መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

2ኛ ቆሮንቶስ 13

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው። «ክስ ሁሉ በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች መጽናት አለበት።»
2ሁለተኛ ስመጣ በፊት ኃጢያት ለሰሩትና ለሌሎች ሁሉ ተናግሬአለው፥ አሁንም ደግሞ እላለው ተመልሼ ስመጣ እንዲሁ አላልፋቸውም።
3ክርስቶስ በእኔ በኩል እየተናገረ ስለ መሆኑ ማስረጃ ስለምትሹ ይህን እነግራችሏለው። ክርስቶስ ስለ እናንተ አይደክምም፥ ይልቁንም እርሱ በእናንተ ኃይለኛ ነው።
4እርሱ በድካም ተሰቅሏልና፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል ሕያው ነው። እኛ ደግሞ በእርሱ ደካሞች ነንና፤ ነገር ግን በመካከላችሁ ብለው የእግዚአብሔር ኀይል ሕያዋን ነን።
5በእምነት መሆናችሁን ለማየት ራሳችሁን መርምሩ። ራሳችሁን ፈትኑ። ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ እንደሚኖር አትገነዘቡምን? ተፈትናችሁ ካላለፋችሁ በቀር፣ እርሱ በእናንተ ይኖራል።
6እኛ ግን ተፈትነን ያለፍን መሆናችንን እንደምታውቁ እተማመናለው።
7እንግዲህ እናንተ ክፉ እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፥ ይህንም የምናደርገው ፈተናውን ያለፍን መሰለን ለመታየት አይደለም፥ ነገር ግን ፈተናውን ያላለፍን ብንመስልም እንኳ፣ እናንተ ትክክል የሆነውን ታደርጉ ዘንድ እጸልያለው።
8ስለ እውነት እንጂ የእውነት ተቃራኒ የሆነ ነገር መሥራት አንችልምና።
9እኛ ደካሞች ሆነን እናንተ ብርቱዎች ስትሆኑ ደስ ይለናልና። እናንተ ፍጹማን እንድትሆኑ እንኛ ደግሞ እንጸልያለን።
10ከእናንተ ርቄ እያለው እነዚህን ነገሮች ጻፍሁላችሁ፤ ከእናንተ ጋር ሳለው እናንተ ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ ያይደለ ጌታ የሰጠኝ ሥልጣንን በመጠቀም እንዳላመናጭቃችሁ ንችው።
11በመጨረሻ፣ ወንድሞችና እኅቶች፣ ደስ ይበላችሁ! ለተሐድሶ ሥሩ፤ተበረታቱ፤እርስ በርሳችሁ ተስማሙ፤በሰላም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላም አምልክም ከእናንተ ጋር ይሆናል።
12በተቀደሰ አሳሳም ሰላም ተባባሉ።
13ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
14የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ፍቅር፣የመንፈስ ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።