መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሁለተኛ ዜና 24

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ኢዮስያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሰባት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም አርባ ዓመት ነገሠ፡፡ የቤርሳቤዋ እናቱ ስም ሳብያ ነበር፡፡
2ኢዮስያስ ካህኑ ዮዳሄ በነበረበት ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ፡፡
3ዮዳሄ ለኢዮስያስ ሁለት ሚስቶችን አጋባው፤ የወንዶችና የሴቶች ልጆች አባት ሆነ፡፡
4ከዚህም በኋላ ኢዮስያስ የእግዚአብሔርን ቤት ለመጠገን ወሰነ፡፡
5ካህናቱንና ሌዋውያኑን በአንድነት ሰብስቦ ፦"በየዓመቱ ወደ ይሁዳ ከተሞች ውጡና የአምላካችሁን ለማደስ ከእስራኤል ሁሉ ገንዘብን ሰብስቡ፡፡ በፍጥነት መጀመራችሁን እርግጠኛ ሁኑ" አላቸው፡፡ ሌዋውያኑ በመጀመሪያ ምንም አላደረጉም፡፡
6በመሆኑም ንጉሡ ሊቀ ካህናቱን ጠርቶ፦"ሌዋውያኑ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ለቃል ኪዳኑ ድንኳን ድንጋጌ የእስራኤል ጉባኤ የተጣለባቸውን ግብር ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም እንዲያስመጡ ለምን አላደረግሃቸውም?" አለው፡፡
7የዚያች ክፉ ሴት የጎቶልያ ልጆች የእግዚአብሔርን ቤት አፍርሰው እና የእግዚአብሔርንም ቤት የተቀደሱ ነገሮች ሁሉ ለበኣል ሰጥተው ነበር፡፡
8በመሆኑም ንጉሡ ስለአዘዘ የገንዘብ ሳጥን ሰርተው በእግዚአብሔር ቤት መግቢያ በስተውጪ አስቀመጡት፡፡
9የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ በእስራኤል ላይ የጣለባቸውን ግብር ለእግዚአብሔር እንዲያመጡ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ሁሉ አዋጅ ነገሩ፡፡
10መሪዎቹ ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ደስ ብሎአቸው ገንዘብ አመጡ፤ እስኪሞሉትም ድረስ በገንዘብ ሳጥኑ ውስጥ አስቀመጡት፡፡
11የገንዘብ ሳጥኑ በሌዋውያኑ እጅ ወደ ንጉሡ ሹማምንት በሚመጣበት ጊዜ ሁሉና ብዙ ገንዘብ እንዳለበት ባዩ ጊዜ ሁሉ የንጉሡ ጸሐፊና የሊቀ ካህናቱ ሹም መጥተው ከገንዘብ ሳጥኑ ገንዘቡን አውጥተው በመውሰድ ሳጥኑን ወደ ሥፍራው ይመልሱት ነበር፡፡ ከፍ ያለ መጠን ያለው ገንዘብ በመሰብሰብ ይህንንም ዕለት ዕለት ያደርጉት ነበር፡፡
12ንጉሡና ዮዳሄ በእግዚአብሔር ቤት የማገልገል ሥራ ለሚሠሩት ሰዎች ገንዘቡን ይሰጡ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቤት ለሚያድሱት ድንጋይ ጠራቢዎችና አናጢዎች እንዲሁም የብረትና የነሃስ ሥራ የሚሠሩትን ቀጥረው ያሠሩበት ነበር፡፡
13በመሆኑም ሠራተኞቹ አብዝተው ሠሩ፤ የጥገናውም ሥራ በእጃቸው ተከናወነ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት በመጀመሪያ ንድፉ አቁመው አጠናከሩት፡፡
