መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሁለተኛ ዜና 14

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1አብያም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፡፡ ልጁም አሳ በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡ በእርሱም ዘመን በምድሪቱ ላይ ለአሥር ዓመታት ፀጥታ ነበር፡፡
2አሳ በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ትክክለኛውን ነገር አደረገ፤
3የእንግዶቹን አማልክት መሠዊያ እና መስገጃዎቹን አስወገደ፤ የተቀደሱትን የድንጋይ ሐውልቶች ሰባበረ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቆራረጠ፡፡
4የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ይሹ ዘንድ እና ሕጉንና ትዕዛዛቱን ይፈጽሙ ዘንድ ይሁዳን አዘዘ፡፡
5ከይሁዳም ከተሞች ሁሉ መስገጃዎቹንና ዕጣን የሚጨስባቸውን መሠዊያዎች አስወገደ፡፡ መንግሥቱም በእርሱ ሥር በሰላም ተቀመጠች፡፡
6በምድሪቱ ላይ ጸጥታ ስለነበርና እግዚአብሔርም ሰላም ስለሰጠው በእነዚያ ዓመታት ምንም ጦርነት ስላልነበረበት በይሁዳ የተመሸጉ ከተሞችን ሠራ፡፡
7አሳም ይሁዳን፡-"እነዚህን ከተሞች እንገንባ፤ በዙሪያቸው ቅጥር ፥ ማማዎች፥ መዝጊያዎች፥ እና መወርወሪያዎች እንሥራ፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ስለፈለግነው ምድሪቱ እስከ አሁንም የእኛ ናት፡፡ እኛም ፈልገነዋል እርሱም በሁሉም በኩል እረፍት ሰጥቶናል፡፡" አላቸው፡፡ እነርሱም ገነቡ፤ ተሰካላቸውም፡፡
8ለአሳም ጋሻና ጦር የሚይዙ ከይሁዳ ሦስት መቶ ሺህ ሰዎች፥ ጋሻ የሚይዙና ቀስት የሚስቡ ደግሞ ከቢኒያም ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች የያዘ ሠራዊት ነበረው፡፡
9ኢትዮጵያዊው ዝሪ አንድ ሚሊዮን ወታደሮችና ሦስት መቶ ሰረገሎች ያሉት ሠራዊት ይዞ ሊያጠቃቸው መጣባቸው፤ ወደ መሪሳም መጣ፡፡
10አሳም ሊጋጠመው ወጣ፤ በመሪሳም በጽፋታ ሸለቆ ውስጥ በጦርነቱ ግንባር ተሰለፉ፡፡
11አሳም ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ፦ "እግዚአብሔር ሆይ ምንም ጉልበት የሌለው ሰው ብዙዎችን በሚጋፈጥበት ጊዜ ካንተ በቀር ማንም የሚረዳው የለም፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ በአንተ ላይ ተማምነናልና እርዳን፤ ይህንን የመጣብንን ብዙ ቁጥር ያለው ሠራዊት በስምህ እንመጣባቸዋለን፡፡ እግዚአብሔር ሆይ አንተ አምላካችን ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህ" ብሎ ጮኸ፡፡
12እግዚአብሔርም በአሳና በይሁዳ ፊት ኢትዮጵያውያንን መታ፤ ኢትዮጵያውያንም ሸሹ፡፡
13አሳና ወታደሮቹም እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዱአቸው፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሔርና በሠራዊቱ ፊት ሙሉ በሙሉ ስለተደመሰሱ ማገገም እስከማይችሉ ድረስ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደቁ፡፡ሠራዊቱም እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰዱ፡፡
14የእግዚአብሔር ድንጋጤ በነዋሪዎቹ ላይ ስለመጣባቸው ሠራዊቱ በጌራራ ዙሪያ ያሉ መንደሮችን ሁሉ ደመሰሱ፡፡ በውስጣቸውም እጅግ ብዙ ምርኮ ስለነበር ሠራዊቱ መንደሮቹን ሁሉ በዘበዙ፡፡
15የከብት አርቢ ዘላኖቹን የድንኳን ሰፈራዎችም ደመሰሱ፤ ከመጠን በላይ በጎችን እንዲሁም ግመሎችን ወስደው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።