አስገብቷቸው በአንድ ዘበኛ እንዲጠበቁ አደረገ፡፡ የሚያስፈልጋቸውን አቀረበላቸው፣ ነገር ግን ከዚያ በኋላ ከእነርሱ ጋር አልተኛም፡፡
4እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ ተዘግቶባቸው እንደ መበለት ይኖሩ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ንጉሡ ለአሜሳይ፣ “በሦስት ቀን ውስጥ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እንዲሰባሰቡ ጥራቸው፣ አንተም እዚህ መገኘት አለብህ” አለው፡፡
5ስለዚህ አሜሳይ የይሁዳ ሰዎች እንዲሰባሰቡ ለመጥራት ሄደ፣ ነገር ግን ንጉሡ ካዘዘው ቀነ-ገደብ በላይ ቆየ፡፡
6ስለዚህ ዳዊት ለአቢሳ፣ “አሁን የቤክሪ ልጅ ሳቤዔ አቤሴሎም ካደረሰው ይልቅ የባሰ ጉዳት ያደርስብናል፡፡ የጌታህን አገልጋዮች ወታደሮቼን ያዝና አሳደው፣ አለበለዚያ የተመሸጉ ከተሞችን ያገኝና ከዓይናችን ይሰወራል፡፡” አለው፡፡
7በዚያን ጊዜ የኢዮአብ ሰዎች ከከሊታውያን ከፈሊታውያን እንዲሁም ከሌሎች ኃያላን ጦረኞች ጋር ተከትለውት ወጡ፡፡ የቤክሪን ልጅ ሳቤዔን ያሳድዱ ዘንድ ከኢየሩሳሌም ወጡ፡፡
8ገባዖን ከሚገኘው ታላቅ ዐለት በደረሱ ጊዜ አሜሳይ ሊገናኛቸው መጣ፣ ኢዮአብ በሰገባው ውስጥ የገባ ሰይፍ በወገቡ የታጠቀበትን ቀበቶ የሚያካትት የጦር ሜዳ ልብሱን ለብሶ ነበር፡፡ ወደፊት እየተራመደ ሳለም ሰይፉ ወደቀ፡፡
9ኢዮአብም አሜሳይን፣ “ወንድሜ ሆይ፣ ደህና ነህን?” አለው፡፡ ኢዮአብም አሜሳይን እንደሚያፈቅረው አድርጎ ለመሳም ጢሙን ይዞ ሳበው፡፡
10አሜሳይ ኢዮአብ በግራ እጁ ይዞት የነበረውን ጩቤ አላስተዋለም፡፡ ኢዮአብ አሜሳይን ሆዱን ወጋው፣ ሆድ-ዕቃውም በምድር ላይ ተዘረገፈ፡፡ ኢዮአብ እንደገና አልወጋውም፣ አሜሳይም ሞተ፡፡ ስለዚህ ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ የቤክሪን ልጅ ሳቤዔን አሳደዱ፡፡
11ከዚያ በኋላ ከኢዮአብ ሰዎች አንዱ በአሜሳይ አጠገብ ቆመና፣ “ኢዮአብን የሚደግፍና የዳዊት የሆነ ኢዮአብን ይከተል” አለ፡፡
12በዚህን ጊዜ አሜሳይ በደም ተጨማልቆ በመንገዱ መካከል ወድቆ ነበር፡፡ ሰዎች ሁሉ ቆመው እንደቀሩ ሰውዬው ተመልክቶ የአሜሳይን ሬሳ ከመንገድ ጎትቶ ወደ እርሻ ውስጥ አስገባው፡፡ ወደ አጠገቡ የደረሰ ማንኛውም ሰው ቆሞ ይቀር እንደነበረ ተመልክቶ ልብስ በላዩ ጣል አደረገበት፡፡
13አሜሳይ ከመንገድ ዞር ከተደረገ በኋላ የቤክሪ ልጅ ሳቤዔን ለማሳደድ ሰዎች ሁሉ ኢዮአብን ተከተሉ፡፡
