መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

2ኛ ቆሮንቶስ 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እንግዲህ፥ይህ አገልግሎት ስላለን እንዲሁም ምህረት እንደተቀበልን መጠን፥ ተስፋ አንቆርጥም።
2በዚያ ፈንታ ግን አሳፋሪ እና ድብቅ የሆኑ መንገዶችን ክደናል። የተንኮል ህይወት አንኖርም፥የእግዚአብሔርንም ቃል ያለ አግባብ አንጠቀምበትም። እውነትንም እየተናገርን ራሳችንን ለሰው ሁሉ ህሊና በእግዚአብሔር ፊት እናቀርባለን።
3ሆኖም ግን ወንጌላችን የተሸፈነ ቢሆን፥የተሸፈነው ለሚጠፉት ሰዎች ብቻ ነው።
4በእነርሱ ሁኔታ ታዲያ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምን አዕምሮዋቸውን አሳውሮታል። በዚህም የእግዚአብሔር መልክ የሆነውን የክርስቶስን የክብር ወንጌል ብርሃን እንዳያዩ አደረጋቸው።
5ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክም፥እንዲሁም ስለ ኢየሱስ ስንል የእናንተ አገልጋዮች ነን።
6ውስጥ ብርሃን ይብራ" ያለው ራሱ እግዚአብሔር ነው፤እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔር ክብር የእውቀት ብርሃን እንዲሰጠን በልባችን ውስጥ አበራልን።
7ነገር ግን እጅግ ታላቅ የሆነው ሃይሉ ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳልሆነ ለማሳየት ይህ ሃብት በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን።
8በሁሉ መንገድ መከራን እንቀበላለን፥ሆኖም በዚያ አንዋጥም። እናመነታለን ነገር ግን ተስፋ በማጣት አንረበሽም።
9ቢሆንም ግን ተረስተን አንቀርም።
10የኢየሱስ ህይወት በሰውነታችን እንዲገለጥ የእርሱን ሞት ሁልጊዜ በሰውነታችን እንሸከማለን።
11ይህም የኢየሱስ ህይወት በሰብዓዊ ሰውነቶቻችን እንዲገለጥ እኛ ህያዋን የሆንን በየዕለቱ ስለ ኢየሱስ ምክንያት ለሞት ታልፈን እንሰጣለን።
12በዚህም ምክንያት ሞቱ በእኛ፥ ህይወቱም በእናንተ ይሰራል።
13ነገር ግን "አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ"ተብሎ እንደተፃፈ፡ ሁላችንም አንድ አይነት የእምነት መንፈስ አለን። ስለምናምንም እንናገራለን።
14ጌታ ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው እኛንም ከእርሱ ጋር ያስነሳናል። ከእናንተም ጋር ወደ ፊቱ እንዲያመጣን እናውቃለን።
15የሚሆነው ለእናንተ ጥቅም ሲሆን ፀጋ ለብዙዎች ሲበዛ ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆን ምስጋናም ይጨምራል።
16ስለዚህም ተስፋ አንቆርጥም። ምንም እንኳ ውጫዊው ማንነታችን እየደከም ቢመጣም ውስጣዊው ማንነታችን ዕለት በየዕለት ይታደሳል።
17ይህ ጊዜያዊ፣ ቀላል መከራችን መለኪያ ለሌለው፥ ለላቀው ዘላለማዊ ክብር የሚያዘጋጀን ነው።
18የሚታዩትን ነገሮች ሳይሆን የማይታዩትን ነገሮች እንመለከታለን። የምናያቸው ነገሮች ጊዜያዊ ሲሆኑ የማይታዩት ነገሮች ግን ዘላለማዊ ናቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።