1ለቅዱሳን ስለ ሚሆነው አግልግሎት ለእናንተ ልጽፍላችሁ አያስፈልገኝም ።
2ለመቄዶንያ ሰዎች ስለተመካሁት በውስጣችሁ ስላለው መሻት አውቃለው። በአካዶያ የሚነግሩት ካለፈው ዓመት ጀምሮ መዘጋጀትቱን ነገርኋቸው። የእናንተ ቅንዓት ብዙዎቻቸውን ለስራ አነሳስቷል።
3እንግዲህ የተዘጋጃችሁ ትሆናላችሁ እንዳልኩት የተዘጋጃችሁ ትሆኑ ዘንድ፣ ስለ እናንተ መመካታችን ከንቱ እንዳይሆን ወድሞችን ልኬአለው።
4ምናልባት አንዳቸው ከ እኔ ጋር ከሜቄዶንያ በመጡ፣ሳትዘጋጁ ቢያገኟችሁ ሁላችንም ሀፍረት ይሰማናል ነገር ግን በእናንተ ስለምተማመን ፣ ስለ እናንተ የምለው ምንም የለኝም።
5ስለዚህ ወደ እናንተ እንዲመጡና እናንተ ተስፋ ለሰጣችሁት ስጦታ በቅድሚያ ዝግጅት እንዲያደርጉ ወንድሞችን መለመን አስፈላጊ እንደሆነ አሰብሁ። ይህም እንድትሰጡ ስለ ተገደዳችሁ ሳይሆን በነጻ እንደተሰጠ ስጦታ ዝግጁ ይሆን ዘንድ ነው።
6ፍሬ ነገሩ ይህ ነው ፦ በጥቂት የሚዘራ በጥቂቱ ያጭዳል ፣ አትረፍርፎ የሚዘራ አትረፍርፎ ያጭዳል።
7እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ ስትሰጡ በሐዘን ወይም በግድ አይደለም።
8እግኢአብሔር ሁልጎዜ በነገር ሁሉ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝቷችሁ በብጎ ስራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።
9እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ «ሀብቱን በተነ ፣ለድሆችም አከፋፈለ።»
10ለዘሪን ዘርን ለምግብ እንጀራን የሚሰጥ ፣የሚዘራ ዘርን ደግሞ ይሰጣል ያበዛውማል፣ ምርት ይጨምራል።
11ለጋሶች እንድትሆኑ በሁሉም ረገድ መበልጸግ ትላላችሁ፣ ይህም በእኛ በኩል ለእግኢአብሔር ምስጋና ምክንያት ይሆናል።
12ይህ የመስጠት አገልግሎት ለቅዱሳን ይሚያስፈልጋቸውን ሁሉ የሚሰጥ ብቻ አይደለምና፣ ነገር ግን ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ብዙ ምስጋና ደግሞ ይበዛል።
13በዚህ አገልግሎት ተፈትናችሁ አልፋችኋል ደግሞም በክርስቶስ ወንጌል ምስክርነት በመታዘዛችሁ ፣እንዲሁም ለእነርሱና ለሁሉ ባደረጋችሁት የስጦታችሁ ልግስና እግዚአብሔርን ታከብራላችሁ።
14በእናንተ ላይ ካለው እጅግ ታላቅ የእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ስለ እናንተ ሲጸልዩ ይናፍቁአችኋል።
15ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!