መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1 ጢሞቴዎስ 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1አሁን ግን መንፈስ በመጨረሻ ዘመን አንዳንድ ሰዎች የራሳቸውን ኅሊና በውሸት በተሞላ ግብዝነት በማደንዘዝ፤
2ለሚያስቱ መናፍስትና ለአጋንንት ትምህርት ትኩረት በመስጠት እምነትን ይክዳሉ በማለት በግልፅ ይናገራል፡፡
3እውነትን ለማወቅ የመጡትን አማኞች ከምሥጋና ጋር ከሚቀበሉትና እርስበርሳቸው ከሚካፈሉት እግዚአብሔር ከፈጠረው ምግብ እንዲርቁ፣ ጋብቻንም እንዳያደርጉ ይከለክላሉ፡፡
4በእግዚአብሔር የተፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና፤ በምሥጋና የሚቀበሉት እንጂ የሚጣል የለውም፡፡
5በእግዚአብሔር ቃልና በጸሎት የተቀደሰ ነው።
6እነዚህን ነገሮች ለወንድሞች ብታስረዳ፣ በእምነት ቃሎች እና በተከተልከውም መልካም ትምህርት የምትመገብ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ፡፡
7ራስህን እግዚአብሔርን ለመምሰል አሰልጥን እንጂ፣ አሮጊቶች የሚወዱአቸውን አለማዊ ተረቶችን አትቀበል፡፡
8የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለጥቂት ነገር ይጠቅማል፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን መምሰል ለአሁኑና ለሚመጣውም ሕይወት ተስፋ ስላለው ለሁሉ ነገር ይጠቅማል፡፡
9ይህ መልእክት የታመነና ሁሉም ሊቀበሉት የተገባው ነው፡፡
10ለዚህም እንታገላለን ጠንክረንም እንሠራለን፣ ይህም የሚሆነው ሰዎችን ሁሉ በተለይም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው እግዚአብሔር ስለምንታመን ነው፡፡
11እነዚህን ነገሮች አውጅ አስተምርም፡፡
12ማንም ወጣትነትህን አይናቀው፣ ነገር ግን በዚህ ፈንታ፣ በቃልና በሥራ፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና የእምነት ምሳሌ ሁን፡፡
13እስክመጣ ድረስ፣ ማንበብህን፣ መምከርህን እና ማስተማርህን ቀጥል፡፡
14በትንቢት ከሽማግሌዎች የእጅ መጫን ጋር ለአንተ የተሰጠህን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል፡፡
15ለእነዚሀ ነገሮች ተጠንቀቅ፣ በእነርሱም ጽና፣ ይህን በማድረግህ ማደግህ በሁሉም ዘንድ ይገለጻል፡፡
16ለራስህ እና ለትምህርቱ ተጠንቀቅ፣ በእነዚህም ጽና ይህን ብታደርግ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።