መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

2ኛ ቆሮንቶስ 5

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ምድራዊው መኖሪያችን ቢፈርስ እንኳ በሰማይ በሰው እጅ ያልተሰራ ዘላለማዊ ቤት በእግዚአብሔር እንደተሰራልን እናውቃለን።
2ድንኳን ውስጥ ሆነን እንቃትታለን፥ሰማያዊ መኖሪያችንንም ልንለብስ እንናፍቃለን።
3ምክንያቱም ያን ለብሰን ስንገኝ ራቁታችንን ሆነን አንገኝም ።
4በርግጥ በዚህ ድንኳን ውስጥ ሆነን ከብዶን እንቃትታለን፤ምክንያቱ ደግሞ ሟች የሆነው ሰውነት በህይወት መዋጥ ስላለበት እኛም ለብሰን እንጂ ራቁታችንን መሆን አንፈልግም።
5ወደ ፊት ሊመጣ ላለው የመንፈሱን ዋስትና የሰጠን ለዚህም ያዘጋጀን እግዚአብሔር ነው።
6እንግዲህ በሰውነታችን በዚህ ምድር በምንኖርበት ጊዜ በሰማይ ካለው ጌታ ርቀን እንዳለን ይህን እርግጠኛ ሁኑ
7ምክንያቱም በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና።
8ስለዚህ ይህ ድፍረት አለን፤ከሰውነታችን ተለይተን ከጌታ ጋር በሰማይ ቤት መሆንን እንመርጣለን።
9ስለሆነም በምድርም ብንሆን ወይም ከምድር ብንለይ ግባችን እርሱን ማስደሰት ነው።
10እያንዳንዳችን በሰውነታችን በዚህ ምድር ላይ የሰራነውን መልካምም ሆነ ክፉ እንቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት መቅረባችን ግድ ነው።
11እንግዲህ ጌታን መፍራት ምን ማለት እንደሆን ስለምናውቅ ሰዎችን ግድ እንላለን። ማንነታችን በእግዚአብሔር ፊት የተገለጠ ስለሆነ ለናንተም ህሊና ግልፅ እንደሚሆን ተስፋ አለኝ።
12ራሳችንን ደግመን እንድታወድሱን አናቀርብላችሁም፥ ሆኖም በልብ ሳይሆን በውጫዊው መልክ ለሚመኩ መልስ መስጠት እንዲቻላችሁ እኛን ምክንያት አድርጋችሁ እንድትመኩ እናስታውቃችኋለን።
13እንደ እብድ ቢያረገን፥ ለእግዚአብሔር ነው፤እንደ ባለአዕምሮ ብንሆን ደግሞ ለእናንተ ስንል ነው።
14የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል፥ በዚህ ነገር እርግጠኞች ነን፡አንዱ ሰው ስለሁሉ ሞተ፥ ስለሆነም ሁሉም ሞቱ ማለት ነው።
15በህይወት ያሉትም ስለእነርሱ ለሞተውና ለተነሳው እንጂ ለራሳቸው እንዳይኖሩ ክርስቶስ ስለሁሉ ሞተ።
16ስለዚህም ምክንያት ክርስቶስን ከዚህ ቀደም በሰዋዊ መንገድ አይተነው ቢሆን፥ካሁን ጀምሮ ማንንም በሰዋዊ መስፈርት አንፈርድም። በማንም ላይ ከዚህ በኋል በዚህ መንገድ አንፈርድም።
17ስለሆነም ማንም በክርስቶስ ውስጥ ቢሆን እርሱ አዲስ ፍጥረት ነው። አሮጌ ነገሮች አልፈዋል። ተመልከቱ፥ ሁሉ አዲስ ሆኗል።
18እነዚህ ነገሮች ሁሉ የሆኑት እኛን በክርስቶስ ከራሱ ጋር ባስታረቀንና የዕርቅ አገልግሎት በሰጠን በእግዚአብሔር ነው።
19እግዚአብሔርም በደላቸውን ሳይቆጥርባቸው ዓለሙን በክርስቶስ ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበር። እኛንም ለዚህ የዕርቅ መልዕክት ታማኝ አድርጎ ሾመን።
20ስለዚህም እግዚአብሔር በእኛ ሆኖ ልመናውን እንደሚያቀርብ፥ የክርስቶስ ተወካዮች ሆነን ተሹመናል። ከእናንተም ጋር በመሆን ስለ ክርስቶስ "ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ!" ብለን ልመና እናቀርባለን።
21እኛም በእርሱ የእግዚአብሔር ፅድቅ እንድንሆን ሃጢያት ሰርቶ የማያውቀውን ክርስቶስን እግዚአብሔር የሃጢያት መስዋዕት አደረገው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።