1ወንድሞችና እህቶች ሆይ ለመቄዶንያ ለአብያተ ክርስቲያናት ስለ ተሰጠው የእግዚአብሔር ጸጋ እንድታውቁ እንፈልጋለን
2እጅግ የሚፈትናቸው መከራ በደረሰባቸው ጊዜ የደስታቸው መብዛትና የደህንነታቸው አስከፊነት የልግስናቸውን መትረፍረፍ አብዝቷል።
3የሚቻላቸውን ያህል ከሚቻላቸውም እንደ ሰጡ እኔ እመሰክርላቸዋለው። በፈቃዳቸውም ለቅዱሳን በሚሰጠው በዚህ አገልግሎት የመሳተፍ ዕድል ይኖራቸው ዘንድ
4እኛን በብዙ ልመና ለመኑን።
5ይህም የሆነው እኛ እንደጠበቅነው አይደለም ነገር ግን በመጀመሪያ ራሳቸውን በጌታ ከዚያም በእግዘአብሔር ፈቃድ ለእኛ ሰጡ።
6ስለዚህ አስቀድሞ ከእናንተ ጋር የጀመረውን ተግባር በእናንተ ዘንድ ያለውን ይህን የልግስና ስራ ከፍጻሜ እንዲደርስ ቲቶን ግድ ብለነው ነበር።
7ነገር ግን እናንተ በሁሉም ነገር በእምነት፥ በንግግር ፣በዕውቀት በትጋት ሁሉ እንዲሁም ለእኛ ባላችሁ ፍቅር እንደሚልቁ በዚህ በበጎ ስራ ደግሞ የምትልቁ ሁኑ።
8ከሌሎች ሰዎች ትጋት ጋር በማወዳደር የፍቅራችሁን ቅንነት ለማረጋገጥ እንጂ ይህንን እንደ ትዕዛዝ አልልም እናንተ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁና።
9በእርሱ ድኽነት እናንተ ባለጠጎች ትሆኑ ዘንድ ፥ እርሱ ባለ ጠጋ ቢሆንም እንኳ ስለ እናንተ ደኸየ።
10በዚህ ጉዳይ እናንተን ስለሚጠቅማችሁ ነገር ምክር እለግሳችኋለው። ከአንድ ዓመት በፊት አንድን ነገር ለማድረግ መጀመር ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ልታደርጉት መሻት በውስጣችሁ ነበር።
11አሁን ያንኑ ማድረጋችሁን ፈጽሙ። እንግዲህ ልክ በዚያን ጊዜ ልታደርጉት ጉጉትና ጠንካራ ፍላጎት እንደ ነበራችሁ፣ወደ ፍጻሜ ልታመጡት ደግሞ ትችላላችሁ።
12ይህን ስራ ለመስራት ጉጉት ካለ፣ አንድ ሰው በሌለው ሳይሆን ባለው ነገር ላይ ተመስርቶ ሲሰራ መልካምና ተቀባይነት ያለው ነው።
13ይህ ተግባር ሚዛናዊነት እንዲኖር ነው እንጂ ሌሎች እንዲቀልላቸው እናንተም ሸክም እንዲበዛላችሁ አይደለም።
14አሁን ያለው የእናንተ መትረፍ ለእነርሱ የሚያስፈልጋቸውን ይሞላል። ይህም ደግሞ ሚዛናዊነት ይኖር ዘንድ የእነርሱ መትረፍረፍ የእናንተ ፍላጎት ደግሞ እንዲሞላ ነው።
15እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ፦ «ብዙ ያለው ምንም አልተረፈውም ፣ጥቂት ያለው ግን ምንም አልጎደለውም።»
16ነገር ግን እኔ ለእናንተ ያለኝን ቅን ሃሳብ በቲቶ ልብ ያኖረው እግዚአብሔር ይመስገን።
17እርሱ ልመናችንን መቀበል ብቻ ሳይሆን ፣ ትጋትን በማሳየት በራሱ ፈቃድ ወደ እናንተ መጥቷልና።
18ከእርሱ ጋርም ወንጌልን በማወጅ ስራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም ልከናል።
19ይህ ብቻ አይደለም ነገር ግን ለራሱ ለጌታ ክብርና እኛ ለመረዳት ያለንን ጉጉት ለመግለጥ ይህን የጸጋ ስራ እንዲያከናውን አብሮን ይጓዝ ዘንድ አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ መርጠውት ነበር።
20ስለምንሰበስበው ስለዚህ የልግስና ስጦታ ማንም ትችት ለማቅረብ ምክንያት እንዳያገኝ እንጠነቀቃለን።
21በጌታ ፊት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በሰዎች ፊት ደግሞ የከበረውን ነገር ለማድረግ እንተጋለን።
22ብዙ ጊዜ ፈትነን በበርካታ ተግባራት ተነሳሽነት ያለው ሆኖ ያገኘውን ፣አሁን ግን በእናንተ ላይ ትልቅ መታመን ምክንያት የበለጠ ትጋት የሚያሳየው ሌላ ወንድም ከእነርሱ ጋር እንልካለን።
23ቲቶን በሚመለከት ግን ስለ እናንተ ከእኔ ጋር የሚሰራ አጋሬ ነው። ወንድሞቻችንን በሚመለከት አብያተ ክርስቲያናት የላኳቸው የክርስቶስ ክብር ናቸው።
24ስለዚህ ፍቅራችንን ፣ በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ዘንድም ስለ እናንተ ለምን እንደ ተመካን ግለጡላቸው።