መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሁለተኛ ዜና 27

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ኢዮአታምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ። የእናቱም ስም ኢየሩሳ ነበር፤ እርሷም የሳዶቅ ልጅ ነበረች።
2በሁሉም ነገር የአባቱን የዖዝያንን ምሳሌ ተከትሎ በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ። ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከመግባትም ተቆጠበ። ሕዝቡ ግን ገና በክፉ መንገድ ይሄዱ ነበር።
3የእግዚአብሔርን ቤት የላይኛውን በር ሠራ፤ በዖፌልም ኮረብታ ላይ እጅግ ብዙ የግንባታ ሥራዎችን ሠራ።
4በተጨማሪም በኮረብታማው የይሁዳ አገር ላይ ከተሞችን፥ በደኖቹ ውስጥ ደግሞ አምባዎችንና ማማዎችን ገነባ።
5ከአሞንም ሕዝብ ንጉሥ ጋር ተዋግቶ አሸነፋቸው። በዚያው ዓመት የአሞን ልጆች አንድ መቶ መክሊት ብር፥ አሥር ሺህ መስፈሪያ ስንዴ፥ አሥር ሺህ መስፈሪያ ገብስ ሰጡት። የአሞን ሕዝብ በሁለተኛውና በሦስተኛውም ዓመት ተመሳሳዩን ያህል ሰጡት።
6በመሆኑም ኢዮአታም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት በጽናት ስለተራመደ ብርቱ ሆነ።
7ኢዮአታምን በተመለከተ ሌሎቹ ነገሮች ጦርነቶቹ ሁሉና መንገዱ እነሆ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።
8ኢዮአታም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌም ለአሥራ ስድስት ዓመታት ነገሠ።
9ኢዮአታምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ቀበሩት። ልጁም አካዝ በእርሱ ቦታ ነገሠ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።