መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሁለተኛ ዜና 11

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሮብዓም ኢየሩሳሌም ሲደርስ ከእስራኤል ጋር ተዋግተው መንግሥቱን ወደ ሮብዓም ለመመለስ ወታደሮች የሆኑ መቶ ሰማንያ ሺህ የተመረጡ ሰዎች ከይሁዳና ከቢንያም ቤት ሰበሰበ፡፡
2ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ሸማያ እንዲህ ሲል መጣ፤
3"ለይሁዳ ንጉሥ ለሰለሞን ልጅ ለሮብዓም በይሁዳና በቢንያምም ላሉት ለእስራኤል ሁሉ ተናገር፦
4እግዚአብሔር ይህንን ይላል፦ "ወንድሞቻችሁን ማጥቃት ወይም መዋጋት አይገባችሁም፡፡ ይህ ነገር በእኔ እንዲሆን የተፈቀደ ስለሆነ እያንዳንዱ ሰው ወደ ቤቱ መመለስ ይገባዋል፡፡" በመሆኑም የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ፤ በኢዮርብዓምም ላይ ለማጥቃት ከመውጣት ተመለሱ፡፡
5ሮብዓም በኢየሩሳሌም ይኖር ነበር፤ በይሁዳም ለምሽግነት ከተሞችን ገነባ፡፡
6ቤቴልሔምን፥ ኤጣምን፥ ቴቁሔን፥
7ቤትጹርን፥ ሦኮን፥ ዓዶላምን፥
8ጌትን፥ መሪሳን፥ ዚፍን፥
9አዶራይምን፥ ለኪሶን፥ ዓዜቃን፥
10ጾርዓን፥ ኤሎንን፥ ኬብሮንን ሠራ፡፡ እነዚህ በይሁዳና በብንያም ያሉት የተመሸጉት ከተሞች ናቸው፡፡
11ምሽጎቹንም አጠናክሮ ምግቡንም፥ ዘይቱንም፥ እና ከወይን ጠጁም መጋዘኖች ጋር አለቆቹንም አኖረባቸው፡፡
12በከተሞቹ ሁሉ ጋሻዎችና ጦሮችም አኖረባቸው፤ ከተሞቹንም እጅግ ጠንካራ አደረጋቸው፡፡ ይሁዳና ብንያምም የእርሱ ወገን ነበሩ፡፡
13በመላው እስራኤል የነበሩት ካህናትና ሌዋውያን ከነበሩባቸው ድንበሮች ወደ እርሱ መጡ፡፡
14ለእግዚአብሔር የክህነት ግዴታቸውን ከዚያ በኋላ መወጣት እንዳይችሉ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አስለቅቀዋቸው ነበርና ሌዋውያንም ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም ለመምጣት መሠማሪያቸውንና ቦታቸውን ትተው ነበር፡፡
15ኢዮርብዓም ለመስገጃዎቹና ለሠራቸው የጥጆችና የፍየሎች ጣኦታት ለራሱ ካህናትን ሾመ፡፡
16የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልባቸው የቆረጠ ሰዎች ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ተከትለዋቸው መጡ፤ ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር ለመሰዋት ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡
17በመሆኑም ለሦስት ዓመታት በዳዊትና በሰለሞን መንገድ ስለሄዱ በሦስቱ ዓመታት ውስጥ የይሁዳን መንግሥት አበረቱ፤ የሰለሞንንም ልጅ ሮብዓምን ጠንካራ አደረጉ፡፡
18ሮብዓም የዳዊትን ልጅ የኢያሪሙትን እና የእሴይን ልጅ የኤልያብን ሴት ልጅ የአቢካኢልን ሴት ልጅ መሐላትን ለራሱ ሚስት አድርጎ ወሰደ፤
19እርስዋም ወንዶች ልጆችን የዑስን፥ ሰማራያን፥ እና ዘሃምን ወለደችለት፡፡
20ከመሐላት በኋላ ሮብዓም የአቤሴሎምን ሴት ልጅ መዓካን ወሰደ፤ እርስዋም አብያን፥ ዓታይን፥ ዚዛን እና ሰሎሚትን ወለደችለት፡፡
21ሮብዓምም ከሌሎቹ ሚስቶቹና ቁባቶቹ ሁሉ ይልቅ የአቤሴሎምን ሴት ልጅ መዓካን ወደደ፤ (አስራ ስምንት ሚስቶችና ስልሳ ቁባቶች ወስዶ የሃያ ስምንት ወንዶች ልጆችና የስልሳ ሴቶች የልጅ ልጆች አባት ሆኖ ነበር፡፡)
22ሮብዓምም ንጉሥ ሊያደርገው ስላሰበ የመዓካን ልጅ አብያን በወንድሞቹ መካከል መሪ እንዲሆን አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡
23ሮብዓም በጥበብ ያስተዳድር ነበር፤ ልጆቹንም ሁሉ ወደ ይሁዳና ቢንያም ምድር ሁሉ ወደ ተመሸጉት ከተሞች ሁሉ በተናቸው፡፡ የተትረፈረፈም ምግብ ሰጣቸው፤ ብዙ ሚስቶችንም ፈለገላቸው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።