መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሁለተኛ ዜና 13

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ንጉሥ ኢዮርብዓም በነገሠ በአሥራ ስምንተኛው ዓመት አብያ በይሁዳ ላይ መንገሥ ጀመረ፡፡
2በኢየሩሳሌም ለሦስት ዓመታት ገዛ፤ የገብዓው ሰው የኡርኤል ልጅ የነበረችው የእናቱ ስም ሚካያ ነበር፡፡ በአብያና በኢዮርብዓም መካከል ጦርነት ነበረ፡፡
3አብያም ከአራት መቶ ሺህ የተመረጡ ጠንካራ፥ ደፋር ሰዎች ሠራዊት ጋር ወደ ጦርነት ሄደ፡፡ ኢዮርብዓምም ከተመረጡት ስምንት መቶ ሺህ የተመረጡ ጠንካራ፥ ደፋር ወታደሮች ጋር ሊጋጠመው ተሰለፈ፡፡
4አብያም በተራራማው በኤፍሬም አገር ባለው በጽማራይም ተራራ ላይ ቆሞ፦ "ኢዮርብዓምና እስራኤል ሁሉ ስሙኝ!
5የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ መንግሥት ለዳዊት ለዘላለም ለልጆቹ በደንብ በተጠበቀ ቃል ኪዳን እንዲገዙ እንደሰጠ አታውቁምን?" አለ፡፡
6የዳዊት ልጅ የሰለሞን ባሪያ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ግን ተነሳና በጌታው ላይ ዐመፀ፡፡
7የማይረቡ ሰዎችም ጸያፍ ሰዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፡፡ የሰለሞን ልጅ ሮብዓም ወጣትና ልምድ የለሽ በነበረበትና ሊቋቋማቸው በማይችልበት ጊዜ በሮብዓም ላይ ተነሱበት፡፡
8አሁንም በዳዊት ዝርያዎች እጅ ውስጥ የሆነውን የእግዚአብሔር አገዛዝ ኃይል ልትቋቋሙ እንደምትችሉ ትናገራላችሁ፡፡ እናንተም ታላቅ ሠራዊት ናችሁ፤ ኢዮርብዓም አማልክት አድርጎ የሠራላችሁ የወርቅ ጥጃዎች ከእናንተ ጋር አሉ፡፡
9የአሮንን ትውልዶች የእግዚአብሔርን ካህናትና ሌዋውያን አላባረራችሁምን? እንደ ሌሎች ምድር ሕዝቦች ልማድ ለራሳችሁ ካህናት አላደረጋችሁምን? ከአንድ ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ጋር ራሱን ሊቀድስ የሚመጣው ሁሉ አማልክት ላልሆኑ ነገሮች ካህን ይሆናል፡፡
10ለእኛ ግን እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ እኛም አልተውነውም፡፡ የአሮን ዝርያዎች የሆኑት እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ካህናትና በሥራቸው ላይ የተሰማሩ ሌዋውያን አሉን፡፡
11በየማለዳውና በየምሽቱ ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ጣፋጩን ዕጣን ያቃጥላሉ፤ የመገኘቱንም ሕብስት በንጹህ ገበታ ላይ ያዘጋጃሉ፤ በየምሽቱ እንዲያበሩ የወርቁን መቅረዝ ከቀንዲሎቹ ጋር ይንከባከባሉ/ይጠብቃሉ፡፡ እኛም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እንጠብቃለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል፡፡
12እነሆ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደ አለቃችን ነው፤ በእናንተ ላይ መለከቶቹን ለመንፋት የእርሱ ካህናትም እዚህ ይገኛሉ፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ ስለማይሳካላችሁ ከአባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር አትዋጉ፡፡
13ኢዮርብዓም ግን ክጀርባቸው ድብቅ ጦር አዘጋጅቶ ነበር፤ የእርሱ ሠራዊት ከይሁዳ ፊት ለፊት ሆኖ ድብቁ ጦር ግን ክጀርባቸው ነበር፡፡
14ይሁዳ ከወደ ኋላ ሲመለከቱ እነሆ ውጊያው ከፊታቸውና ከኋላቸውም ነበር፡፡ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ፤ ካህናቱም መለከቶቹን ነፉ፡፡
15የይሁዳም ሰዎች ጮኹ፤ በጮኹም ጊዜ እግዚአብሔር ኢዮርብዓምንና እስራኤልን ሁሉ በአብያና በይሁዳ ፊት መታቸው፡፡
16የእስራኤል ሕዝብ ከይሁዳ ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔርም በይሁዳ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡
17አብያና ሠራዊቱ በታላቅ አገዳደል ገደሏቸው፤ አምስት መቶ ሺህ የተመረጡ የእስራኤል ሰዎች ተገድለው ወደቁ፡፡
18በዚህ መንገድ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ተሸነፉ፤ የይሁዳ ሕዝብ በአባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ታምነው ስለነበር አሸነፉ፡፡
19አብያ ኢዮርብዓምን አሳደደ፤ ከእርሱም ከተሞችን ወሰደ፤ ቤቴልንና መንደሮችዋን፥ ይሻናንና መንደሮችዋን፥ እንዲሁም ዔፍሮንንና መንደሮችዋን ወሰደ፤
20ኢዮርብዓምም በአብያ ዘመን እንደገና ኃይሉ ከቶም አላገገመም፡፡ እግዚአብሔርም ቀሰፈው፤ እርሱም ሞተ፡፡
21አብያ ግን በረታ፤ ለራሱ አስራ አራት ሚስቶችን ወሰደ፤ ሃያ ሁለት ወንዶች ልጆችንና አስራ ስድስት ሴቶች ልጆችን ወለደ፡፡
22የተቀሩት የአቢያ ድርጊቶችና ባሕርዩ የተናገራቸው ነገሮችም በነቢዩ አዶ ትርጓሜ/አንድምታ ተጽፈዋል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።