መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሁለተኛ ዜና 22

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችም የኢዮራምን ታናሽ ልጅ አካዝያስን በእርሱ ቦታ አነገሡት፤ ምክንያቱም ከአረቢያኖቹ ጋር ወደ ካምፑ የመጡባቸው የሽፍቶች ቡድን የእርሱን ታላላቆች ሁሉ ገድለዋቸው ስለነበር ነው፡፡ በመሆኑም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ነገሠ፡፡
2አካዝያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ አርባ ሁለት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሁለት ዓመት ነገሠ፡፡ የእናቱ ስም ጎቶልያ ነበረ፤ እሷም የዖምሪ ልጅ ነበረች፡፡
3እናቱ ክፉ ነገሮችን ለማድረግ መካሪው ስለነበረች እርሱም በአክዓብ ቤት መንገድ ሄደ፡፡
4ከአባቱ ሞት በኋላ ለገዛ ራሱ ጉዳት እስኪሆን የአክዓብ ቤት መካሪዎቹ ስለነበሩ የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፡፡
5ምክራቸውንም ተከተለ፤ የአራምን ንጉሥ አዛሄልን በሬማት ዘገለዓድ ሊዋጋ ከእስራኤል ንጉሥ ከአክዓብ ልጅ ከኢዮራም ጋር ሄደ፡፡ አርመናውያንም ኢዮራምን አቆሰሉት፡፡
6ኢዮራምም የአራምን ንጉሥ አዛሄልን በራማ በተዋጋ ጊዜ ካቆሰሉት ቁስል ይፈወስ ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ፡፡ ኢዮራም ቆስሎ ስለነበር የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የአክዓብን ልጅ ኢዮራምን ሊያየው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ፡፡
7አካዝያስ ኢዮራምን በመጎብኘቱ አማካይነት እንዲጠፋ እግዚአብሔር ፈቅዶ ነበር፡፡ በመጣ ጊዜ የአክዓብን ቤት እንዲያጠፋ እግዚአብሔር የመረጠውን የናሚሴን ልጅ ኢዩን ለማጥቃት ከኢዮራም ጋር ሄደ፡፡
8ኢዩም የእግዚአብሔርን ፍርድ በአክዓብ ቤት ላይ እየፈጸመ በነበረበት ጊዜ የይሁዳን መሪዎችና አካዝያስን የሚያገለግሉትን የአካዝያስን ወንድሞች ልጆች አገኛቸው፡፡ ኢዩም ገደላቸው፡፡
9ኢዩ አካዝያስን ፈለገው፤ በሰማርያም ተሸሽጎ አገኙት፤ ወደ ኢዩም አመጡት፤ እርሱም ገደለው፡፡ ከዚያም "እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ የፈለገው የኢዮሳፍጥ ልጅ ነው" ብለው ቀበሩት፡፡ በመሆኑም የአካዝያስ ቤት መንግሥቱን ለመምራት ምንም የቀረ ኃይል አልነበረውም፡፡
10የአካዝያስ እናት ጎቶልያ ልጇ መሞቱን ባየች ጊዜ ተነስታ በይሁዳ ቤት ውስጥ የነገሥታቱን ዝርያ ልጆች ሁሉ ገደለች፡፡
11ነገር ግን የንጉሡ ልጅ ዮሳቤት የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስን ከተገደሉት ከንጉሡ ልጆች መካከል ሰርቃ ወሰደችው፤ እርሱንና ሞግዚቱን በመኝታ ክፍል ውስጥ አስቀመጠቻቸው፡፡ ስለዚህ የንጉሡ የኢዮራም ልጅ የካህኑ የዮዳሄ ሚስት ዮሳቤት (የአካዝያስ እኅት ስለነበረች) ጎቶልያ እንዳትገድለው ከጎቶልያ ሸሸገችው፡፡
12ጎቶልያ በምድሪቱ ላይ ስትገዛ ሳለ እርሱ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ለስድስት ዓመታት ተሸሽጎ ከእነርሱ ጋር ነበረ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።