መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሁለተኛ ዜና 34

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ኢዮስያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ እድሜው ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ።
2በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ፤ በአባቱም በዳዊት መንገድ ሄደ፤ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም።
3በነገሠም በስምንተኛው ዓመት ገና ወጣት እያለ የአባቱን የዳዊትን አምላክ መፈለግ ጀመረ። በአሥራ ሁለተኛው ዓመትም ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ከኮረብታው መስገጃዎች፥ ከማምለኪያ ዐፀዶቹ፥ ከተቀረጹት ምስሎችና ቀልጠው ከተሠሩት ምስሎች ማጽዳት ጀመረ።
4ሕዝቡ የበኣሊምን መሠዊያዎች በእርሱ ፊት አፈረሱ፤ እርሱ ከበላያቸው የነበሩትን የዕጣን መሠዊያዎች ሰባበረ። የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ሰባበረ፤ የተቀረጹትን ምስሎች፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች አፈር እስኪሆኑ ድረስ አደቀቃቸው። ትቢያውንም መሥዋዕት ይሰዉላቸው በነበሩ ሰዎች መቃብር ላይ በተነው።
5የካህናቶቻቸውንም አጥንቶች በመሠዊያቸው ላይ አቃጠለ። በዚህ መንገድ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አጸዳ።
6በምናሴ፥ በኤፍሬም፥ በስምዖን ከተሞችም እስከ ንፍታሌም ድረስና በዙሪያቸው ባሉት ፍርስራሾች ሁሉ ተመሳሳይ ነገር አደረገ።
7መሠዊያዎቹን አፈረሰ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንና የተቀረጹትን ምስሎች አደቀቃቸው፤ በእስራኤል ምድር ሁሉ የዕጣን መሠዊያዎችን ሁሉ ቆራረጠ፤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
8ኢዮስያስ ምድሪቱንና ቤተ መቅደሱን ካጸዳ በኋላ በነገሠ በአሥራ ስምንተኛው ዓመት የኤዜልያስን ልጅ ሳፋን፥የከተማይቱንም ገዢ መፅሤያ፥ የታሪክ ጸሐፊውንም የኢዮአካዝን ልጅ ኢዮአክን የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቤት እንዲያድሱ ላካቸው።
9እነርሱም ወደ ሊቀ ካህኑ ወደ ኬልቅያስ ሄደው ሌዋውያኑ፥ የበሮቹ ጠባቂዎች ከምናሴና ከኤፍሬም፥ ከእስራኤል ቅሬታዎች ሁሉ፥ ከይሁዳና ከብንያም ሁሉ፥ ከኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች የሰበሰቡትን ወደ እግዚአብሔር ቤት የመጣውን ገንዘብ አደራ ሰጡት።
10ገንዘቡን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ በበላይነት ለሚቆጣጠሩት ሰዎች ሰጧቸው። እነዚህ ሰዎች ቤተ መቅደሱን ለሚጠግኑና ለሚያድሱ ሠራተኞች ከፈሏቸው።
11የተጠረበውን ድንጋይ፥ ለማጋጠሚያ ጣውላ እንጨትና አንዳንድ የይሁዳ ነገሥታት እንዲፈርስ ለተዉት መዋቅር ወራጆች እንዲገዙ ለአናጢዎቹና ግንበኞቹ ከፈሏቸው።
12ሰዎቹም ሥራውን በታማኝነት ሠሩ። ሥራውን በበላይነት የሚቆጣጠሯቸው ሌዋውያኑ ከሜራሪ ልጆች ኢኤትና አብድዩ፥ ከቀዓትም ልጆች ዘካርያስና ሜሱላም ነበሩ። ሁሉም መልካም የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቾች የነበሩ ሌሎች ሌዋውያንም ሠራተኞቹን በቅርበት አቅጣጫ ይመሯቸው ነበር።
13እነዚህ ሌዋውያን የግንባታ ዕቃ የሚሸከሙትንና በሌላም መንገድ የሚሠሩትን ሌሎች ሰዎች ሁሉ ይቆጣጠሩ ነበር። ጸሐፊዎች፥ አስተዳዳሪዎችና የበር ጠባቂዎች የነበሩ ሌሎች ሌዋውያንም ነበሩ።
14ወደ እግዚአብሔር ቤት የመጣውን ገንዘብ ወደ ውጪ ሲያመጡት ካህኑ ኬልቅያስ በሙሴ በኩል የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ አገኘ።
15ኬልቂያስም ጸሐፊውን ሳፋንን፦" በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሕጉን መጽሐፍ አግኝቼአለሁ" አለው። ኬልቅያስም መጽሐፉን ወደ ሳፋን አመጣው።
16ሳፋንም መጽሐፉን ወደ ንጉሡ ወስዶ፦"አገልጋዮችህ በኃላፊነት የተሰጣቸው ማናቸውንም ነገር እያደረጉ ናቸው።
17በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የተገኘውን ገንዘብ ወደ ውጪ አውጥተው ለተቆጣጣሪዎቹና ለሠራተኞቹ አደራ ሰጥተዋል" በማለት ነገረው።
