1በጥቂት ሞኝነቴ ልትታገሱኝ ብትችሉ እመኝ ነበር፣ እናንተ ግን በእርግጥ ታግሳችሁኛል!
2እኔ ስለ እናንተ እቀናለሁና እንደ አንዲት ንጽሕት ድንግል ለክርስቶስ ላቀችርባችሁ ለአንድ ባል ስላጨዋችሁ በእግዚአብሔር ቅንአት እቀናላችኃለው ።
3ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳታለላት ፣ ሐሳባችሁ ለክርስቶስ ካልችሁ ቅንና ንጹህ ታማኝነት መረን እንዳትወጡ ብዬ እፈራለው።
4አንድሰው መጥቶ እኛ ከሰበክበው የተለየ ሌላ ኢየሱስ ቢያውጅላችሁ፣ ወይም ቀድሞ ከተቀበላችሁት የተለየ መንፈስ ብትቀበሉ ወይም እናንተ ከተቀበላችሁት የተለየ ወንጌል ቢደርሳችሁ ደህና ትታገሱታላችሁና።
5ከነዚያ «ገናና ሐዋርያት» በጥቂቱ እንኳ የማንስ አይደለሁም ብዬ አስባለውና።
6ነገር ግን በአነጋገር ያልሰለጠንሁ አይደለሁም። በሁሉም መንገድና በሁሉም ነገር ይህን አሳውቀናችኋል።
7የእግዚአብሔርን ወንጌል በነፃ ስለሰበኩለችሁ፥ እናንተ ከፍ እንድትሉ እኔ ራሴን በማዋረዴ ኋጢያት ሰራሁን?
8እናንተን ማገልገል እችል ዘንድ ከእነርሱ እርዳታ በመቀበል ሌሎችን አብያተ ክርስቲያናት«ጎዳሁ»።
9አብሬአችሁ በሆንኩና በተቸገርሁ ጊዜም በማንም ላይ ሸክም አልሆንሁም። ከመቄዶንያ የመጡት ወንድሞች የሚያስፈልገኝን ሰጥተዋልና። በሁሉም ረገድ ለእናንተ ሸክም ከመሆን ተጠንቅቄአለሁ፣ይህን ማድረጌንም እቀጥላለው ።
10የክርስቶስ እውነት በእኔ ውስጥ ያለ እንደ መሆኑ፣ ይህ የእኔ ትምህርት?
11ለምንስ እንዲህ ይሆናል? ለማልወደችሁ ነውን? እንደምወዳችሁ እግዚአብሔር ያውቃል። እንደነዚህ ያሉ ሰዎችን ራሳቸውን እንደ ክርስቶስ ሐዋርያት በማስመሰል ሐሰተኞች ሐዋርያት፣ አታላይ ሰራተኞች ናቸውና ።
12እኔን የሚነቅፉትንና እኛ የምናደርገውን እነርሱም እያደረጉ እንደ ሆነ እየተናገሩ የሚመኩበትን ምክንያት ለማሳጣት አሁን የሚደረገውን ወደ ፊትም አደርጋለሁ።
13እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች ሐሰተኛ ሐዋርያትና አታላይ ሸራተኞች ናቸው።
14ይህም የሚያስደንቅ አይደለም፣ ሰይጣን እንኳ ራሱን የብርሓን መልአክ በማስመሰሉ ርሱን ይለውጣልና።
15የእርሱ አግልጋዮች ደግሞ የጽድቅ አገልጋዮች በማስመሰል ራሳቸውን ቢለውጡ እጅግ የሚያስደንቅ አይደለም። ዕጣ ፈንታቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።
16ደግሜ እላለሁ፦ እኔ ሞኝ እንደሆንሁ ማንም አያስብ ። ሞኝ እንደሆንሁ ብታስቡ ግን በጥቂቱ እመካ ዘንድ እንደ ሞኝ ተቀበሉኝ።
17እንደዚህ ታምኜ በመመካት የምናገረው፣ ጌታ የፈቀደው አይደለም፣ እኔ ግን እንደ ሞኝ እናገራለው።
18ብዙ ሰዎች በሥጋ ሰለሚመኩ፣ እኔም ደግሞ እመካለው።
19እናንተ ብልሆች ሆናችሁ ሞኞችን በደስታ ትታገሣላችሁና!
20ማንም ባሪያዎች ቢያደርጋችሁ፣ ማንም በመካከላችሁ መለያየትን ቢፈጥር፣ ማንም መጠቀሚያ ቢያደርጋችሁ፣ ማንም ቢቀማችሁ ፣ወይም ፊታችሁን በጥፊ ቢመታችሁ ትታገሱታላችሁና.
21ይህንን ስናደርግ በጣም ደካሞች እንደ ነበርን እያፈርሁ እናገራለ። ሆኖም ማንም በሚመካበት ጊዜ ሁሉ እንደ ሞኝ እላለው፣ እኔ ደግሞ እመካለሁ።
22እነርሱ ዕብራውያን ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ እስራኤላውያን ናቸውን እኔ ደግሞ ነኝ። የአብርሃም ዘር ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ።
23የክርስቶስ አግልጋዮች ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ (እንደ እብድ እናገራለው) እኔ እበልጣለሁ፣ በከባድ ሥራ አብዝቼ በመታሰር አብዝቼ፣ በመደብደብ ከልክ በላይ፣ ብዙ የሞት አደጋዎችን በመጋፈጥ ብዙ ጊዜ ሆንሁ።
24አይሁድ «አንድ ሲጎድል አርባ ጅራፍ»አምስት ግዜ ገረፉኝ።
25ሦስት ጊዜ በበትር ተመታሁ። አንድ ግዜ በድንጋይ ተወገርሁ። ሦስት ጊዜ የተሳፈርኩበት መርከብ ተሰበረ። አንድ ሌሊትና አንድ ቀን በባህር ላይ አሳለፍሁሁሁ፣
26በተደጋጋሚ በመንገድ ተጓዝሁ። በወንዞች አደጋ፣ በወንበዴዎች አደጋ በወገኖቼ በኩል አደጋ፣ በአሕዛብ በኩል አደጋ፣ በከተማ አደጋ በምድረ በዳ አደጋ፣ በባሕር አደጋ፣ በሐሰተኞች በኩል አደጋ ነበረብኝ።
27በከባድ ስራና በችግር፣ እንቅልፍ ባጣሁባቸው ብዙ ሌሊቶች፣ በረሃብና በጥም ፣ እንዲሁም የሚበላ በማጣት፣በብርድባ በራቁትነት ነበርሁ።
28ከሌላውም ሁሉ በተለይ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ ለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያለኝ ጭንቀት ነው።
29ደካማ ምን ነው እኔስ አልደክምምን? ኃጢአት እንዲሠራ ሌላውን ያሰናከለ ማን ነው፣ እኔስ በውስጤ አልናደድምን?።
30መመካት ካለብኝ፣ ድካሜን ስለሚያሳየው ነገር እመካለው።
31እንደማልዋሽ፣ ለዘላለም የተመሰገነው የጌታ ኢየሱስ አምላክና አባት ያውቃል።
32በደማስቆ ከንጉስ አርስጦስዮስ በታች የሆነ ገዢ እኔን ይዞ ለማሰር ከተማዋን እየጠበቀ ነበር፣
33ነገር ግን በቅጥሩ ባለ መስኮት በቅርጫት አወረዱኝ፣ ከእጆቹም አመለጥሁ።