1ሽማግሌ የሆነውን አትገስጸው፣ ነገር ግን እንደ አባት ለምነው፣ ወጣቶችን እንደ ወንድሞች፣
2አሮጊቶችን እንደ እናቶች፣ ቆነጃጅቶችን እንደ እኅቶች በሙሉ ንጽሕና ለምናቸው፡፡
3በትክክል መበለት የሆኑትን አክብር፤
4ነገር ግን ባሏ የሞተባት ልጆችና የልጅ ልጆች ከሏት፣ እነርሱ ራሳቸው በቤታቸው አክብሮትን፣ ለወላጆቻቸው ብድራት መክፈልን ይማሩ፣ ይህ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው፡፡
5ነገር ግን እውነተኛ መበለት ሁሉን ነገር ትታ በእግዚአብሔር ታምና ትኖራለች፣ ልመናዋን ሁል ጊዜ በእርሱ ፊት በማቅረብ ሌትና ቀን ትጠባበቃለች፡፡
6የሆነ ሆኖ፣ መቀማጠልን የምትወድ ሴት በሕይወትም ብትኖር የሞተች ነች፡፡
7ከወቀሳ የራቁ እንዲሆኑ እነዚህን ነገሮች ስበክ፡፡
8ነገር ግን ማንም ለዘመዶቹ የሚያስፈልጋቸውን የማይሰጥ፣ ይልቁንም ለገዛ ቤተሰቡ የማያስብ እምነትን የካደ ከማያምን ሰው ይልቅ የከፋ ነው፡፡
9ባሏ የሞተባት ሴት በመዝገብ ለመጻፍ እድሜዋ ከስድሳ ማነስ የለበትም፣ የአንድ ባል ሚስትም መሆን አለባት፡፡
10ልጆቿን በሥርዓት የምታሳድግ፣ እንግዶችን የምትቀበል፣ ወይም የቅዱሳንን እግር በማጠብ፣ የተጨነቁትንም በማጽናናት፣ በመልካም ሥራ ሁሉ የተመሰከረላት መሆን አለባት፡፡
11ወጣት መበለቶችን ግን እንደ መበለት አትመዝግባቸው፣ ምክንያቱም የክርስቶስ ተቃራኒ የሆነው ሥጋዊ ፍላጎታቸው ሲያይልባቸው ለማግባት ይፈልጋሉና፡፡
12በዚህ ሁኔታ የቀድሞ እምነታቸውን ስለተዉ በደለኞች ናቸው፡፡
13ለሥራ ፈትነትም ስለሚጋለጡ ከቤት ወደ በት የሚዞሩ ይሆናሉ፡፡ ሥራ ፈቶች መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ሐሜተኞችና በሰው ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ የማይገባውን የሚናገሩ ይሆናሉ፡፡
14ስለዚህ ወጣት ሴቶች እንዲያገቡ እና ልጆችን እንዲወልዱ ቤታቸውንም በመልካም እንዲያስተዳድሩ፣ ተቃዋሚውም ክፉ እንደምናደርግ የሚከስበትን ምክንያት እንዲያሳጡት እመክራለሁ፡፡
15አንዳንዶች ሰይጣንን ለመከተል ዞር ብለዋል፡፡
16መበለቶች ያሏት አንዲት የምታምን ሴት ብትኖር፣ ትርዳቸው፣ ስለሆነም የቤተ ክርስቲያን ሸክም ይቀልላታል እውነተኞቹን መበለቶች ለመርዳት ትችላለች፡፡
17በመልካም የሚያስተዳድሩ መሪዎች በተለይም በቃሉ ስብከትና በማስተማር የሚተጉ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል፡፡
18የእግዚአብሔር ቃል ‹‹የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር›› እንዲሁም ‹‹ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል›› ይላል፡፡
19ሁለት ወይም ሦስት ምስክሮች ሳታገኝ በሽማግሌ ላይ ክስ አትቀበል፡፡
20ሁሉም ይማሩ ዘንድ አጥፊዎችን በሁሉ ፊት ገስጻሳቸው፡፡
21በእግዚአብሔር ፊት፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት፣ በተመረጡትም መላእክት ፊት አዝዝሃለሁ፣ አንዳች አድልኦ ሳታደርግ እነዚህን ደንቦች ጠብቅ፡፡
22በማንም ላይ ቸኩለህ እጅህን አትጫን፣ ከማንም ኃጢአት ጋር አትተባበር፣ ርስህን በንጽሕና መጠበቅ አለብህ፡፡
23በተደጋጋሚ ሆድህን ስለሚያምህ ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ ለወደፊቱ ውኃ ብቻ አትጠጣ፡፡
24የአንዳንድ ሰዎች ኃጢአት በግልጽ የታወቀ ነው፣ ፍርድን ያስከትልባቸዋል፣ አንዳንዶች ግን ኋላ ይከተሉታል፡፡
25ልክ እንደዚሁ አንዳንድ መልካም ሥራዎች የተገለጡ ናቸው፣ ነገር ግን ሌሎቹ በጊዜው የተገለጡ ባይሆንም እንኳ የተሰወሩ አይደሉም፡፡