18ጸሐፊውም ሳፋን ለንጉሡ ፦"ካህኑ ኬልቅያስ አንድ መጽሐፍ ሰጥቶኛል" ብሎ ነገረው። ከዚያም ለንጉሡ አነበበለት።
19ንጉሡ የሕጉን ቃላት በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀደደ።
20ንጉሡም ኬልቅያስን፥ የሳፋንንም ልጅ አኪቃምን፥ የሚክያስንም ልጅ ዓብዶንን፥ ጸሐፊውንም ሳፋንን የራሱንም አገልጋይ ዓሳያን፦
21"ሄዳችሁ ከተገኘው መጽሐፍ ቃል የተነሳ ለእኔና በእስራኤልና በይሁዳ ለተረፉት ሰዎች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠይቁ። በእኛ ላይ የፈሰሰው የእግዚአብሔር ቁጣ ታላቅ ስለሆነ፥ በውስጡ የተጻፈውን ሁሉ ለመታዘዝ አባቶቻችን የዚህን መጽሐፍ ቃላት ስላልሰሙ ቁጣው ታላቅ ነው።
22በመሆኑም ኬልቅያስና ንጉሡ ያዘዛቸው ሰዎች (በኢየሩሳሌም በሁለተኛው ክፍል ትኖር ወደ ነበረችው) ወደ ልብሰ ተክህኖ ጠባቂው ወደ ሐስራ ልጅ፥ ወደ ቲቁዋ ልጅ፥ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢይቱ ወደ ሕልዳና ሄዱ፤ እንዲህም ብለው አናገሯት።
23እርሷም፦"የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፦ወደ እኔ ለላካችሁ ሰው ንገሩት፥
24"እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፦ 'እነሆ በይሁዳ ንጉሥ ፊት ባነበቡት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉትን እርግማን ሁሉ በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ ጥፋትን ላመጣ ነው።
25ባደረጓቸው ተግባራት ሁሉ ለቁጣ ሊያነሳሱኝ እኔን ትተው ለሌሎች አማልክት ዕጣንን ከማጠናቸው የተነሳ ስለዚህ ቁጣዬ በዚህ ሥፍራ ላይ ይነድዳል፤ ምንም ነገርም አያቆመውም'" አለቻቸው።
26ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመጠየቅ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ የምትሉት ይህ ነው፦" የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ ሰማኸው ቃል፦
27' ልብህ ለስላሳ ስለ ነበርና በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ እንደሚመጣ የተነገረውን ቃሉን ስትሰማ በእግዚአብሔር ፊት ራስህን ስላዋረድህ፥ ራስህንም በፊቴ አዋርደህ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ ስላለቀስህ እኔም ሰምቼሃለሁ' እግዚአብሔር የሚናገረው ይህ ነው፤
28'እነሆ ወደ ዝርያዎችህ እሰበስብሃለሁ፤ በሰላምም ወደ መቃብርህ ትሰበሰባለህ፤ በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ የማመጣውን የትኛውንም ጥፋት ዓይኖችህ አያዩም'" በመሆኑም ሰዎቹ ይህንን መልዕክት ለንጉሡ መልሰው ወሰዱለት።
29ከዚያም ንጉሡ መልዕክተኞችን ልኮ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ።
30ንጉሡም የይሁዳ ወንዶችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑና ከትልቅ እስከ ትንሽ ሕዝቡ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ። በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ቃል ሁሉ እየሰሙት አነበበላቸው።
31ንጉሡም በቦታው ቆሞ እግዚአብሔርን ተከትሎ ለመሄድ፥ ትዕዛዛቱን፥ የቃል ኪዳን ድንጋጌዎቹንና ደንቦቹን ለመጠበቅ፥ በሙሉ ልቡና በሙሉ ነፍሱ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉትን የቃል ኪዳኑን ቃላት ለመታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረገ።
32በኢየሩሳሌምና በብንያም የሚገኙትን ሁሉ በቃል ኪዳኑ እንዲቆሙ አደረጋቸው። የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር ቃል ኪዳን በመታዘዝ አደረጉ።
33ኢዮስያስም የእስራኤል ሕዝብ ከነበረው ምድር ላይ አስጸያፊውን ነገር ሁሉ አስወገደ። በእስራኤልም የነበሩት ሰዎች ሁሉ አምላካቸው እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ አደረጋቸው። በእርሱ ዘመን ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ከመከተል ዘወር አላሉም።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።