1አንድ ሰው መሪነትን ቢፈልግ፣ መልካምን ሥራ ተመኝቶአል፣ የሚለው አባባል የታመነ ነው፡፡
2ስለዚህ መሪው ነቀፋ የሌለበት፣ የአንዲት ሚስት ባል፣ በመጠን የሚኖር፣ አስተዋይ፣ ሥርዓት ያለው፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ለማስተማር የሚበቃ፣
3የማይሰክር፣ የማይጨቃጨቅ፣ ነገር ግን፣ ለሌሎች የሚጠነቀቅ፣ ሰላማዊ፣ ገንዘብን የማያፈቅር መሆን አለበት፡፡
4ቤቱን በመልካም የሚያስተዳድርና ልጆቹም በሁሉም ረገድ የሚታዘዙለት ለሆን ይገባል፤
5ሰው የራሱን ቤት በመልካም ማስተዳደር የማያውቅ ከሆነ ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንዴት ሊጠነቀቅ ይችላል?
6ዲያብሎስ በትእቢት እንደወደቀ እንዳይወድቅ አዲስ አማኝ የቤተ ክርስቲያን መሪ አይሁን፤
7በውጭ ባሉት ዘንድ መልካም ምስክርነት ያለው ሊሆን ይገባል፣ በመሆኑም በነቀፋ እና በዲያብሎስ ወጥመድ አይወድቅም፡፡
8ዲያቆናትም እንዲሁ፣ የተከበሩ፣ ቃላቸው አንድ የሆነ፣ ብዙ የወይን ጠጅ የማይጠጡ፣ የማይስገበገቡ መሆን አለባቸው፡፡
9በንጹህ ኅሊና የተገለጠውን የእምነት እውነት ሊጠብቁ ይገባቸዋል፡፡
10አስቀድመው ይገምገሙ፣ ከዚያም ያለነቀፋ ሆነው ከተገኙ በዲቁና አገልግሎት ይሾሙ፡፡
11እንዲሁም ሴቶች የተከበሩ፣ የማያሙ፣ ልከኞችና በሁሉ ነገር የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል፡፡
12ዲያቆናት እያንዳንዳቸው የአንዲት ሚስት ባል መሆን አለባቸው፤ ቤታቸውንና ልጆቻቸውንም በመልካም የሚያስተዳሩ ሊሆኑ ይገባል፡፡
13መልካም አገልግሎት የሚያበረክቱ እነርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ ባላቸው እምነት ለራሳቸውእውነተኛ መሠረትና ድፍረትን ያገኛሉ፡፡
14እነዚህን ነገሮች ስጽፍልህ ወደ አንተ በቅርቡ እንደምመጣ ተስፋ በማድረግ ነው፡፡
15ነገር ግን ብዘገይ፣ በእግዚአብሔር ቤት፣ ማለትም የእውነት ዓምድና መሠረት በሆነው፣ በሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንዴት መኖር እንደሚገባህ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፡፡
16እኛ ሁላችን በዚህ እንስማማለን፡- ‹‹የተገለጠው እግዚአብሔርን የመምሰል ምስጢር ታላቅ ነው፣›› ይህም በሥጋ የተገለጠው፣ በመንፈስ የጸደቀው፣ በመላእክት የታየው፣ በሕዝቦች መካከል የታወጀው፣ በዓለም የታመነው፣ በክብር ወደ ሰማይ ያረገ ነው፡፡