መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

2ኛ ቆሮንቶስ 12

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1መመካት አለብኝ፤ ነገር ግን በመመካት ጥቅም አይገኝም። ከጌታ ወዳሉት ራዕዮችና መገለጦች ግን እሄዳለው።
2በሥጋ ይሁን ወይም ከሥጋ ውጭ አላውቅም፤ እግዚአብሔር ግን ያውቃል። ከዐሥራ አራት ዓመታት በፊት በክርስቶስ የሆነ አንድ ሰው ወደ ሦስተኛ ሰማይ ተነጠቀ። እንደዚህ ያለውን ሰው ዐውቃለው።
3በሥጋ ይሁን ወይም ከሥጋ ውጭ እኔ አላውቅም፣ እግዚአብሔ ግን ያውቃል፣
4ይህ ሰው ወደ ገነት ተነጠቀ፤ ማንኛውም ሰው የማይናገራቸው እጅግ የተቀደሰ ነገሮችን ሰማ።
5እንደዚህ ስላለው ሰው እመካለው ስለራሴ ግን ከድካሜ በቀር አልመካም።
6ልመካ ከፈለግሁ፣ ሞኝ አይደለሁም፣ እውነትን እናገራለሁና፤ ነገር ግን ማንም በእኔ ከታየው ወይም ከእኔ ከተሰማው ፣
7ወይም በመገልጦቹ ልዩ ባሕርይ ምክንያት የምበልጥ አድርጎ እንዳያስብ አልመካም።ስለዚህ እንዳልታበይ፣ እጅግ እንዳልኩራራ የሥጋ መውጊያ፣የሚነዘንዘኝ የሰይጣን መልዕክተኛ ተሰጠኝ።
8መውጊያውን ከእኔ እንዲያነሣው ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ።
9እርሱም፣ «ጸጋዬ ይበቃሃል ኃይል በድካም ይፈጸማልና» አለኝ። ስለሆነም የክርስቶስ ኃይል ያርፍብኝ ዘንድ አብዝቼ ስለ ድካሜ እመካለው።
10ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም፣ በስድብ፣ በችግር፣ በስደት ፣ በጭንቀትም እርካታ ይሰማኛል በምደክምበት ጊዜ ሁሉ ብርቱ ነኝና።
11ሞኝ ሆኜአለሁ! እንዲህ እንድሆን ያስገደዳችሁኝ እናንተ ናችሁ፣እናንተ እኔን ልታመሰግኑኝ ይገባችሁ ነበር፥ምክንያቱም እኔ ምንም ባልሆን እንኳ ከ«ገናና ሐዋርያት» የማንስ አልነበርሁም።
12የአንድ ሐዋርያ እውነተኛ ምልክቶች በሁሉ ትዕግሥት፦ በምልክቶችና በድንቆች በብርቱ ተግባራትም በእናንተ መካከል ተደረጉ።
13እኔ ሸክም ካልሆንሁባችሁ በቀር ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት የምታንሱት እንዴት ነበር? ይህን ስሕትቴን ይቅር በሉኝ!
14አስተውሉ! ለሦስተኛ ጊዜ ወደ እናንተ ለመምጣት ተዘጋጅቻለው፤ ሸክም አልሆንባችሁም፤ እናንተን እንጂ፣ የእናንተ የሆነውን አልፈልግም። ወላጆች ለልጆች እንጂ ልጆች ለወላጆች ገንዘብ አያስቀምጡምና።
15እኔ እጅግ በጣምታልቅ በሆነ ደስታ ስለ ነፍሳችሁ እከፍላለው። እናንተን የበለጠ ብወዳችሁ፣ እኔ ከዚህ ያነሰ መወደድ አለብኝን?
16ልክ እንደዚህ፣ እኔ አልከበድሁባችሁም፤ነገር ግን በጣም በተንኮልና በጥበብ ያታለልኃችሁ መሰላችሁ።
17ወደ እናንተ በላክሁት በማንም ተጠቀምሁባችሁን?
18ወደ እናንተ እንዲመጣ ቲቶን የግድ አልኩት ፤ ከእርሱ ጋርም ሌላውን ወንድም ላክሁት። ቲቶስ ተጠቀመባችሁን? በአንድ መንገድ አልተጓዝንምን? በአንድ ፈለግስ አልተራመድንምን?
19በዚህ ጊዜ ሁሉ ለእናንተ ራሳችንን የምንከላከል ይመስላችኃልን? በእግዚአብሔር ፊት ስለእናንተ ድፍረት በክርስቶስ ብዙ ነገር እየተናገርን ነበር።
20ስመጣ እንደምፈልገው ሆናችሁ አላገኛችሁምብዬ እፈራለው። እናንተም እንደምትፈልጉት ሆኜ አታግኙኝም ብዬ እፈራለው ምናልባት ክርክር፣ ቅንዓት፣ የቁጣ መግንፈል፣ራስ ወዳድነት ያለበት ምⶉት፣ ሐሜት፣ ኩራትና ሁከት ይሆናሉ።
21ተመልሼ ስመጣ፣ አምላኬ በፊታችሁ ዝቅ እንዳያደርገኝ ብዬ እፈራለው ፣ከዚህ በፊትም ኃጢያ ስለሠሩት፣ እንዲሁም ስለ ፈጸሙት ርኩሰትና ዝሙት መዳራትም ስለ ብዙዎቻቸው አዝናለው ብዬ እፈራለው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።