መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1 ጢሞቴዎስ 6

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእግዚአብሔር ስምና ትምህርቱ እንዳይሰደብ ከቀንበር በታች ያሉ ባሪያዎች ለገዢዎቻቸው የሚገባቸውን ክብር ይስጡ፡፡
2አማኞች የሆኑ ገዢዎች ያሉአቸው ባሪያዎች፣ በእምነት ወንድሞቻቸው ስለሆኑ ገዢዎቻቸውን መናቅ የለባቸውም፡፡ ይልቁንም በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የተወደዱ ወንድሞች በመሆናቸው አብልጠው ያገልግሉአቸው፡፡ እነዚህን ነገሮች አስተምር ግለጽም፡፡
3ማንም ልዩ ትምህርትን ቢያስተምር፣ እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚረዳውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶሰን ቃል እና የእኛንም ጤናማ ቃል ባይቀበል፣
4በትእቢት ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም፡፡ ነገር ግን በክርክርና በቃል በመዋጋት የተለከፈ ነው፣ ከዚህም ምቀኝነት፣ ክርክር፣ መሳደብ፣ ክፉ አሳብና፣ እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፡፡
5እነርሱም አእምሮአቸው የተበላሸባቸው ከእውነትም የራቁ እግዚአብሔርን መምሰል ጥቅም ማግኛ የሚመስላቸው ናቸው፡፡
6ባለው ለሚረካ ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፡፡
7ወደ ዓለም ምንም አላመጣንምና፣ አንዳችም ይዘን መሄድ አይቻለንም፡፡
8ምግብ እና ልብስ ካለን ያ ይበቃናል፡፡
9ባለጠጋ ለመሆን የሚመኙ በፈተና ውስጥ ይወድቃሉ፣ በወጥመድ፣ ሞኝነት በመሰሉ አያሌ ጎጂ ምኞቶች፣ እንዲሁም ሰዎችን በሚያሰጥሙና በሚያጠፉ በሌሎች ነገሮች ላይ ይወድቃሉ፡፡
10የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፡፡ አንዳንድ ሰዎች ይህን ሲመኙ ከእምነት ስተው ራሳቸውን በብዙ ሐዘን ጎዱ፡፡
11አንተ ግን፣ የእግዚአብሔር ሰው፣ ከእነዚሀ ነገሮች ሽሽ፡፡ ጽድቅን፣ እግዚአብሔርን መምሰል፣ ታማኝነትን፣ ፍቅርን፣ ጽናትን እና ለሰዎች መጠንቀቅን ተከታተል፡፡
12መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፡፡ የተጠራህለትን በብዙ ምሥክሮች ፊት ስለመልካምነቱ የመሰከርክለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ፡፡
13ሁሉን ነገር በፈጠረ፣ በእግዚአብሔር ፊት፣ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ፊት እውነትን በመሰከረው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አዝዝሃለሁ፣
14ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ያለነቀፋ ሆነህ ትእዛዛቱን በፍጹምነት ጠብቅ፡፡
15እርሱም መገለጡን የተባረከውና፣ ብቻውን ኃያል የሆነው፣ የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶችም ጌታ በወሰነው በትክክለኛው ጊዜ ያሳያል፡፡
16እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ውስጥ ይኖራል፡፡ ማንም ሰው አላየውም ሊያየውም አይችልም፡፡ ለእርሱ ክብር የዘላለምም ኃይል ይሁን፡፡ አሜን፡፡
17በአሁኑ ዘመን ሀብታሞች ለሆኑት እንዳይታበዩ ንገራቸው፡፡ ደስ እንዲለን እግዚአብሔር በሚሰጠን እውነተኛ ብልጥግና እንጂ እርግጠኛ ባልሆነው በዚህ ምድራዊ ባለጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው፡፡
18በመልካም ሥራ ባለጠጎች እንዲሆኑ፣ መልካም የሆነውን እንዲያደርጉ ለማካፈልም ፈቃደኞች እንዲሆኑ ንገራቸው፡፡
19በዚህ ሁኔታ በሚመጣው ዓለም ለራሳቸው መልካም መሠረትን ይጥላሉ፣ እውነተኛውንም ሕይወት ይይዛሉ፡፡
20ጢሞቴዎስ ሆይ፣ ለአንተ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፡፡ የማይረባውን ወሬ አስወግድ፣ በሐሰት እውቀት ከተባለ እርስ በርሱ ከሚጋጭ ነገር ጋር ከመከራከር ራቅ፡፡
21አንዳንድ ሰዎች ይህ እውቀት አለን በማለት ከእምነት ርቀዋል፡፡ ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።