14በጨረሱም ጊዜ የተረፈውን ገንዘብ ወደ ንጉሡና ዮዳሄ አመጡት፡፡ ይህ ገንዘብ የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ፥ ለአገልግሎትና መሥዋዕት ለማቅረብ የሚሆኑ ማንኪያዎችንና የወርቅና የብር ዕቃዎች ለማሟላት ጥቅም ላይ ዋለ፡፡ በዮዳሄ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሚቃጠል መሥዋዕት ባለማቋረጥ ያቀርቡ ነበር፡፡
15ዮዳሄም ሸመገለ፤ ዕድሜም ጠግቦ ሞተ፡፡ በሚሞትበት ጊዜ ዕድሜው መቶ ሠላሳ ዓመት ነበር፡፡
16በእስራኤልም ለእግዚአብሔርና ለእግዚአብሔር ቤት መልካም ስላደረገ በነገሥታቱ መካከል በዳዊት ከተማ ቀበሩት፡፡
17ዮዳሄ ከሞተ በኋላ የይሁዳ መሪዎች መጥተው ለንጉሡ ክብርን ሰጡት፡፡ ንጉሡም አዳመጣቸው፡፡
18የአባቶቻቸውን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤት ትተው የማምለኪያ ዐፀዶችንና ጣዖታቱን አመለኩ፡፡በዚህም ኃጢአታቸው ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ መጣ፡፡
19ሆኖም ግን ወደ እግዚአብሔር ወደ ራሱ እንደገና እንዲያመጧቸው ነቢያትን ይልክላቸው ነበር፤ ነቢያቱም በሕዝቡ ላይ ይመሰክሩባቸው ነበር፤ እነርሱ ግን ለመስማት እምቢ አሉ፡፡
20የእግዚአብሔር መንፈስ በካህኑ በዮዳሄ ልጅ በዘካርያስ ላይ መጣ፤ እርሱም ከሕዝቡ በላይ ቆሞ፦"እግዚአብሔር ይህንን ይላል፤ 'የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ? መልካም ነገር ሊሆንላችሁ አይችልም፡፡ እግዚአብሔርን ስለተዋችሁ እርሱም ትቶአችኋል'" አላቸው፡፡
21እነርሱ ግን አሴሩበት፤ በንጉሡ ትዕዛዝም በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ውስጥ በድንጋይ ወገሩት፡፡
22በዚህ ሁኔታ ንጉሡ ኢዮአስ የዘካርያስ አባት ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት ችላ አለ፡፡ ይልቁንም የዮዳሄን ልጅ ገደለ፡፡ ዘካርያስም በሚሞትበት ጊዜ፦" እግዚአብሔር ይህንን ይየው፤ ይጠይቃችሁም" አለ፡፡
23በዓመቱ መጨረሻም የአራም ሠራዊት ሊያጠቁት በኢዮአስ ላይ መጡበት፡፡ ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ የሕዝቡን መሪዎች ሁሉ ገደሉ፤ ከእነርሱ የወሰዱትንም ምርኮ ሁሉ ወደ ደማስቆ ንጉሥ ላኩ፡፡
24የሶርያውያንም ሠራዊት የመጡት ከትንሽ ሠራዊት ጋር ነበር፤ ነገር ግን ይሁዳ የአባቶቻቸውን አምላክ ከመተዋቸው የተነሳ እግዚአብሔር እጅግ ታላቅ በነበረው ሠራዊት ላይ ድልን ሰጣቸው፡፡ በዚህ መንገድ የሶርያውያን ሠራዊት በኢዮአስ ላይ ፍርድን አመጡበት፡፡
25ሶርያውያን ከሄዱ በኋላ ኢዮአስ ክፉኛ ቆስሎ ነበር፡፡ ከካህኑ ከዮዳሄ ልጆች ግድያ የተነሳ የገዛ አገልጋዮቹ አሲረውበት ነበር፡፡ በአልጋው ላይ ገደሉት፤ እርሱም ሞተ፤ በነገሥታቱ መቃብር ሳይሆን በዳዊት ከተማ ቀበሩት፡፡
26ያሴሩበትም ሰዎች የአሞናዊቷ የሰምዓት ልጅ ዛባድ፥ የሞዓባዊቷ የሰማሪት ልጅ ዮዛባት ነበሩ፡፡
27የልጆቹ ነገርና ስለ እርሱ የተነገሩት ዋና ዋና ትንቢቶች እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቤት እንደገና መገንባቱ እነሆ በነገሥታቱ መጽሐፍ ማብራሪያ ተጽፈዋል፡፡ ልጁም አሜስያስ በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።