መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

2ኛ ቆሮንቶስ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ራሳችንን እንደገና ልናወድስ እንጀምራለንን? አንዳንድ ሰዎች እንደሚያደርጉት ለናንተም ሆነ ከእናንተ የድጋፍ ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆን? አያስፈልገንም።
2እናንተ ራሳችሁ በልባችን ላይ የተፃፋችሁ፥በሁሉም ሰዎች የምትታውቁ እና የምትነበቡ የድጋፍ ደብዳቤያችን ናችሁ።
3በእኛ የቀረባችሁ የክርስቶስ መልዕክት ከመሆናችሁም በላይ በህያው የእግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም ያልተፃፋችሁ፤በሰዎች የልብ ፅላት ላይ እንጂ በድንጋይ ፅላት ላይ ያልተቀረፃችሁ ናችሁ።
4እንግዲህ በክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ላይ ይህ መታመን አለን።
5ከእኛ የሆነ ብለን ልናስበው የምንችል አንዳች ችሎታ የለንም፤ነገር ግን ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው።
6እርሱም የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች አደረገን። ይህ ኪዳን የፊደል ሳይሆን የመንፈስ ነው። ምክንያቱም ፊደል ይገድላል፣ መንፈስ ግን ህይወትን ይሰጣል።
7የእስራኤል ህዝብ ከፊቱ ክብር የተነሳ እያደር የሚደበዝዘውን የሙሴን ፊት መመልከት እስኪያቅታቸው ድረስ በፊደላት በድንጋይ ላይ የተቀረፀው የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ፤
8የመንፈስ አገልግሎት እጅግ በክብር አይልቅምን?
9የኩነኔ አገልግሎት ክብር ከነበረው፥የፅድቅ አገልግሎት እንደምን በክብር ይብዛ!
10በርግጥም ቀድሞ በክብር የነበረው ከሱ በሚበልጥ ክብር ተሽሯል።
11አላፊው በክብር ከሆነ ፀንቶ የሚኖረው በክብር እንዴት ይበልጥ!
12እንግዲያውስ እንዲህ ያለ ትምክህት ስላለን እጅግ በድፍረት እንናገራለን።
13እኛ የእስራኤል ህዝቦች የሚያልፈውን ክብር ትኩር ብለው መመልከት እንዳልቻሉት፤ ፊቱን በመሸፈኛ እንደ ከለለው እንደ ሙሴ አይደለንም።
14ሆኖም ግን አእምሮዋቸው ተሸፈነባቸው። እስከዛሬም አሮጌው ኪዳን ሲነበብ ያው መሸፈኛ ይኖራል፤ሊገለጥም አይችልም፤ ምክንያቱም ሊወገድ የሚችለው በክርስቶስ ነው።
15ሆኖም ግን እስከዛሬ ድረስ የሙሴ ህግ ሲነበብ በልባቸው ላይ መሸፈኛው ይኖራል።
16ሰው ግን ወደ ጌታ መለስ ሲል ፥መሸፈኛው ይነሳል።
17ጌታም መንፈስ ነው፤የጌታም መንፈስ ባለበት ነፃነት አለ።
18እኛም ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት የጌታን ክብር እያየን እርሱን ወደሚመስል ከአንድ ክብር ደረጃ ወደ ሌላ ክብር ደረጃ እንለወጣለን፤ይህም የሚሆነው መንፈስ ከሆነው ጌታ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።