1እኔ ራሴ ጳውሎስ ፣ በፊታችሁ ትሁት የሆንሁ በክርስቶስ ገርነትና የዋህነት እለምናችኃለሁ።
2እንደ ስጋ ፈቃድ እንደምንኖር የሚያስቡትን በምቃወምበት ጊዜ ፣ ከእናንተ ጋር ሳለሁ መሆን እንደሚገባኝ በራስ በመተማመን የምደፍር መሆን የለብኝም ብዬ እለምናችኃለው ።
3ምንም እንኳ በስጋ የምንመላለስ ብንሆን፣ እንደ ስጋ አንዋጋም።
4የምንዋጋባቸው የጦር መሳሪያዎች ሥጋዊ አይደሉምና ይልቁንም ምሽጎችን ለመስበር መለኮታዊ ኃይል አለቸው ፥ አሳሳች የሆኑ ክርክሮችንም ያፈርሳሉ።
5ደግሞም በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ የሚነሳውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ፥ እንዲሁም ለክርስቶስ ለመታዘዝ ሀሳብን ሁሉ እንማርካለን።
6መታዘዛችሁም በተፈጸመ ጊዜ ፣ ይለመታዘዝን ተግባር ሁሉ ለመቅጣት እንዘጋጃለን።
7በግልጽ ከፊታችን ያለውን ተመልከቱ ፥ ማንም የክርስቶስ እንደሆነ ቢያምን ልክ እርሱ የክርስቶስ እንደሆነ እኛ ደግሞ እንዲሁ መሆናችንን ራሱ ያሰበው።
8ሊያንጻችሁ እንጂ ሊያጠፋችሁ የይደለ ጌት ኣስለ ሰለ ሰጠው ስልጣናችን ጥቂት አብዝቼ ብመካም እንኳ፥ አላፍርም።
9በመልዕክቶቼም ላስደነግጣችሁ አልፈልግም።
10አንዳንድ ሰዎች ፥«መልእቶቹ ጠንከር ያሉና ኃይለኛ ናቸው፥ ነገር ግን በአካል ደካማ ነው፥ ንግግሩም ሊሰማ የሚገባ አይደለም»ይሉናል።
11እንደነዚህ ያሉ ሰዎችን ስንርቅ በመልዕክት የምንለው፥እዚያ ስንሆን ከምናደርገው ጋር አንድ መሆኑን ይረዱ።
12ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ጋር ራሳችንን እስከ ማስተያየት ወይም እስከ ማወዳደር ድረስ አንሔድም። ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከሌላ ጋር ሲመዝኑና ራሳቸውን እርስ በእርስ ሲያወዳድሩ ፥ ማስተዋል ተላቸውም።
13ይሁን እንጂ እኛ ከልክ በላይ አንመካም፥ ነገር ግን ወደ እናንተ እንኳ እስክንደርስ እግዚአብሔር በወሰነልን ስራ እንሆናለን።
14ወድ እናንተ ስንደርስ ከመጠን አላለፍንምንና በክርስቶስ ወንጌል ወደእናንተ ለመድረስ የመጀመሪያዎች ነበርን።
15በሌሎች ድካም ከልክ ያለፈ አንመካም ፥ ነገር ግን ከእናንተ አካባቢ አልፎ እንኳ
16ወንጌልን እንሰብክ ዘንድ እምነታችሁ ሲያድግ ስራችን እጅግ እንደሚስፋፋ ተስፋ እናደርጋለን ። በሌላ ስፍራ እየተሰራ ስላለው ሥራ አንመካም።
17«ነገር ግን የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ።»
18ጌታ የሚያመሰግነው እንጂ፣ ራሱን የሚያመሰግን ተፈትኖ የሚወጣ አይደለምና።