14ሳቤዔአም በእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል አልፎ ወደ አቤል ቤትማዓካና ተሰባስበው ሳቤዔን ያሳድዱ ወደነበሩት ወደ መላው የቤክሪያውያን ግዛት መጣ፡፡
15ደረሱበትና አቤል ቤትመዓካ ላይ ከበቡት፡፡ በከተማይቱም ላይ ግድግዳውን አስጠግተው የአፈር ድልድል ሠሩበት፡፡ ከኢዮአብ ጋር የነበረውም ሠራዊት ግንቡን ለመናድ ደበደበው፡፡
16ከዚያ በኋላ አንድ ብልህ ሴት ከከተማ ውስጥ ተጣራችና፣ “ስማኝ፣ እባክህን ስማኝ ኢዮአብ፤ እንዳነጋግርህ ወደዚህ ጠጋ በል” አለችው፡፡
17ስለዚህ ኢዮአብ ጠጋ አለ፣ ሴቲቱም፣ “አንተ ኢዮአብ ነህን?” አለችው፡፡ እርሱም፣ “አዎን፣ ነኝ” አለ፡፡ እርሷም ከዚያ በኋላ ለእርሱ፣ “የባሪያህን ቃል ስማ” አለችው፡፡ እርሱም፣ “እየሰማሁ ነው” ብሎ መለሰላት፡፡
18ከዚያ በኋላም እርሷ፣ “በቀደሙት ጊዜያት ‘በእርግጥ ምክርን ከአቤል ጠይቅ ምክሩም ችግሮችን ይፈታል’ ይሉ ነበር፡፡
19እኛ በእስራኤል ውስጥ እጅግ ሰላማዊና ታማኝ ከሆኑት ከተሞች አንዱ ነን፡፡ በእስራኤል ውስጥ እናት የሆነችውን ከተማ ለማጥፋት እየሞከርክ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ርስት ለምን ለመዋጥ ትፈልጋለህ?”
20ስለዚህ ኢዮአብ፣ “መዋጥ ወይም ማጥፋት ከእኔ የራቀ ይሁን፣
21ያ እውነት አይደለም፡፡ ነገር ግን ከኮረብታማው ከኤፍሬም አገር የሆነ ሳቤዔ የተባለ የቤክሪ ልጅ እጁን በንጉሡ ላይ ፣ በዳዊት ላይ አንስቷል፤ እርሱን ብቻ አሳልፋችሁ ስጡኝ፣ ከተማውን ለቅቄ እወጣለሁ” ብሎ መለሰላት፡፡ ሴቲቱም ለኢዮአብ፣ “ራሱ በቅጥሩ ላይ ይወረወርልሃል” አለችው፡፡
22ከዚያም ሴቲቱ በጥበብዋ ወደ ሕዝቡ ሁሉ ሄደች፡፡ የቤክሪን ልጅ የሳቤዔን ራስ ቆርጠው በቅጥሩ ላይ ለኢዮአብ ወረወሩለት፡፡ እርሱም ቀንደ-መለከቱን ነፋ፣ የኢዮአብም ሰዎች ከተማይቱን ለቀው እያንዳንዱ ሰው ወደየቤቱ ሄደ፡፡
23በዚህን ጊዜ ኢዮአብ በሠራዊቱ ሁሉ ላይ የበላይ ነበር፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ደግሞ በከሊታውያንና በፈሊያታውያን ላይ አለቃ ሆነ፡፡
24አዶኒራም በግዳጅ ሥራ ላይ ለተሰማሩት አለቃ ሆነ፣ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ ደግሞ ታሪክ ጸሐፊ ሆነ፤
25ሱሳ ጸሐፊ፣ ሳዶቅና አብያታር ካህናት ነበሩ፤
26እንዲሁም የኢያዕር ሰው ዒራስ የዳዊት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነ፡፡